ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2021-12-02
በገበያ ውሎዋችን ኮተቤ 02 ገበያ ላይ የአትክልት ዋጋን ተመልክተናል፡፡  
2021-12-01
ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ከነገ ጀምሮ መጠሪያውን ወደ ኦሮሚያ ባንክ እንደሚቀይር ተሰማ። ባንኩ ከእንግዲህ በኋላ “ኦሮሚያ ባንክ’’ ተብሎ እንደሚጠራ ሸገር ከምንጮቹ ሰምቷል፡፡  ባንኩ ለ13 ዓመት የተጠቀምኩበትን የንግድ ምልክት ከዘመኑ ጋር በሚጓዝ መልኩ እቀይራለሁ  ብሏል። የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ተፈሪ መኮንን የባንኩን አዲስ የንግድ ምልክት በነገው ዕለት እናስተዋውቃለን ሲሉ ተናግረዋል።  ተቋማዊ የንግድ ስያሜና መለያውን ለመለወጥ የ20 ወራት ጊዜ እንደፈጀ ፕሬዝዳንቱ ሲናገሩ ሰምተናል።
2021-12-01
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዘመኑ የደረሰበትን የባንክ ቴክኖሎጂ መጠቀም ጀመርኩ አለ፡፡ ባንኩ T 24 R 2020 በመባል የሚጠራውን ቴክኖሎጂ ዘርግቶ መጠቀም መጀመሩን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል፡፡ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ገነነ ሩጋ፣ ባንከቸው ቴክኖሎጂውን ከሌሎች ኢትዮጲያ ውስጥ ካሉ ባንኮች ቀድሞ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ ቴክኖሎጂው የባንኩን ሥራ ቀልጣፋ፣ ዘመናዊ እና ምቹ ለማድረግ በብርቱ ያግዛል ተብሏል፡፡ ባንኩ አዲስ ባቀረብኩት ቴክኖሎጂ የሞባይልና የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎቴን በከፍተኛ ሁኔታ የቀለጠፈና የማያስቸግር ለማድረግ ያስችለኛል ብሏል፡፡ የባንኩ ምክንትል ፕሬዝዳንት እና የአይቲ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አሰፋ ይሻነው ባንኩ ከቀደመው ቴክኖሎጂ ወደ አዲሱ ቴክኖሎጂ ሲሸጋገር ላጋጠሙ ችግሮችና መስተጓጎል ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ በቴክኖሎጂ ልውውጥ ወቅት ባንኮችና ሌሎች የፋይናንስ ቋሞች በቴክኖሎጂ ሽግገር ወቅት የአገልግሎት መስተጓጎል ዓይነት ችግር ያጋጥማችዋል ያሉት አቶ አሰፋ አሁን ግን ቴክኖሎጂው ሙሉ ለሙሉ ተጨማሪ ያንብቡ
2021-11-24
በዛሬው የገበያ ውሎ በየሳምንቱ እሁድ ሻጭና ገዢ እንዲገናኙበት የተጀመረውን ገበያ ይቃኛል፡፡
2021-11-04
በዛሬው የገበያ ውሎ በኤግዚቢሽን ማዕከል ትላንት የተከፈተውን የመሰረታዊ ሸቀጦች ባዛርን ይቃኛል፡፡  
2021-10-22
በዛሬው የገበያ ቅኝታችን ረቡዕና ቅዳሜ እለት ሞቅ ደመቅ የሚለው ጉለሌ አካባቢ የሚገኘውን የሩፋኤል ገበያን እንጎበኛለን፡፡
2021-10-07
በዛሬው የገበያ ቅኝታችን ከዚህ ቀደም በኮተቤ 02 ገበያ ስፍራ ተገኝተን የነገርናችሁ የዋጋ ሁኔታ ምን መስሎ ይሆን ስንል ዳግም ምልከታ አድርገናል፡፡  
2021-09-30
በዛሬው የገበያ ቅኝት መሰናዶዓችን በአዲስ አበባ ከተማ በስፋት እየተለመደ የመጣውን የእሁድ ገበያ እንቃኛለን፡፡  በቀደሙት ዓመታት በአብዛኛው አልባሳት ብቻ ይሸጡባቸው የነበሩት የእሁድ ገበያዎች አሁን አሁን ለገበያ የሚቀርቡት ሸቀጦች በዓይነትም እየሰፉ መኾኑን ሸገር ተመልክቷል፡፡ 
2021-09-23
መሠረታዊ ሸቀጦች ከውጪ ሲገቡም በሀገር ቤት ሲመረቱም ከቀረጥና ታክስ ነፃ ናቸው ተብሎ ከሳምንታት በፊት ተነግሮ ነበር፡፡ ይህ የመንግስት ውሳኔ በገበያው ላይ ምን ለውጥ አመጣ?
2021-09-09
የደብተር፣ የቦርሳ፣ የምሳ ዕቃው  ገበያ እንዴት እየሆነ ነው፡፡