ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2020-11-26
አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮኮብ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ከዚህ አለም በሞት ተለየ።  ማራዶና ህይወቱ ያለፈችው በ60 ዓመቱ መሆኑን BBC አውርቷል። የቀድሞው ኮኮብና አሰልጣኝ በቅርቡ የጭንቀት ደም መርጋት ቀዶ ህክምና ማድረጉን የወሬ ምንጩ ፅፏል። ከአለማችን የእግር ኳስ ኮከቦች መካከል ስሙ ጎልቶ የሚነሳው ማራዶና ሀገሩ አርጀንቲና የ1986ቱን የአለም ዋንጫ ስታነሳ ቡድኑን በአንበልነት መርቷል። አርማንዶ ማራዶና ለስፔኑ ባርሴሎና እንዲሁም ለጣሊያኑ ናፖሊ ተጫውቶ አሳልፏል። ሀገሩን በ4 የአለም ዋንጫ ወክሎ የተጫወተው ኮኮቡ ለሀገሩ በተጫወተባቸው 91 ጨዋታዎች 34 ጎሎች አስቆጥሯል። ማራዶና ከተጫዋችነቱ በተጨማሪ ሀገሩን በአሰልጣኝነት አገልግሏል ፣የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ሜክሲኮ አገር ክለቦችንም አሰልጥኗል።
2019-12-31
ሞሮኳዊው አብድረዛቅ ሃምዳላህ የ2019 የዓለማችን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኗል።ሃምዳላህ የሳውዲ ሊግ ክለብ የኾነው አል ናስር ተጫዋች ነው።ባሳለፍነው ቅዳሜ አል ፊያህ ላይ ባስቆጠራቸው 3 ጎሎች ወደ ዓለማችን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ተሸጋግሯል። ተጫዋቹ 57 ጎሎችን በማስቆጠር እንደ ሮበርት ሌቫንዶቭስኪና ሊዮ ሜሲ ያሉ ከዋክብቶችን በመብለጥ የ2019 ውድድር ዘመን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብርን አግኝቷል። ኤሪክ ቤይ ወደ ጨዋታ ሊመለስ ተቃርቧል።ቤይ ጉልበቱ ላይ ከተደረገለት ቀዶ ጥገና በኃላ ማገገም በመቻሉ በቅርብ ጊዜ ወስጥ ለጨዋታ ዝግጁ ይሆናል ተብሏል።ትናንት የመጀመሪያ ልምምዱን ማድረጉም ተሰምቷል።ይህ ኮትዲቫራዊ ተጫዋች ለክለቡ በሁሉም ውድድሮች የተሳተፈባቸው የጨዋታ ብዛት 7 ብቻ ነበሩ። ካሪም ቤንዜማ ከሪያል ማድሪድ ጋር ያለውን የውል ስምምነት አሯዝሟል።ቤንዜማ ውሉን ያደሰው ለተጨማሪ 1 ዓመት ነው።አዲሱ የውል ስምምነት ተጫዋቹን በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት እስከ 2022 የውድድር ዘመን ድረስ ያከርመዋል።የቤንዜማ ተጨማሪ ያንብቡ
2019-12-30
ዴቬድ ሞይስ የዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኝ ሹመትን አግኝተዋል።የ55 ዓመቱ ስኮትላንዳዊ ጎልማሳ ሞይስ የዌስትሃም አሰልጣኝነት መንበርን ሲቆናጠጡ ለሁለተኛ ጊዜያቸው ነው።ከዚህ ቀደም 2017 የውድድር ዘመን ማብቂያ ላይ ስላቨን ቢሊችን ተክተው የምስራቅ ለንደንኑን ክለብ በኋላፊነት መረከባቸው ይታወሳል። ትላንት ምሽት በተሰማ ወሬ በኤቨርተን፣ማንችስተር ዩናይትድ፣ሪያል ሶሴይዳድ እንዲሁም ሰንደርላንድ ክለቦች የሚታወቁት ዴቪድ ሞይስ የማኑዌል ፔሌግሪኒ ስንብትን ተከትለው ክለቡን በኋላፊነት ለዳግም ዙር ተረክበዋል።ክለቡ ቅዳሜ ዕለት በሌስተር ሲቲ 2 ለ 1 መሸነፉ የፔሌግሪኒንን ሰንብት እንዳፋጠነው ተገልጿል።የዌስትሃም ኋላፊዎች ከሽንፈቱ በኋላ በክለቡ ለ18 ወራት የከረሙት ፔለረግሪንን ለመሸኘት ከ2 ሰዓታት በላይ መታገስ እንዳልቻሉ ቢቢሲ ስፖርት ተናግሯል። ክርስቲያኖ ሮናልዶ የ2019 ግሎብ ሶከር አዋርድ አሸናፊ ሆኗል።ከ2011 ጀምሮ ለዚህ የሽልማት ስነ ስርዓት ቤተኛ ነው የሚባለው ፖርቱቹጋላዊው ኮከብ ሮናልዶ ይህን ክብር ሲጎናፀፍ ተጨማሪ ያንብቡ
2019-12-27
ዐቢይ ነጥቦች፡   በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት አንድ ቀሪ ጨዋታ በሞልኒክስ ስታዲየም ዛሬ ምሽት 4፡45 በባለሜዳዎቹ ዎልቭሶች እና ማንችስተር ሲቲ መካከል ይደረጋል።   በዎልቭሶች ቤት ምንም ዓይነት አዲስ የተጫዋቾች ጉዳት ወሬ አለመሰማቱ እንደ በጎ ነገር ቢቆጠርላቸውም የአምናው የፕሪምየር ሊግ ባለክብሩን ማንችስተር ሲቲን ማስተናገዳቸውና ከ45 ሰዓታት በኋላ አንፊልድ ላይ ከጠንካራው ሊቨርፑል ጋር የሚጫወቱ መኾናቸው ምናልባት ነገሮች አሰልጣኝ ኑኖ ኤስፕሪቶ ሳንቶስን ቅዠት ውስጥ ሊከታቸው ይችላል።   በአንፃሩ ሲቲዎች ባሳለፍነው ሳምንት ሌስተሮችን ማሸነፋቸው የፈጠረላቸውን የመነቃቃት ስሜት የምሽቱን ጨዋታ በማሸነፍ ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል ጋር ያላቸውን ሰፊ የነጥብ ልዩነትን ለማጥበብ ሊጠቀሙበት ይችላሉ የሚሉ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ይገኛሉ።   ሲቲዎች ከዚህ ጨዋታ በኋላ እሁድ ምሽት 3፡00 በሜዳቸው ኢትሃድ ከሼፊልድ ጋር ይጫወታሉ።   የተጫዋቾች የጉዳት ወሬ፡   በባለሜዳዎቹ ዎልቭሶች ተጨማሪ ያንብቡ
2019-12-27
የሀገር ውሰጥ ስፖርታዊ ወሬ፡ የጨዋታዎች ጥቆማ፡ 5ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ መርሃ ግብሮች፡ ነገ ታህሳሰ 18፣2012 ወላይታ ዲቻ ከ ወልቂጤ ከተማ ስሁል ሽረ ከ ከአዳማ ከተማ ጅማ አባጅፍር ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና ድሬድዋ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና ሀዲያ ሆሳዕና ከ ባህር ዳር ከተማ እሁድ - ታህሳሰ 19፣2012 ሰበታ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ መቖለ 70 እንደርታ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ = = = = = = = = = = = = = = የባህር ማዶ ስፖርታዊ ወሬዎች፡ የቦክሲንግ ደይ ጨዋታ ውጤቶች፡ ፨ ቶተንሃም ( 2 - 1 ) ብራይተን ፨ አስቶን ቪላ ( 1 - 0) ኖርዊች ሲቲ ፨ ኤቨርተን ( 1 - 0 ) በርንሌይ ፨ ክሪስታል ፓ.( 2 - 1 )ዌስትሃም ፨ ቼልሲ ( 0 - 2 ) ሳውዛምፕተን ፨ በርንማውዝ ( 1 - 1 )አርሰናል ፨ ሼፊልድ ( 1 - 1 ) ዋትፎርድ ፨ ማን ዩናይትድ ( 4 - 1 ) ኒውካስል ፨ ሌስተር ( 0 - 4 ተጨማሪ ያንብቡ
2019-12-26
የቦክሲንግ ደይ የጨዋታ መርሃግብሮች ቅድመ ዳሰሳ(PL Boxing day matches preview) ዐቢይ ነጥቦች፡ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አንደኛ እና ሁለተኛ ላይ የሚገኙት ሊቨርፑልና ሌስተር ሲቲ ምሽት 5 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ ልዩ ትኩረት አግኝቷል፣ በርካታ ሃሳቦችም እየተሰነዘሩ ይገኛሉ።ሁለቱ የቅርብ ተሿሚዎች፣ የአርሰናሉ ሚኬል አርቴታ እና የኤቨርተኑ ካርሎ አንችሎቲ ክለቦቻቸውን እየመሩ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ሌሎቹ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው።የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከዓለም የክለቦች ዋንጫ አሸናፊነት ማግስት ወደ ኪንግ ፓወር ተጉዘው ምርጡ ሌስተር ሲቲን ይገጥማሉ። ባሳለፍነው ሳምንት በቼልሲ በአሳማኝ ሁኔታ ሁለት ለዜሮ የተሸነፉት ቶተንሃሞች በሜዳቸው ብራይተን ኤንድ ኦቭ አልቢዮንን ያስተናግዳሉ። ዦዜ ሞሪንሆ በቀድሞ ተጫዋቻቸው ፍራንክ ላምፓርድ ብልጫ ባለው ታክቲክ ከደረሰባቸው ሽንፈት ለማገገም የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ይኖርባቸዋል።በአጠቃላይ የሰሞኑን ጨዋታዎች ማሸነፍ የሚችሉ ቡድኖች ድሎቻቸው እንደ ጥሩ የገና ተጨማሪ ያንብቡ
2019-12-26
የዓለም የክለቦች ሻምፒዮና የኾኑት ሊቨርፑሎች በአንድ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ላይ ብቻ ወርቃማውን ባጅ ለብሰው እንዲጫወቱ ይኹንታን ማግኘታቸውን ዘ ቴሌግራፍ ተናግሯል። ሁነኛ አሰልጣኝ በማፈላለግ ላይ የሚገኙት የፈረንሳዩ ክለብ ሞናኮ ኃላፊዎች ዐይናቸውን ወደ ቀድሞው የአርሰናል አሰልጣኝ ስፔናዊው ኡናይ ኤምሬ እያማተሩ ናቸው ተብሏል።የባስኩ ሰው የመድፈኞቹን ቤት ከተሰናበቱ ወዲህ ከሥራ ወጪ መኾናቸው ይታወቃል። የስፔኑ የወሬ ምንጭ አስ ባወጣው መረጃ ደግሞ ኤምሬ በሞናኮ የአሰልጣኝነት ህይወት አልሰምርልህ ያለውን ሊዮናርዶ ዣርዲምን ምናልባት ሊተኩ ይችላሉ ብሏል። የአርሰናሉ ወጣት ተጫዋች ቡካዮ ሳካ ለየትኛው ብሔራዊ ቡድን መጫወት እንዳለበት አስካሁን አለመወሰኑ ተሰምቷል።እንደ ዘ ሰን ዘገባ ከኾነ ይህ የ18 ዓመት የክንፍ ተጫዋች የእንግሊዝ ዜግነት ቢኖረውም ለምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን የመጫወት እድል አለው ተብሏል። ዐቢይ ሐብታሙ
2019-12-25
የአር ቢ ሳልዝቡርግ ክለብ ተጫዋች ኢርሊንግ ሃላንድ ቀጣይ ክለብ ታውቋል የሚል የጭምጭምታ ወሬ ከወደ ጣልያን ተሰምቷል።እንደ ማንችስተር ዩናይትድ እና የጀርመኑ አር ቢ ላይፕዚንግ ያሉ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ደግሞ የተጫዋቹ ብርቱ ፈላጊዎች ናቸው።ነገር ግን እንደ ኮሬሪዮ ዴሎ ስፖርት የወሬ ምንጭ ከሆነ ሃላንድን የማስፈረም አሽቅድድም በዩቬንቱሶች አሸናፊነት መጠናቀቁ ተነግሯል።ሃላንድ የሴሪ ኤውን ክለብ የመቀላቀሉ ጉዳይ እውን ከኾነ ዩቬንቱሶች ለዝውውሩ 30 ሚለዮን ዩሮ ወጪ ያደርጋሉ ተብሏል። የእንግሊዙ ክለብ ኒውካስትል ዩናይትድ ከወደ አሜሪካ የግዢ ጥያቄ ቀርቦለታል መባሉን ስካይ ስፖርት ተናግሯል። እንደ ወሬ ምንጩ መረጃ ከሆነ አሜሪካዊው ዲታ ጆሴፍ ዳግሮሳ ክለቡን ስለመግዛት ላሳዩት ፍላጎት ማረጋገጫ ሰጥተውበታል ተብሏል።የኢንቨስተሩ ዳግሮሳ ክለቡን በባለቤትነት የመጠቅለል ውጥናቸው እውን ይኾን ዘንድ የኒውካስትሉ አለቃ ይኹንታ ያስፈልጋል መባሉን በመረጃው ተጠቅሷል።ዳግሮሳ አሜሪካን ካፒታል ፓርትነርስ በተባለው ኩባንያቸው በኩል ተጨማሪ ያንብቡ
2019-12-25
የ14ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የመዝጊያ ስነ ስርዓት በኢንተር ኮንቲነንታል አዲስ ሆቴል ተካሂዷል። የመዝግያ ስነ ስርዓቱ ዋና አካል የነበረው የሽልማት መርሃ ግብርም ተከናውኗል። የቅዱስ ጊዮርጊሱ ሳላዲን ሰኢድ ለሽልማት በታጨባቸው ሁለት ዘርፎች አሸንፏል። የተሸለመባቸው ዘርፎች በውድድሩ ባስቆጠራቸው 4 ጎሎች በኮከብ ግብ አስቆጣሪነት እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ ላይ ባስቆጠራት ጎል በምርጥ ጎል አስቆጣሪነቱ ዘርፍ ነው። የኢትዮጵያ ቡናው ፈቱዲን ጀማል የውድድር ኮከብ ተጨዋች ተብሏል። የኮከብ አሰልጣኝነትን ክብርን ደግሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሰርዳን ዝቪችሆቪሰች አሸንፈዋል። አለን ፓርዲው ወደ አሰልጣኝነት መንበር ዳግም ተመልሰዋል። የቀድሞው የኒውካስትል ዩናይትድና ዌስትሃም አለቃ እንግሊዛዊው የ58 ዓመት ጎልማሳ አለን ፓርዲው በደች ዋናው ሊግ ወይም ኤሪዲቪዜ ላይ የሚወዳደረው አዶ ደን ሀግ አሰልጣኝ ተደርገው መሾማቸውን ቢቢሲ ስፖርት ተናግሯል። የፓርዲው ኋላፊነት እስከ ውድድር ዘመኑ ማብቂያ ድረስ የሚዘልቅ ተጨማሪ ያንብቡ
2014-12-24
  ኴስ ሜዳ ታህሳስ 19