ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2021-12-04
መሠረታዊ የሚባሉና ዜጎችን የሚጠቅሙ የጤና መረጃዎች በነፃ የሚቀርቡበት ማዕከል ዛሬ ሥራ መጀመሩ ተነገረ፡፡  በማዕከሉ የህክምና ምክር እንዲሁም ሌሎችም አገልግሎቶች ይሰጣሉ ተብሏል፡፡ 
2021-12-04
መሠረታዊ የሚባሉና ዜጎችን የሚጠቅሙ የጤና መረጃዎች በነፃ የሚቀርቡበት ማዕከል ዛሬ ሥራ መጀመሩ ተነገረ፡፡  በማዕከሉ የህክምና ምክር እንዲሁም ሌሎችም አገልግሎቶች ይሰጣሉ ተብሏል፡፡ 
2021-12-04
ሕወሃት በአፋር ክልል የተፈፀመው ወረራ ባደረሰው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ሳቢያ በክልሉ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ ለጉዳት ተጋልጧል ተባለ፡፡ ቡድኑ በአፋር ክልል 21 ወረዳዎች ላይ ባደረሰው ጥቃት ከ360,000 በላይ ዜጎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውም ተነግሯል፡፡ ጉዳት በደረሰባቸው በእዚሁ ወረዳዎች የሚገኙ እንደ ትምህርት ቤትና ሆስፒታል ያሉ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ሙሉ በሙሉ መውደማቸው የተነገረ ሲሆን ዜጎች በከፍተኛ ችግር ውስጥ ናቸው ተብሏል፡፡ ይህን የሰማነው በአፋር ክልል በጦርነቱ ምክንያት ለደረሰው ጉዳት ድጋፍ ለማሰባሰብ በአዲስ አበባ የተቋቋመው ግብረ ሀይል መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው፡፡ የአፋር ልማት ማህበር ከአፋር ተወላጆችና ወዳጆች ጋር በመሆን ያቋቋመው ግብረ ሀይል በህወሃት ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉት ዜጎች፤ ቡድኑን ለመፋለም ለዘመቱትና ለቤተሰቦቻቸው ድጋፍ ለማሰባሰብ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግሯል፡፡ የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዘሀራ ዑመድ የአፋር ህዝብ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት እየከፈለ ላለው ተጨማሪ ያንብቡ
2021-12-04
ኢትዮጵያ በህግ አውጪ አካሏ ሽብርተኛ ብላ የፈረጀችውን ሕወሃት መዋጋት ከጀመረች 1 ዓመት አልፏታል፡፡ ጦርነቱ፣ ውጊያው የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ቀልብ ሊባል በሚችል መልኩ ቀልብ ወጥሮ የያዘ ነው፤ የታዳጊዎችንም ጭምር፡፡ ታዳጊዎች የጦር ሜዳ ውሎዎችን ሲመለከቱ፤ ምን ይሰማቸዋል?  ሲሰሙ አስተሳሰባቸው ላይስ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ይኖረው ይሆን?   

ኢትዮጵያ በዓለም ፊት በሎጀስቲክስ ጉዳዮች ተሰሚነቷን ከፍ የሚያደርግ አጋጣሚ ተፈጥሮላታል፡፡ አውሮፓዊያን ብቻ ሲዘውሩት የነበረውን ከ40000 በላይ የእቃ አስተላላፊ ድርጅቶችና የሎጀስቲክስ ኩባንያዎች የተወከሉበትን ኢንዱስትሪ እንዲመሩ ሁለት ኢትዮጵያዊያን  ተመርጠዋል፡፡
2021-12-04
ኢትዮጵያ በዓለም ፊት በሎጀስቲክስ ጉዳዮች ተሰሚነቷን ከፍ የሚያደርግ አጋጣሚ ተፈጥሮላታል፡፡ አውሮፓዊያን ብቻ ሲዘውሩት የነበረውን ከ40000 በላይ የእቃ አስተላላፊ ድርጅቶችና የሎጀስቲክስ ኩባንያዎች የተወከሉበትን ኢንዱስትሪ እንዲመሩ ሁለት ኢትዮጵያዊያን  ተመርጠዋል፡፡
2021-12-04
ሰሞኑን በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው የአፍሪካ ቻይና የጋራ ሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ቤጂንግ ከታሪፍ ነፃ የአፍሪካ የግብርና ምርቶችን ወደ ሀገሯ ለማስገባት የሚያስችላትን ፕሮግራም አስተዋውቃለች፡፡ ከአሜሪካ የአጎአ እድል ለወጣችው ኢትዮጵያ ይህ የቻይና ፕሮግራም ምን ያመጣላታል? አጎአን መተኪያስ ይሆናታል?   

ኢትዮጵያ የሀገር አንድነቷን ለማፅናት ዘመቻ ላይ ባለችበት በዚህ ወቅት የረጅም ዓመታት ወዳጆቿ አሜሪካና ምዕራባዊያን ፊታቸውን ካዙሩባት ዋል አደር ብለዋል፡፡ ዋሽንግተንና በእርሷ ሳምባ የሚተነፍሱ የሚመስሉት ምዕራባዊያን ኢትዮጵያን በዚህ በፈተናዋ ወቅት ፊታቸውን ቢያዞሩባትም እንደ ቻይና፣ ህንድ፣ ሩሲያ ያሉ ሀገራት ግን አለሁልሽ እያሏት ነው፡፡ ሰሞኑንም የቻይናው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ደርሰው ተመልሰዋል፡፡ እነ አሜሪካ ዜጎቻቸውን ውጡ እያሉ በሚወተውቱበት በዚህ ወቅት የቻይናው ሚኒስትር አዲስ አበባ መምጣት ምን አንደምታ አለው?