ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ግንቦት 21፣ 2012/ የሼህ ሆጀሌ አል ሀሰን ኡመድ የአዲስ አበባ ማረፊያ የነበረው የመኖሪያ ሕንፃ ቅርስን ለማደስ የ10 ሚሊዮን ብር በጀት ሊፀድቅለት ነው ተባለ

የሼህ ሆጀሌ አል ሀሰን ኡመድ የአዲስ አበባ ማረፊያ የነበረው የመኖሪያ ሕንፃ ቅርስን ለማደስ የ10 ሚሊዮን ብር በጀት ሊፀድቅለት ነው ተባለ፡፡

በጉለሌ ክፍለ ከተማ፣ ሩፋኤል አካባቢ የሚገኘው የበርታ ብሔረሰብ ገዥ የነበሩት ሼህ ሆጀሌ አል ሀሰን ኡመድ የአዲስ አበባ መቆያ በነበረው ቤት ይኖሩ ለነበሩ ሰዎች ሌላ የተገነባ መኖሪያ እንዲያገኙ ይደረጋል መባሉን ሰምተናል፡፡

ወሬውን የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አንድ የስራ ሀላፊ ለሸገር ነግረዋል፡፡ቅርሱን ለማደስ እና ታሪካዊነቱን ለመዘከር የከተማ መስተዳድሩ የ10 ሚሊዮን ብር በጀት ያፀድቅለታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የስራ ሀላፊው ነግረውናል፡፡

ዛሬ በስማቸው ከሚጠራው መስጂድ አቅራቢያ የሚገኘው ይኸው መኖሪያ፣ ሼህ ሆጀሌ አልሀሰን ኡመድ በአፄ ምንሊክ ዘመን ለንጉሰ ነገስቱ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ይዘው ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ያርፉበት የነበረ ቤት እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ