ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2021-03-05
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,119 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 7,211 የላብራቶሪ ምርመራ 1,119 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ ባለፋት 24 ሰዓታት የ10 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 2,404 አድርሶታል። በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 228 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 137,431 አድርሶታል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 164,073 ደርሷል፡፡
2021-03-05
ፀሀፊ፣አዘጋጅ፣ተዋናይ፣ገጣሚ አለምፀሐይ ወዳጆ የመኖሪያ ቤት ተሰጣቸው። ለሁለገቧ የጥበብ ሰው አለምፀሀይ ወዳጆ የመኖሪያ አፖርታማ የሰጣቸው የሮዜታ ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ቴዎድሮስ ሽፈራው ናቸው። አርቲስት አለምፀሐይ ወዳጆ በአዲስ አበባ ማረፊያ መኖሪያ ቤት ያልነበራቸው ነገር ግን በአሜሪካ መኖሪያ ቤቷ እንግዶችን፣ስደተኞችን ያስጠጉ እንደነበር ሲነገርላቸው ሰምተናል። ይህን የመሰከሩት አቶ ቴዎድሮስ  ከሚኖሩበት አሜሪካ ሀገራቸው በሚመጡበት ወቅት ሆቴል ያርፉ እንደነበር ሰምተው ቤቱን በስጦታ እነዳበረከቱላቸው ሰምተናል።
2021-03-05
በመጪው ግንቦት ወር መጨረሻ በሚካሄደው ምርጫ የኮቪድ 19 መከላከያ መንገዶችን ያካተተ እንዲሆን በጤና ሚኒስቴር መመሪያ ተዘጋጅቶለታል ተባለ፡፡
2021-03-05
ኢትዮጵያ በ2030 HIVን ሙሉ ለሙሉ የመግታት ውጥን እንዳላት ተናገረ፡፡  ቫይረሱ የሚገታውም በሶስት ዜሮዎች ህግ  እንደሆነ ተነግሯል፡፡  ይህን የሰማነው የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት HIVን ለመከላከል ተቋማትና ክልሎች መከወን ያለባቸውን ስራ ለማስተዋወቅ ባዘጋጀው መድረክ ላይ የጤና ሚኒስቴር የ HIV ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑትን ምርቴ ጌታቸውን አግኝተን ባናገርናቸው ጊዜ ነው፡፡  እርሳቸው እንዳሉት ከሆነ ሚኒስቴሩ ከሚመለከታቸው  መስሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር በ2030 ሶስቱን የዜሮ ህጎች  በመጠቀም ማለትም፤ዜሮ በአዲስ የመያዝ  ምጣኔን በአዲስ ምክንያት የሚከሰት ሞትን ዜሮ በማድግና ዜሮ አድሎና መገለልን ተግባራዊ በማድረግ HIVን ለመግታት ውጥን ተይዟል፡፡  ይህንንም ተግባራዎ ለማድረግ የቫይረሱ ስርጭት በርትቶ በሚታይባቸው አከባቢዎች ከወትሮው በተለየ በጥናት የተደገፈ የመከላከልና ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ይሰራል ብለውናል ፡፡  
2021-03-05
በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት በመጪው እሁድ ወደ ሀገር ቤት ይገባል ተባለ።  የጤና ሚኒስቴር እንደተናገረው የመጀመሪያው ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት በመጪው እሁድ ወደ ሀገር ቤት እንደሚገባ ተናግሯል።  በዓለም የጤና ድርጅት እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጥምረት የተመሰረተው  ኮቫክስ በኩል ክትባቱ ተገኝቷል ተብሏል።  የጤና ሚኒስቴር በ2 ወራት ጊዜ ውስጥ 9 ሚሊየን ዜጎችን ለመከተብ የሚያስችል ክትባት እንደሚረከብ ተናግሯል።  
2021-03-05
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 980 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,557 የላብራቶሪ ምርመራ 980 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ ባለፋት 24 ሰዓታት የ3 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 2,394 አድርሶታል። በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 760 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 137,203 አድርሶታል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 162,954 ደርሷል፡፡  
2021-03-05
በኢትዮጵያ ያለው የኮቪድ 19 ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ፡፡ በዚህም በየዕለቱ በአማካይ ምርመራ ከሚደረግላቸው ዜጎች ውስጥ 13 በመቶዎቹ በቫይረሱ እንደሚያዙ ተነግሯል፡፡ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ዛሬ ረፋድ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ የቫይረሱ ስርጭት በሀገሪቱ አሳሳቢ ከሚባል ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡ እስካለፈው ሳምንት አርብ ድረስ ብቻ በነበሩት 10 ቀናት ከ8000 በላይ ዜጎች በቫይረሱ መያዛቸውንም ሚኒስትሯ አስታውሰዋል፡፡ የህክምና መስጫ ማዕከላት እየሞሉ የመተንፈሻ መሳሪያ እጥረት እየገጠመ በ10 ቀናት ውስጥ ብቻ 123 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ ይህም በቀን በአማካይ 12 ሰው ሕይወቱን እንደሚያጣ ያሳያል ሲሉ ዶ/ር ሊያ ተናግረዋል፡፡ የሀገሪቱ ዕለታዊ የምርመራ መጠን ቢጨምር ኖሮ በቫይረሱ መያዛቸው የሚረጋገጥ ዜጎች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል ተብሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ የኮቪድ 19 ስርጭት 54 በመቶ ደርሷል የተባለ ሲኾን፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ የሥርጭቱ ተጨማሪ ያንብቡ
2021-03-05
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሚወስዱት መካከል ለፈተናው ተዘጋጅተናል ያሉ ብቻ ፈተናውን ይወስዳሉ ተባለ፡፡  በክልሉ ካለው ወቅታዊ ጫና አንፃር በዚህ ዓመት ለመፈተን አልተዘጋጀንም የሚሉ ካሉ በመጭው ዓመት እንዲፈተኑ ይደረጋል መባሉን ሸገር ሰምቷል፡፡
2021-03-05
በትክክል ስልጠና አልሰጡም የተባሉ 4 የአሽከርካሪ ማሰልጠኞችም ተቋማት መዘጋጀታቸው ተነገረ፡፡  ሌሎች 24 ተቋማት ደግሞ ጊዜያዊ እግድ ተጥሎባቸዋል፡፡ 
2021-03-04
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በመጪው ምርጫ አልሳተፍም አለ፡፡