ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ታህሳስ 15፣2012/ የሸገር ስፖርት ወሬዎች- የአር ቢ ሳልዝቡርግ ክለብ ተጫዋች ኢርሊንግ ሃላንድ ቀጣይ ክለብ ታውቋል የሚል የጭምጭምታ ወሬ ከወደ ጣልያን ተሰምቷል

የአር ቢ ሳልዝቡርግ ክለብ ተጫዋች ኢርሊንግ ሃላንድ ቀጣይ ክለብ ታውቋል የሚል የጭምጭምታ ወሬ ከወደ ጣልያን ተሰምቷል።እንደ ማንችስተር ዩናይትድ እና የጀርመኑ አር ቢ ላይፕዚንግ ያሉ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ደግሞ የተጫዋቹ ብርቱ ፈላጊዎች ናቸው።ነገር ግን እንደ ኮሬሪዮ ዴሎ ስፖርት የወሬ ምንጭ ከሆነ ሃላንድን የማስፈረም አሽቅድድም በዩቬንቱሶች አሸናፊነት መጠናቀቁ ተነግሯል።ሃላንድ የሴሪ ኤውን ክለብ የመቀላቀሉ ጉዳይ እውን ከኾነ ዩቬንቱሶች ለዝውውሩ 30 ሚለዮን ዩሮ ወጪ ያደርጋሉ ተብሏል።
የእንግሊዙ ክለብ ኒውካስትል ዩናይትድ ከወደ አሜሪካ የግዢ ጥያቄ ቀርቦለታል መባሉን ስካይ ስፖርት ተናግሯል። እንደ ወሬ ምንጩ መረጃ ከሆነ አሜሪካዊው ዲታ ጆሴፍ ዳግሮሳ ክለቡን ስለመግዛት ላሳዩት ፍላጎት ማረጋገጫ ሰጥተውበታል ተብሏል።የኢንቨስተሩ ዳግሮሳ ክለቡን በባለቤትነት የመጠቅለል ውጥናቸው እውን ይኾን ዘንድ የኒውካስትሉ አለቃ ይኹንታ ያስፈልጋል መባሉን በመረጃው ተጠቅሷል።ዳግሮሳ አሜሪካን ካፒታል ፓርትነርስ በተባለው ኩባንያቸው በኩል ከማግባይሶች ባለቤት ማይክ አሸሊ ጋር ንግግሮች ላይ መኾናቸውን ተናግረዋል።

ዐቢይ ሐብታሙ
ቁልፍ ቃላት
ምላሽ