ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2020-07-20
በሸገር ልዩ ወሬ ቀርበው የነበሩት በአሳዛኝ ሁኔታ በቅጠል ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩት እማማ አያንቱ እና እጇ አልታዘዝ ብሏት ከነልጇ ጎዳና የወደቀችው የቀድሞዋ ፖሊስ አባል መዓዛ እነሆ ዛሬ የሞቀ ቤት ባለቤት ሆነዋል፡፡ የወንድሙ ኃይሉን ሙሉውን ዝግጅት ያዳምጡ
2020-06-23
በአዲስ አበባ፣ ቦሌ ሚካዔል አካባቢ፣ ግብርና ሰፈር ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ውዳሴ የዓይን ብርሃናቸውን ያጡት ቀስ በቀስ ነበር፡፡ ባለቤታቸው የዓይን ብርሃናቸው እንዲመለስ በርካታ የሕክምና ተቋማት ወስደዋቸው ነበር አልተሳካም እንጂ፡፡ ከዚህ በኋላ በቀጠሉት ዓመታት ሁለት ልጆችን አከታትለው ሲወልዱ የባሰው መጣ - ሁለቱም ልጆች የዓይን ብርሃናቸውን አጥተው ነው የተወለዱት፡፡ ቤተሰቡን ይደግፉ የነበሩት አባወራ ለንግድ ሥራ በሄዱበት በቢጫ ወባ ሕመም ሲሞቱ ወይዘሮዋ ሰማይ ተደፋባቸው፡፡ ልጆቹን ይዘው ጎዳና ወጡ፡፡ ኋላ ላይ በበጎ ሰዎች ርብርብ እንደምንም የቀበሌ ቤት አግኝተው በሰዎች እርዳታ ኑሮን ይገፉ ጀመር፡፡ አሁን የመጀመሪያ ልጃቸው 26 ዓመቱ ነው፤ ሁለተኛው እና የኦቲዝም ተጠቂው ደግሞ 22 ዓመቱ ነው፡፡ ይህ የኮሮና ወረርሽኝ ሲመጣ ደግሞ ለዓይነ ሥውር እናት እና ልጆቹ ጊዜውን የከፋ አድርጎባቸዋል ይለናል የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ…ሙሉ ታሪካቸውን ያዳምጡ…
2020-05-27
እማማ አያንቱ ደበላ ክረምትን አይወዱትም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የሚሸጡትን ቅጠል ስለሚያበሰብስባቸው ብቻ አይደለም፡፡ በቅጠል እና በተበጣጠሰ ላስቲክ እንደነገሩ የተወታተፈችው ጎጇቸው ክረምት ሲመጣ ከላይ በዝናብ ከሥር በጎርፍ ውሃ ትሞላለች፡፡ እድሜዬን አላውቀውም የሚሉት እማማ አያንቱ ደበላ፣ ገና ድሮ ነው ከሜጫ ወደ አዲስ አበባ የመጡት፡፡  ትዳርም ሆነ ልጅ የላቸውም፡፡ ለበርካታ ዓመታት የሰው ቤት ሰራተኛ ሆነው ከኖሩ በኋላ ይህቺን ጎጆ ራሳቸው ሰርተው ቅጠል ሸጠው መኖር ጀመሩ… እነሆ ቅጠል ሲሸጡ ብዙ ዓመታት ሆናቸው፡፡ ሁሌ ክረምት ሲመጣ ግን ሐሳብ ይገባቸዋል ይለናል እማማ አያንቱን ያነጋገራቸው የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ፡፡ ከእጅ ወደ አፍ የሆነው የእማማ አያንቱ ኑሮ የሚደጎመው በሰፈሩ ልጆች እርዳታ ነው፡፡ የክረምቱ መግቢያ ነውና፣ በቅጠል ጣራ በቅጠል እንጀራ የሚኖሩት እማማ አያንቱ ከሰሞኑም ዝናብ በባሳ የመጪው ክረምት ዶፍ ነው የሚያሳስባቸው፡፡ ሙሉውን ያዳምጡ…
2020-05-19
ከመጀመሪያዎቹ የበረራ አስተናጋጆች አንዷ የነበሩት የ79 ዓመቷ ወ/ሮ አልማዝ ሰይፉን እናስተዋውቃችሁ…አሁን መኖሪያቸውን ሰራተኛ ሰፈር ያደረጉት ወ/ሮ አልማዝን የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ አነጋግሯቸዋል…
2020-05-09
ከኮሮና በፊት ለሰዎች ልብስ እያጠበች በምታገኘው ገንዘብ በ800 ብር ቤት ተከራይታ ነበር የምትኖረው፡፡ ኮሮና ሲመጣ እና ሰዎች ቤት መዋል ሲጀምሩ ልብሱን እኛው እናጥበዋለን ብለው ሲያሰናብቷት ገቢዋ ነጠፈ፡፡ ለኪራይ የምትከፍለው የለምና የተከራየችውን ቤት ለመልቀቅ ተገደደች፡፡ ባጠራቀመችው 2 000 ብርም ጎዳና ዳር የቆርቆሮ ቤት ሰርታ ነው የምትኖረው፡፡ የሰፈር ሰው የቻለውን ያህል ይረዳታል…ወንድሙ ኃይሉ አነጋግሯታል… Image
2020-05-04
እኛ ይቅር ካልተባባልን ይህ የመጣብን ወረርሽኝ አይተወንም ብለው በየመንደሩ እየዞሩ 80 ጠበኞችን ያስታረቁት እናቶች ታሪክ…ኮሮና ይጠፋልን ዘንድ ፀሎት ያሻል፤ ቂም ይዞ ፀሎት ደግሞ ዋጋ ቢስ ነው በሚል በየመንደሩ እየዞሩ እስከ 30 ዓመታት ያህል ተጣልተው የኖሩትን ያስታረቁትን እናቶች የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ አነጋግሯል፡፡ እድሜያቸው ከ60 እስከ 80 የሚሆኑት እኒህ የቀጨኔ አካባቢ እናቶች ድንጋይ ተሸክመውም፣ ተንበርክከውም፣ እግር ላይ ወድቀውም እስካሁን 80 ያህል ጠበኞችን አስታርቀዋል፡፡ማስታረቃቸውንም ቀጥለዋል፡፡ለእርቁ አመንትተው ቀጠሮ ለሚሰጧቸውም እናቶቹ የሚሰጡት መልስ አላቸው፣ “ቀን የማይሰጥ ሞት ነው እኮ የመጣብን !!!”በዚህ ሰበብ ለመታረቅ የበቁትም ምስጋናቸው ወደር የለውም…   Image
2020-04-18
በዊልቸሯ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰች አካል ጉዳተኞችን ከኮሮና ተጠበቁ የምትለውን ዘነበች ጌታነህን እናስተዋውቃችሁ፡፡ Image
2020-04-07
በሸገር ልዩ ወሬ ከዚህ ቀደም የቀረበችው፣ በልጇ የተለየ አፈጣጠር ሳቢያ የሰዉን አፍ ፍራቻ ለረጅም ጊዜ በቤት ተወስና የኖረችው ለምለም ታሪኳን የሰሙ ብዙዎች የተለያዩ ድጋፎች አድርገውላት ምስጋናውን አቅርባለች…አሁን ከቤት በመውጫ ጊዜዬ ግን ከቤት የማያስወጣው ኮሮና መጣ የምትለው ለምለም፣ በቤት ተወስኖ መቀመጡን ከማንም በላይ ታውቀዋለችና ስለዚሁ ያላትን መልዕክት ለሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ ነግራዋለች… Image
2020-03-31
ተወልዶ ካደገባት ወልዲያ በተማረው የቤተ ክህነት ትምህርት ሊያገለግል ወደ አዲስ አበባ የመጣው ዮሐንስ ፍፁም ያሰበው አልሳካልህ ቢለው ተስጥኦውን ተጠቅሞ የጎዳና ዳር ሰዓሊ ወጣው…ጎዳና ላይ ሲስል ሰዉ መሰብሰቡ ያላስደሰታቸው ፀጥታ አስከባሪዎች ከአንዱ የአዲስ አበባ አካባቢ ወደ ሌላው ሲያባርሩት ከርመው የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ ሲያገኘው አራት ኪሎ ደርሷል፡፡ አሁን ደግሞ ሌላ ባላንጣ መጥቶብኛል ይላል ዮሐንስ - ኮሮና፡፡ በዚህ ወረርሽኝ ሳቢያ ሰዉም መምጣት አቆመ - የስዕል ሽያጭ ገቢውም ቀነሰ…እሱ ግን እጅ አልሰጠም - እዛው ጎዳና ላይ የኮሮናን ስዕል እየሳለ አላፊ አግዳሚውን ያስጠነቅቃል…ሙሉውን ያዳምጡ…
2020-03-17
አባይ ሙሉ ይባላል፡፡ በአውቶብሶች ውስጥ አስፈቅዶ እየገባ ተሳፋሪዎቹን ጠይቆ ሲፈቀድለት ስለኢትዮጵያዊነት፣ ስለበጎነት ይሰብካል፡፡መልዕክትህን ለማስተላለፍ አውቶብሶችን ለምን መረጥክ ሲል የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ ጠይቆት ነበር…“አውቶብስ ማለት ሐገር ነው” ነው የአባይ ሙሉ መልስ…ሙሉውን ያዳምጡ