ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ግንቦት 21፣2012/ ለ2012 በጀት ዓመት 48.3 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ፀደቀ

ለ2012 በጀት ዓመት 48.3 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ፀደቀ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አምስተኛ ዓመት 4ኛው ልዩ ስብሰባ ነው ተጨማሪ በጀቱን ያፀደቀው፡፡ተጨማሪ በጀት ሆኖ ከፀደቀው 48.3 ቢሊየን ብር ውስጥ 28.3 ቢሊዮን ብሩ ከውጭ አገራት እንዲሁም 20 ቢሊዮን ብሩ ከሀገር ውስጥ የሚገኝ መሆኑንን ሰምተናል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለእንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ ተጨማሪ በጀቱ የኮሮና ወረርሺኝ በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለመቋቋም ያለመ ነው ብለዋል፡፡

ከእንደራሴዎች ምክር ቤት ማህበራዊ የትስስር ገፅ እንደተመለከትነው የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ለተጨማሪ በጀቱ ከውጭ የሚገኘው ብድር የዋጋ ንረትን እንዳያስከትል ጥንቃቄ የተሞላበት የብድር ሂደት እንከተላለን ብለዋል፡፡

ለፌዴራል መንግስት የ2012 በጀት ዓመት 386.9 ቢሊዮን ብር ሆኖ ባለፈው ዓመት መፅደቁ ይታወሳል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ