ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2020-12-27
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አጠቃላይ ገቢዬ 3.1 ቢሊየን  ብር ደርሶልኛል አለ፡፡ ባንኩ በተጠናቀቀው የጎርጎሮሲያኑ በጀት ዓመት ከግብር  በፊት 781 ሚሊዮን አትርፌአለው ብሏል፡፡ ባንኩ በዚሁ ጊዜ  8.3 ቢሊየን ብር ማበደሩን ተናግሯል፡፡ አጠቃላይ የብድር ክምችቱ 19.1 ቢሊየን ደርሷል ብሏል፡፡ የውጪ ምንዛሬ 169.6 ሚሊየን ዶላር ማግኘቱን ባንኩ ዛሬ መደበኛና ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ጊዜ ሰምተናል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 31.8 ቢሊየን ብር መድረሱን ከቀረበ ሪፖርት ተመልክተናል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ እዳ 28.3 ቢሊየን ብር የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 2.2 ቢሊየን ብር እንደደረሰ ተነግሯል፡፡ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ባንኩን ቢፈትነውም የተቀማጭ ገንዘቡን በማሰባሰብ በኩል ውጤት ማግኘቱን ተናግሯል፡፡
2020-12-27
ዘመን ባንክ በ2012 በጀት ዓመት 1 ቢሊዮን 46 ሚሊዮን ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ተናገረ፡፡ ባንኩ በዓመቱ ያገኘሁት ትርፍ በእቅዴ ይዤው ከነበረው የትርፍ መጠን የ29 በመቶ ጭማሪ አለው ብሏል፡፡ የ2012 በጀት ዓመት ትርፉ ከቀዳሚው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ388 ሚሊዮን ብር ወይንም የ59 በመቶ እድገት ማሳየቱን ተናግሯል፡፡ ዘመን ባንክ ዛሬ ጉባኤውን ባለ አክሲዮኖች በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል። ባንኩ ትርፌ ለማደጉ የብድር አቅርቦት እና በአገልግሎት ዘርፍ የተመዘገበው አፈፃፀም ከፍተኛ ድርሻ አበርክቶልኛል ብሎ ሲናገር ሰምተናል፡፡ ባንኩ በ2012 በጀት ዓመት ያገኘው አጠቃላይ ገቢ 2.15 ቢሊዮን ብር ነው የተባለ ሲሆን ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ570 ሚሊዮን ብር ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል፡፡ ዘመን ባንክ በአጠቃላይ ሀብቱ 18.5 ቢሊዮን ብር መድረሱን፣የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 1.8 ቢሊዮን መድረሱን ተናግሯል፡፡ ባንኩ የሰጠሁት ብድር 9.7 ቢሊዮን ብር ደርሷልም ተብሏል፡፡ ባንኩ ተጨማሪ ያንብቡ
2020-12-24
ንብ ባንክ በዘንድሮው የባንኩ የበጀት ዓመት 1.3 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ፡፡  የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 3.44 ቢሊዮን መድረሱንም ሰምተናል፡፡ ንብ ባንክ በአውሮጳውያኑ 2020 የበጀት ዓመት በአጠቃላይ 25.8 ቢሊዮን ብር ማበደሩን ተናግሯል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብም 33.7 ቢሊዮን ብር መድረሱን ባንኩ ለባለድርሻዎች ዓመታዊ ሪፖርቱን ሲያቀርብ ሰምተናል፡፡በባንኩ ገንዘባቸውን ያኖሩ ሰዎች ቁጥር ከባለፈው አመት መጨመሩ ተሰምቷል፡፡ ባንኩ አጠቃላይ ገቢዬ 4.55 ቢሊዮን ብር ደርሷል ብሏል፡፡ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ባስገነባው ባለ 32 ወለል ሕንፃ ውስጥ ዘንድሮ ሥራ እንደሚጀምር ተናግሯል፡፡ ባንኩ ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቀሴዎች 21.9 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማደረጉን እወቁልኝ ብሏል፡፡  
2020-12-24
ዳሽን ባንክ የተከፈለ ካፒታሉን ከ3.5 ቢሊዮን ወደ 5.5 ቢሊዮን ማሳደጉን ተናገረ፡፡ ዳሽን ባንክ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘቡ መጠን 53.49 ቢሊዮን ብር፣ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ደግሞ 68.26 ቢሊዮን ብር መድረሱን ተናግሯል፡፡ ባንኩ ዛሬ ባካሄደው ጠቅላላ የባለድርሻዎች ጉባዔ ላይ ዓመታዊ ሪፖርቱን ሲያቀርብ በመጠናቀቅ ላይ ባለው የአውሮፓውያን ዓመት ባንኩ 1.79 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ተናግሯል፡፡ ዳሽን ባንክ ከ3 ዓመት በፊት የጀመረው የአሞሌ ዘመናዊ ክፍያ ገንዘብ ማስተላለፍያ ደንበኞቹ ቁጥር ከ3 ሚሊዮን እንዳለፈ ተናግሯል፡፡ ሀገሪቱ የጀመረችውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ለማደርጀትም ባንኩ በተለያዩ ፕሮጀክቶች እንደሚሰማራ ተናግሯል፡፡ የዳሽን ባንክ የዓመቱ አጠቃላይ ወጪ 5.4 ቢሊዮን ብር መሆኑን ከዓመታዊ ሪፖርቱ ተመልክተናል፡፡ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የተፈለገውን ያህል የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት እንዳላስቻለው የተናገረው ባንኩ፣ እንዲያም ሆኖ ከወጭ ንግድ እና ከሐዋላ በአመቱ 562.8 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን ተናግሯል፡፡ የውጭ ምንዛሪ ተጨማሪ ያንብቡ
2020-12-24
ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለዘመናዊ ግብርና፤ ለዘመነ አርሶ አደር
2020-12-23
ኢጋድ የፖለቲካም የኢኮኖሚም መንገድ  
2020-12-22
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና፤ ዕድሎችና ፈተናዎች  
2020-12-21
ቡና ባንክ በዘንድሮ በጀት ዓመት መጨረሻ ከ10 የውጭ ባንኮች ጋር የቀጥታ ግንኙነት መሥርቼ እየሠራሁ ነው ብሏል። ባንኩ በጎርጎሮሳውያኑ 2020 ዓመት የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 13.88 ቢሊዮን ብር ደርሶልኛል ብሏል። ባንኩ በበጀት ዓመቱ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች 11.57 ቢሊዮን ብር ብድር መስጠቱን ሰምተናል። ቡና ባንክ ካበደርኩት ገንዘብ ከፍተኛውን ምጣኔ የሚይዘው ለገቢ እና ወጭ ንግድ፣ እንዲሁም ለግንባታና ኮንስትራክሽን የሰጠሁት ነው ብሏል። ባንኩ በዘንድሮ በጀት አመት 159.6 ሚሊዮን የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱን ዓመታዊ ሪፖርቱን ሲያቀርብ አድምጠናል። ቡና ባንክ ካስገባው አጠቃላይ የውጭ ምንዛሪ ውስጥ 111 ሚሊዮን ዶላሩን ከወጭ ንግድ ማግኘቱን ተናግሯል። 28.4 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ከውጭ ሀገር በሐዋላ እና በስዊፍት የተገኘ ነው ብሏል። የኮቪድ 19 ተፅዕኖ የውጭ ምንዛሪ ግኝቱ ዝቅ እንዲል ማድረጉን ባንኩ ተናግሯል። የባንኩ አጠቃላይ ገቢ 2.173 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተሰምቷል። የቡና ባንክ አጠቃላይ ሀብት ወደ 18.87 ተጨማሪ ያንብቡ
2020-12-21
ዳሽን ባንክ በአሞሌ አማካኝነት በወር ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ልውውጥ እየተደረገበት ነው ማለቱ ተሰማ፡፡ ዳሽን ባንክ አሞሌ የዓመቱን ዓለም አቀፍ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዲጂታል ከፍተኛ ዋሌት ሽልማት ማሸነፌን እወቁልኝ ብሏል፡፡ አሞሌ አሁን ከ3 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች  እንዳለው ታውቋል፡፡ ባንኩ ከ2010 ጀምሮ ከሞኔታ ቴክኖሎጂ አ.ማ ጋር በመተባበር አሞሌ የተሰኘው ዘመናዊ የክፍያ ገንዘብ የማስተላለፍና ግብይት የማስፈፀም አገልግሎት እየሰጠ ነው ተብሏል፡፡ ዳሽን ባንክ አሞሌን ለደንበኞቹ ከማስተዋወቁ በፊት የነበሩት የዲጂታል ደንበኞች ቁጥር 50,000 እንደነበር ባንኩ ከላከልን መረጃ አንብበናል፡፡ ዳሽን ባንክ ብሔራዊ ባንክ ያለመውን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማበርታት ከጥሬ ገንዘብ ውጭ ግብይትን ከፍ ለማድረግ የአሞሌን እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን ያሳድጋል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ሸዋ ሱፐር ማርኬት፣ ዲኤስ ቲቪ፣ ለሚ ቡክስ፣ ዚሞል ሾፒንግ፣ ኤታ ታክሲ፣ ህዳሴ ቴሌኮምና ሌሎች ተቋማት በአሞሌ አማካኝነት አብረው ተጨማሪ ያንብቡ
2020-12-21
እናት ባንክ ተቀማጭ ገንዘቤ 8.4 ቢሊዮን ብር ደርሷል አለ፡፡ በ2012 በጀት ዓመት ከባንኩ አስቀማጭ ደንበኞች ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡ የእናት ባንክ አጠቃላይ ሀብቱ 11.2 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተሰምቷል፡፡ ባንኩ ለወለድ 656 ሚሊዮን ብር ክፍያ ፈፅሟል፡፡ የባንኩ ጠቅላላ ወጭ 1.09 ቢሊዮን ብር መሆኑ ከ7ተኛው ዓመታዊ ሪፖርት ተመልክተናል፡፡ በበጀት ዓመቱ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 1.4 ቢሊዮን ብር ደርሷል መባሉን ሰምተናል፡፡