ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2020-10-29
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 481 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 7,773 የላብራቶሪ ምርመራ 481 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ ባለፋት 24 ሰዓታት የ6 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,457 አድርሶታል። በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 867 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 50,753 አድርሶታል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 95,301 ደርሷል፡፡
2020-10-29
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 602 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 6,290 የላብራቶሪ ምርመራ 602 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ ባለፋት 24 ሰዓታት የ6 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,451 አድርሶታል። በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 918 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 49,886 አድርሶታል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 94,820 ደርሷል፡፡
2020-10-29
የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት በኦሮሚያ ክልል የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች 2.3 ሚሊዮን ዶላር ሊሰጥ ነው፡፡   
2020-10-29
በኢትዮጵያ በጡት ካንሰር ከሚያዙ ሴቶች 65 በመቶዎቹ ወደ ጤና ተቋማት የሚሄዱት በሽታው ከተሰራጨ በኋላ  ነው፡፡ ይህም የመዳን ዕድላቸውን እንዲጠብ እያደረገው ነው ተባለ፡፡ ሴቶችን ለህልፈት ከሚያበቁ የካንሰር ዓይነቶች ቀዳሚ መሆኑ የሚነገርለት የጡት ካንሰር፤ በጊዜ ከታወቀና ሕክምና ከተደረገለት ሊድን የሚችል በሽታ ነው ተብሏል፡፡  የኮቪድ 19 ተፅዕኖ እንደ ካንሰር ያሉ ህመሞች አነስተኛ ትኩረት እንዲሰጣቸው እያደረገ ነውም ተብሏል፡፡ ወረርሽኙ የካንሰር ህክምናቸውን የሚከታተሉ ታካሚዎች ወደ ጤና ተቋም ሄደው ህክምናና ክትትል እንዳያደርጉ ጫና እያሳደረ እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረው የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀንን አስመልክቶ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ሲናገሩ፤ ችግሩን ለማስተካከል የጤና ሚኒስቴር የጡር ካንሰር ህክምና እንዲስፋፋ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡ ህክምናው በአሁኑ ሰዓት በ12 የክልል ሆስፒታሎች ሐኪሞችን በማሰልጠን እየተሰጠ ነው የተባለ ሲሆን፤ ለከፍተኛ ህክምና ብቻ ወደ ተጨማሪ ያንብቡ
2020-10-29
ባለፉት 3 ወራት በወረራ የተያዙ 460 ሄክታር መሬት ማስመለሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተናገረ፡፡  የመሬት ወረራ ውስጥ የመንግስሥ ሀላፊዎች ብቻ ሳይሆኑ የተፎካካሪ ፓርቲ ሰዎችም ጭምር ተሳታፊ ሆነው ተገኝተዋል፡፡   
2020-10-29
የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ኢትዮጵያዊያን አንድነታችንን አጠናክረን አገራችንንና ሰላማችንን ልንጠብቅ ይገባል ሲሉ ተናገሩ፡፡
2020-10-29
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አካውንት በማውጣት እንጂ በነባሩ አካውንት የ’online’ ፓስፖርት ለማደስ ክፍያ መፈፀም አይቻልም ተብለናል ለሚለው የደምበኞች ጥያቄ የማንን ምን እንጠይቅልዎ አዘጋጅ ግርማ ፍስሐ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሩን አነጋግሯል፡፡  
2020-10-29
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የሆኑ የጦር ጉዳተኞች የምንኖርበት ግቢ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አይደለም ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ፡፡   
2020-10-29
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሞኑ የታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የተናገሩትን ንግግር ተከትሎ በተለያዩ መድረኮች ውይይቶች እየተካሄዱ ነው፡፡      ንጋቱ ሙሉ አንደኛውን ተመልክቶታል፡፡
2020-10-28
የትምህርት ሚኒስቴር 2 ሰራተኞቼ ጥይት ተተኩሶባቸው ሕይወታቸው አልፏል አለ፡፡ ሁለቱ የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች ሕይወታቸው ያለፈው ለስራ ጉዳይ ወደ አፋር ክልል በሄዱበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡ ሁለቱ ግለሰቦች ሕይወታቸው ያለፈው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ነው ያለው ትምህርት ሚኒስቴር አደጋው መቼ እንደተፈፀመ ያለው ነገር የለም፡፡