ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ግንቦት 21፣2012/ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5015 የላብራቶሪ ምርመራ 137 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚንስትር ተናገረ

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5015 የላብራቶሪ ምርመራ 137 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚንስትር ተናገረ፡፡

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 968 ደርሷል። 

በተጓዳኝ ህመም ምክንያት ህክምና ላይ የነበሩ የ62 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወንድ ለኮሮና ቫይረስ የላብራቶሪ ናሙና ተወስዶ ውጤቱ ሳይደርስ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤የምርመራው ውጤት ቫይረሱ እንዳለባቸው ስላረጋገጠ በቫይረሱ የሞቱ ቁጥር 8 ደርሷል።

በተጨማሪም በትናንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ 6 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ እስካሁን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 197 ደርሷል፡፡

በአሁኑ ወቅት 4 ሰዎች በፅኑ ሕክምና መስጫ ውስጥ እንደሚገኙም የጤና ሚኒስቴር ካወጣው መረጃ ለማየት ችለናል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ