ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ህዳር 22፣ 2014/ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዘመኑ የደረሰበትን የባንክ ቴክኖሎጂ መጠቀም ጀመርኩ አለ

Image
NIB

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዘመኑ የደረሰበትን የባንክ ቴክኖሎጂ መጠቀም ጀመርኩ አለ፡፡

ባንኩ T 24 R 2020 በመባል የሚጠራውን ቴክኖሎጂ ዘርግቶ መጠቀም መጀመሩን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል፡፡

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ገነነ ሩጋ፣ ባንከቸው ቴክኖሎጂውን ከሌሎች ኢትዮጲያ ውስጥ ካሉ ባንኮች ቀድሞ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

ቴክኖሎጂው የባንኩን ሥራ ቀልጣፋ፣ ዘመናዊ እና ምቹ ለማድረግ በብርቱ ያግዛል ተብሏል፡፡

ባንኩ አዲስ ባቀረብኩት ቴክኖሎጂ የሞባይልና የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎቴን በከፍተኛ ሁኔታ የቀለጠፈና የማያስቸግር ለማድረግ ያስችለኛል ብሏል፡፡

የባንኩ ምክንትል ፕሬዝዳንት እና የአይቲ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አሰፋ ይሻነው ባንኩ ከቀደመው ቴክኖሎጂ ወደ አዲሱ ቴክኖሎጂ ሲሸጋገር ላጋጠሙ ችግሮችና መስተጓጎል ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

በቴክኖሎጂ ልውውጥ ወቅት ባንኮችና ሌሎች የፋይናንስ ቋሞች በቴክኖሎጂ ሽግገር ወቅት የአገልግሎት መስተጓጎል ዓይነት ችግር ያጋጥማችዋል ያሉት አቶ አሰፋ አሁን ግን ቴክኖሎጂው ሙሉ ለሙሉ ስለተዘረጋ ደንበኞቻችን ወደ ባንኩ በመሄድ የቀለጠፈውን አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጠቅላላ የሀብት መጠኔ ከ54 ቢሊየን ብር በላይ ደርሷል ብሏል፡፡

የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 43 ቢሊየን ብር ፣የተከፈለ ካፒታሉ 4.3 ቢሊየን ብር ሆኗል ተብሏል፡፡

የትርፍ መጠኑም 1.6 ቢሊየን ብር እንደደረሰም ሰምተናል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ