ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2021-12-04
በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለው ግንኙነት ፍፁም የጠላትነት ነው፡፡ በኢራን የኒኩሊየር መርሃ ግብር ጉዳይ የሁለቱ አገሮች የእርስ በርስ መዛዛት ጣራ እየነካ ነው፡፡  ዛቸው ወዴት ያመራ ይሆን?   
2021-12-03
የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ምክትል መሪ ሌተና ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳግሎ አውሮፓ እና አሜሪካ መንግሥታችንን ከመደገፍ ውጭ አማራጭ የላቸውም አሉ፡፡ ዳግሎ አውሮፓ እና አሜሪካ በሱዳን ሊፈጠር የሚችለውን የስደተኞች ቀውስ ለማስወገድ የሱዳንን ወታደራዊ መንግስት ሊደግፉ እና ሊያግዙ ይገባል ሲሉ መናገራቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡ ካለበለዛ በተለይ አውሮፓ በሱዳን ስደተኞች ልትጥለቀለቅ ትችላለች ሲሉ ማስፈራራታቸው ተሰምቷል፡፡ የሱዳን የጦር አለቆች ከወር በፊት ዳግም የመንግሥት ግልበጣ ካደረጉ በኋላ ከየአቅጣጫው ጫና በርትቶባቸዋል፡፡ በአገር ውስጥም ተቃውሞው አይሎባቸዋል፡፡ የጦር አለቆቹ አብደላ ሐምዶክን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ቢመልሷቸውም የአገሪቱ ፖለቲካ ቀውስ እየተባባሰ መምጣቱ ይነገራል፡፡ የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሱዳንን ጊዜያዊ መንግስት እንዲደግፍ መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡ በሱዳን ዳግም ወታደራዊ የመንግስት ግልበጣ ከተደረገ ወዲህ አገሪቱ ከአፍሪካ ተጨማሪ ያንብቡ
2021-12-03
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አውሮፓ ወደ ከፋ ወታደራዊ ግጭት እያመራች ነው ሲሉ አስጠነቀቁ፡፡ የላብሮቭ አስተያየት የተሰማው የአውሮፓ የፀጥታ ነክ ጉባኤ በስዊድን እየተካሄደ ባለበት ወቅት እንደሆነ ስቶክ ኦን ትሬንት በድረ ገፁ ፅፏል፡፡ በሩሲያ እና በሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) መካከል ወታደራዊ ፍጥጫው እየተባባሰ መምጣቱ ተነግሯል፡፡ ምዕራባዊያን ሩሲያ ዩክሬይንን ለመውረር በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ወሰን ላይ አስፍራለች ሲሉ እየከሰሷት ነው፡፡ ሞስኮ በተደጋጋሚ እያስተባበለች ነው፡፡ አሜሪካ የመካከለኛ ርቀት ተወንጫፊ ሚሳየሎችን ወደ አውሮፓ መላኳ ፍጥጫውን እያባባሰው መምጣቱ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ የላቭሮቭም ማስጠንቀቂያ የተሰማው በዚሁ ምክንያት መሆኑ ታውቋል፡፡ ጊዜው የቀዝቃዛው ጦርነትን ዘመን እያስታወሰ ነው፡፡
2021-12-03
በጀርመን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ያልተከተቡ ሰዎች በርካታ ገደቦች ሊጣሉባቸው ነው፡፡ ባልተከተቡት ሰዎች ላይ ገደቦቹ እንዲጣሉባቸው መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል እና የግዛት አስተዳዳሪዎች እንደተስማሙበት ደችላንድ ኒውስ ፅፏል፡፡ የኮሮና ቫይረስ መከላከያውን ያልተከተቡት እንደ ቡና ቤት እና ሬስቶራንቶች ባሉ ተቋማት እንዳይገለገሉ ይደረጋል መባሉ ተሰምቷል፡፡ በሌሎችም ሕዝብ በሚበዛባቸው ሥነ-ሥርዓቶች አይገኙም ተብሏል፡፡ ባልተከተቡት ዜጎች ላይ ገደብ የሚጣልባቸው አገሪቱ ወደ ወረርሽኙ 4ኛው ማዕበል በገባችበት ወቅት መሆኑ ታውቋል፡፡ በብዙ የአውሮፓ አገሮችየኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዳግም እየተባባሰ መምጣቱ ይነገራል፡፡ በጀርመን ከመጪው የካቲት ወር አንስቶ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መከተብ አስገዳጅ እንደሚሆን በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
2021-12-01
ጃፓን በአዲሱ የኦሚክሮን የኮሮና ቫይረስ ልውጥ ዝርያ ምክንያት ማንኛውም የውጭ አገር መንገደኛ እንዳይመጣባት አገደች፡፡ እገዳው ለመጪው 1 ወር እንደሚዘልቅ ጃፓን ታይምስ ፅፏል፡፡ ስለ አዲሱ ልውጥ ዝርያ ከሚታወቀው የማይታወቀው እንደሚያመዝን ሲነገር ሰንብቷል፡፡ ከፍተኛ የጤና ሊቃውንት ሳይቀር በኦሚክሮን ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ የተነሳ ስጋት ገብቶናል እያሉ ነው፡፡ ጃፓን የውጭ አገራት ሰዎቸ እንዳይመጡባት የእገዳ እርምጃዋን ሥራ ላይ ከመዋልዋ አስቀድሞ በኮሮና የኦሚክሮን ልውጥ ዝርያ የተያዘ ናሚቢያዊ የአውሮፕላን ተጓዥ መገኘቱ ተሰምቷል፡፡ አብረውት የመጡ 70 ያህል መንደኞችም ለ10 ቀናት በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ይሰነብታሉ ተብሏል፡፡
2021-12-01
የሌሶቶው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማስ ታባኔ በነፍስ ግድያ ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ታባኔ ክስ የተመሰረተባቸው የቀድሞ ባለቤታቸው ሊፖሊላ ታባኔ ላይ በተፈፀመ ግድያ እንደሆነ ኒውስ 24 ፅፏል፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የአሁኗ ባለቤትም በዚሁ ግድያ አብረው መከሰሳቸው ተሰምቷል፡፡ ሊፖሊላ ከጥቂት ዓመታት በፊት ተተኩሶባቸው የተገደሉት መኖሪያ ቤታቸው አጠገብ መኪና ውስጥ እንዳሉ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡ በሴትዮዋ ላይ የተፈፀመው ግድያ በመላ አገሪቱ ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረ ነበር ተብሏል፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአሁኗ ባለቤታቸው በፍርድ ቤት እንደተገኙ ክሱ በንባብ መሰማቱ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ ሁለቱም ወንጀሉን አልፈፀምንም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
2021-12-01
ትንታኔ ወደ ዴሞክራሲያዊ የሲቪል አስተዳደር የመሸጋገር ህልማቸው በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት የተስተጓጎለባቸው ሱዳናውያን፣ ‹‹የሲቪል አሥተዳደር ወደ ቦታው ይመለስ›› በሚል ሕዝባዊ የተቃውሞ አመጽ እየበረቱ ነው፡፡  የራሱን ቤት ከማጽዳት ይልቅ በማወክ የተጠመደው የጄነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን መንግሥት ግን፣ ከቤቱ አልፎ ጎረቤት ኢትዮጵያን ለማወክ እየተጋ ይገኛል፡፡ 
2021-11-30
የካሪቢያኗ አገር ባርባዶስ ሪፖብሊክ ሆነች፡፡ አገሪቱ የብሪታንያዋን ንግሥት ኤልሳቤት ዳግማዊት ርዕሰ ብሔርነት ከእንግዲህ በቃኝ ማለቷን ዘ ጋርዲያን ፅፏል፡፡ ንግስቲቱም ለባርባዶሳውያን በሪፖብሊክነት ሁሉም መልካም ይሁንላችሁ ሲሉ የመልካም ምኞት መልዕክት መላካቸው ታውቋል፡፡ ባርባዶስ ለ400 ዓመታት ያህል በብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ሥር ቆይታለች፡፡ ከብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ከተላቀቀች 55 ዓመታት ሆኗታል፡፡ ያም ሆኖ አገሪቱ የብሪታንያዋን ንግስት ኤልሳቤት ዳግማዊትን ርዕሰ ብሔሯ አድርጋ መቆየቷን መረጃው አስታውሷል፡፡
2021-11-30
ማቅዳሊና አንደርሰን ዳግም የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ተመረጡ፡፡ ማግዳሊና ባለፈው ሳምንት በፓርላማው ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ከተመረጡ በኋላ ሥልጣን የለቀቁት ከሰዓታት በኋላ ነበር፡፡ ማቅዳሊና ባለፈው ሳምንት በተሾሙ በሰዓታት ልዩነት ሥልጣን የለቀቁት ጥምረታቸው ሥንጥቃት ስላጋጠመው እንደነበር RTE የመረጃ ምንጭ አስታውሷል፡፡ ማቅዳሊና አንደርሰን ትናንት በድጋሚ በአገሪቱ ፓርላማ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን መመረጣቸው ተሰምቷል፡፡ ሴትዮዋ ከሶሻል ዴሞክራቶቹ የፖለቲካ ማህበር ወገን ናቸው፡፡ በሲውዲን ታሪክም የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን በቅተዋል፡፡ መንግሥታቸው የባለ አደራነት ሚና እንደሚኖረው ታውቋል፡፡ በአገሪቱ በመጪው መስከረም ወር ምርጫ ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
2021-11-30
የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂን ፒንግ ለአፍሪካ ተጨማሪ 1 ቢሊዮን ዶዝ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባቶችን እንሰጣለን አሉ፡፡ ቻይና ለአፍሪካ ከምትለግሳቸው ክትባቶች 600 ሚሊዮኑ በቀጥታ የሚላክ እንደሆነ ሺ ጂን ፒንግ መናገራቸውን ሺንዋ ፅፏል፡፡ የተቀረው እንደ ኮቫክስ ባሉ አካላት አማካይነት የሚለገስ መሆኑ ታውቋል፡፡ እስካሁን ቻይና ለአፍሪካ 180 ሚሊዮን ዶዝ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባቶችን እንደለገሰች መረጃው አስታውሷል፡፡ በአፍሪካ እስካሁን በአጠቃላይ መከላከያውን የተከተቡት መከተብ ካለባቸው ከ7 በመቶ ያልበለጡት ናቸው ተብሏል፡፡ በኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ረገድ አፍሪካ ከብዙዎቹ የአለም ክፍሎች ደከም ብላ ትገኛለች፡፡ የቻይና መንግሥት ክትባቱን በአፍሪካ በበቂ ሁኔታ ለማዳረስ የአገሪቱ ኩባንያዎች በመጪዎቹ 3 ዓመታት በአህጉሪቱ 10 ቢሊዮን ዶላር ሥራ ላይ እንዲያውሉ እያበረታታቸው ነው ተብሏል፡፡