ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ህዳር 24፣ 2013/ የመንግሥት ንብረት አልሰጥም ያለው የወ/ሮ ኬሪያ ሾፌር

ኢንስፔክተር ወልዳይ አብርሃ የቀድሞዋ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ሾፌር ነው፡፡ 

ወ/ሮ ኬሪያ ስልጣናቸውን ለቀው መቐለ  በአውሮፕላን ከመብረራቸው በፊት ሾፌሩን 2 ልጆቻቸውን ቀድሞ መንግሥት በመደበላቸው እና ለ 2ዓመት ዘወትር ከእሳቸው ጋር በቆየው V-8 መኪና እንዲወስድ ነገሩት፡፡

ሾፌራቸው ኢንስፔክተር ወልዳይ እንደተባለው እሁድ ማለዳ ልጆቹን ይዞ መቐለ ተጓዘ፡፡ ከወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ጋር መቐለ ተገናኙ፡፡ 

ወ/ሮ ኬሪያ መኪናው በትግራይ ክልላዊ መንግሥት ስም አዙረዋለው ስለዚህ መኪናው አይሄድም ሲሉ ለሹፌሩ ነገሩት፡፡ ሹፌሩም ይህ እንደማይሆን አስረድቷቸው በራሱ ውሳኔ ሌሊት ጉዞውን ሳያሳውቅ  መኪናውን ይዞ ተመልሷል፡፡ 

ተህቦ ንጉሴ ለ 2ዓመት መንግሥት ለወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የመደበውን V-8 መኪና ሲያሽከረክር የነበረውን ኢንስፔክተር ወልዳይ አብርሃን አነጋግሮታል፡፡
 

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ