ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ታህሳስ 17፣2012/ የሸገር ስፖርት ወሬዎች- የቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ፡ዎልቭስ ከ ማንችስተር ሲቲ

ዐቢይ ነጥቦች፡
 
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት አንድ ቀሪ ጨዋታ በሞልኒክስ ስታዲየም ዛሬ ምሽት 4፡45 በባለሜዳዎቹ ዎልቭሶች እና ማንችስተር ሲቲ መካከል ይደረጋል።
 
በዎልቭሶች ቤት ምንም ዓይነት አዲስ የተጫዋቾች ጉዳት ወሬ አለመሰማቱ እንደ በጎ ነገር ቢቆጠርላቸውም የአምናው የፕሪምየር ሊግ ባለክብሩን ማንችስተር ሲቲን ማስተናገዳቸውና ከ45 ሰዓታት በኋላ አንፊልድ ላይ ከጠንካራው ሊቨርፑል ጋር የሚጫወቱ መኾናቸው ምናልባት ነገሮች አሰልጣኝ ኑኖ ኤስፕሪቶ ሳንቶስን ቅዠት ውስጥ ሊከታቸው ይችላል።
 
በአንፃሩ ሲቲዎች ባሳለፍነው ሳምንት ሌስተሮችን ማሸነፋቸው የፈጠረላቸውን የመነቃቃት ስሜት የምሽቱን ጨዋታ በማሸነፍ ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል ጋር ያላቸውን ሰፊ የነጥብ ልዩነትን ለማጥበብ ሊጠቀሙበት ይችላሉ የሚሉ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ይገኛሉ።
 
ሲቲዎች ከዚህ ጨዋታ በኋላ እሁድ ምሽት 3፡00 በሜዳቸው ኢትሃድ ከሼፊልድ ጋር ይጫወታሉ።
 
የተጫዋቾች የጉዳት ወሬ፡
 
በባለሜዳዎቹ ዎልቭሶች በኩል ይህ ነው የሚባል አዲስ የተጫዋቾች ጉዳት የለም።
 
በሲቲዎች በኩል የተሰሙት የተጫዋቾቻቸው የጉዳት ወሬዎች ከስፔናዊው ዴቪድ ሲልቫ እና ተከላካዩ ጆን ስቶንስ ጋር የሚገናኙ ናቸው።
 
ሲልቫ የተጎዳው በማንችስተር ደርቢ ጨዋታ ላይ ሲኾን ስቶንስ ደግሞ በጡንቻ መሳሳብ እክል ሳቢያ አራት ጨዋታዎች አልፈውት ነበር።
 
አጥቂው ሰርጂዮ አጉዌሮ ከታፋ ጉዳት መመለሱ ቢያንስ በተጠባባቂ ወንበር ላይ ኾኖ ጨዋታውን ሊያስጀምረው ይችላል።
 
በቡድኑ ወስጥ አንድ መሐል ተከላካዩ አይሜሪክ ላፖርቴ እና ዊንገሩ ሌሮይ ሳኔ ያሉ ተጫዋቾች ለረጅም ጊዜያት ከጨዋታ ዉጪ መኾናቸው ይታወቃል።
 
ዐቢይ ሐብታሙ
ቁልፍ ቃላት
ምላሽ