ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ታህሳስ 20፣2012/ የሸገር ስፖርት ወሬዎች- ዴቬድ ሞይስ የዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኝ ሹመትን አግኝተዋል...ክርስቲያኖ ሮናልዶ የ2019 ግሎብ ሶከር አዋርድ አሸናፊ ሆኗል

ዴቬድ ሞይስ የዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኝ ሹመትን አግኝተዋል።የ55 ዓመቱ ስኮትላንዳዊ ጎልማሳ ሞይስ የዌስትሃም አሰልጣኝነት መንበርን ሲቆናጠጡ ለሁለተኛ ጊዜያቸው ነው።ከዚህ ቀደም 2017 የውድድር ዘመን ማብቂያ ላይ ስላቨን ቢሊችን ተክተው የምስራቅ ለንደንኑን ክለብ በኋላፊነት መረከባቸው ይታወሳል።

ትላንት ምሽት በተሰማ ወሬ በኤቨርተን፣ማንችስተር ዩናይትድ፣ሪያል ሶሴይዳድ እንዲሁም ሰንደርላንድ ክለቦች የሚታወቁት ዴቪድ ሞይስ የማኑዌል ፔሌግሪኒ ስንብትን ተከትለው ክለቡን በኋላፊነት ለዳግም ዙር ተረክበዋል።ክለቡ ቅዳሜ ዕለት በሌስተር ሲቲ 2 ለ 1 መሸነፉ የፔሌግሪኒንን ሰንብት እንዳፋጠነው ተገልጿል።የዌስትሃም ኋላፊዎች ከሽንፈቱ በኋላ በክለቡ ለ18 ወራት የከረሙት ፔለረግሪንን ለመሸኘት ከ2 ሰዓታት በላይ መታገስ እንዳልቻሉ ቢቢሲ ስፖርት ተናግሯል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ የ2019 ግሎብ ሶከር አዋርድ አሸናፊ ሆኗል።ከ2011 ጀምሮ ለዚህ የሽልማት ስነ ስርዓት ቤተኛ ነው የሚባለው ፖርቱቹጋላዊው ኮከብ ሮናልዶ ይህን ክብር ሲጎናፀፍ ለ6ኛ ጊዜያት ሆኗል።ትላንት ዱባይ በተደረገ ደማቅ ስነ ስርዓት ላይ ሽልማቱን ተረክቧል።

ከዚህ ቀደም ሮናልዶ በባሎንዶር ሽልማት የሦስተኛነት ክብርን ማግኘቱ ይታወቃል።ተጫዋቹ ባለፈው የውድድር ዘመን ከክለቡ ጁቬንቱስ ጋር የሴሪ ኤውን ዋንጫ እንዲሁም ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር የኔሽን ሊግ ዋንጫን ማሸነፉ ይታወሳል።
የግላስኮ ደርቢ በሬንጀርሶች የበላይነት ተጠናቋል።ኦልድ ፈርም እየተባለ በሚጠራው የሁለቱ የስኮትላንድ ክለቦች የደርቢ ጨዋታ ሬንጀርስ ሴልቲክን 2 ለ 1 አሸንፏል።በቀድሞ የሊቨርፑል ተጫዋች እንግሊዛዊው ስቴቨን ዤራርድ የሚመሩት ሬንጀርሶች ከ9 ዓመታት በኋላ በሜዳቸው ያሳኩት ድል ሆኖላቸዋል።
አሁን ላይ የስኮትላንድ ሊግን ሴልቲክ በ52 ነጥቦች ሲመራ ሬንጀርሶች በ50 ነጥቦች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።ዐቢይ ሐብታሙ
ቁልፍ ቃላት
ምላሽ