ማስታወቂያ

programs top mid size ad

የውስኪ ቤቶቹ ደጃፍ

ከጠጡ አይንዱ ለጆሮአችን አዲስ ያልሆነ የተለመደ ቀን ከማታ የምንስማው በየቦታው ተፅፎ የምናነበው ሀሳብ ... ከጠጡ አይንዱ እኔም ይኼን ሀሳብ እጋራለው ጠጥቶ ማሽከርከር ለአደጋ ያጋልጣል፤ ንብረት ያወድማል ህይወት ይቀጥፋል ልላችሁ አይደለም ግልፅ ነው አዎ የከፋ ነው! ግን በከተማችን የሚገኙ መጠጥ ቤቶች በቦሌ፣ ደጃች ውቤ፣ በካዛንቺስ፣ በፒያሳ እና በሌሎችም .... ቦታዎችን ያልገለፅኳቸው አካባቢዎች የሚገኙ የተጠመቀ ቢራ ሻጮች እና ውስኪ ቤቶች በደጃፋቸው ላይ ከንጉሱ ኒሻን እንደሚረከብ ባለማዕረግ የተደረደሩ እና የተኮለኮሎ መኪኖችን ማየቱ እንግዳ አይደለም፡፡ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ደግሞ የመኪናቸውን ሁለት እግር ጐማ በእግረኛ መረማመጃ ላይ፤ የቀረውን የኋላ እግር ጐማ ወይም ግማሹን የመኪና አካል ደግሞ ከዋናው መንገድ ላይ አኑረው ትክክል ባልሆነ የመኪና አቋቋም በመሬቷ ይፋቀሩባታል፡፡ ሲላቸውም የእግረኛውን መንገድ ሙሉ በሙሉ የመኪና ማቆሚያ አድርጐ፤ በመውሰድ ይዘጉታል ወይም መኪናቸውን ፓርክ ያደርጉታል፡፡ በመቀጠልም የእግረኛውን መንገድ ከፊልም ይሁን በሙሉ ይዘጉታል፡፡

አንዳንዶች ደግሞ በስርዓት ተደርድረው የመጠጡ ብዛት እና አይነት ወደሚገኝበት የመጠጡ ድግስ ወደ ተደገሰበት ቤት ጐራ ይላሉ፡፡ የተቀሩት ደግሞ በውጪ መስተንግዶ ወይም Out door Service በሚል መስተንግዶ የፈለጉት አይነት እና የመረጡት የመጠጥ አይነት መኪናቸውን ወዳቆሙበት ቦታ ከመጠጥ ቤቱ ፊት ለፊት ወይም አካባቢ ከመኪናቸው ሳይወርዱ ይመጣላቸዋል፤ ጐሽ እየተባሉም ይስተናገዳሉ፤ መጠጥ ከመጐንጮታቸው በፊት የእግረኛውን መንገድ ዘግተው እግረኛውን ያጉላላሉ እግረኛው ከቻለ ባለመኪናዎቹ ጠጪዎች ይቻላል ብለው የእግረኛው መንገድ ላይ ገባ ብለው በመቆም ባስቀሯት መረማመጃ ላይ እየተጣበበ እና ከመኪናው የፊት አካል ጋር እየተሻሸ አያጉረመረመ ያልፋል፡፡ የተዘጋበት ደግሞ በዋናው መንገድ ለመሄድ ይገደዳል አስቡት ክፉቱን ዝርዝር አያስፈልገውም፤ በተመሳሳዩ አይነስውሮችን አስቧቸው መንገዱ የተዘጋባቸው መንገድ ተዘግቶባቸው ከቆሙ መኪና ጋር ሲጋጩ እና ሲላተሙ ... ሃሎ በዛ ሂዱ በዚ ሂዱ ተብለው በተወናበደ ሃሳቦች ይተራመሳሉ ይሄ እንግዳ መኪናቸውን አስነስተው ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ያለው ችግር ነው አስቡት እስካሁን እየጠጡ ነው፡፡

መጠጥ ጠጥተው ምን ሊሆኑ ይችላሉ የሚለው በማሰብ ጊዜ ማባከን አያስፈልግም በተመሳሳዩ ከቢራ ቤቱ ወይም ከውስኪ ቤቶቹ ፊት ለፊት ህጉ በሚፈቅድላቸው መንገድ የተኮለኮሉ መኪኖች ምን እየሰሩ ነው? አመታዊ ምርመራ?ነዳጅ ሊቀዱ? ምን ሊሰሩ እየጠጡ ወይስ እያስጠጡ ትኩረትስ መደረግ ያለበት የቱ ጋ ነው?

ሁሉንም ባይባልም አንዳንድ ትራፊኮች ትኩረታቸው የእግረኛ መንገድ ዘጋክ፣ ደርበህ ቆምክ፣ ዜብራ ላይ አቁመካል ብሎ ታርጋ ከመፍታት እና ከመክሰስ ባሻገር ለምን መኪና ውስጥ ትጠጣለህ ብሎ ሲያነጋግር አይስተዋልም ባለመኪናውም እየተንገዳገደ መጥቶ መኪናውን ለመንዳት ሲኮረኩር ከአስከባሪው ጋር ሲነጋገር አይታይም ትኩረት መደረግ ያለበት መቼ ነው? ጠጥቶ ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡

አዎ የተከለከለሰ ነው.... ጠጪዎችም መኪናችሁ ውስጥ እንደፋሽን እና ዘመናዊነት ተረድታችሁ ሃይ ባይ ሳትሹ ክፋቱን ብታስቡት ቤተሰብ አስተዳደሪነታችሁን ልብ ብትሉት ከሁሉ ደግሞ ከፈቃዳችሁ አልፋችሁ የሌላውን ህይወት ጥያቄ ውስጥ እንዳታስገቡት አካሉን እንዳትጐዱት ንብረት እንዳታወድሙ ብትባንኑ መልካም ነው፤ አንዳንዶች ደግሞ እኔ ስጠጣ ጠንቃቃ እሆናለው የመንዳት ብቃቴም ይጨምራል የምትሉ ከ365 ቀን ውስጥ አንዱን ብትስቱ መልሳችሁ የምታስቡበት ጊዜ የላችሁም እና እናንተም ብትባንኑ፤ ጠጥቶ የሚያሽከረክሩ ሰዎችን የሚያጋልጥ መሳሪያ አልኮል ቴስተር ትራፊኮቻችን ከሚናፍቁ መኪናቸው ውስጥ ቦትል አውርደው ሲገባበዙ ቢራ እየቀዱ ጠጪ ጠጣ ጠጡ ሲባባሉ ከመመልከት እና ችርስ እየተባባሉ የሚያጋጩትን የብርጭቆ ድምፅ ከመስማት የተሻለ መፈተሻ ባይናፍቁ እነሱም ቢባንኑ እየደረሰ ያለውን አደጋ ለመቀነስ ይረዳል፡፡

ትራፊኮችስ ምነው ጠጥተው የሚያሸከረክሩ ሰዎች ባደረሱት አደጋ አጥፍተሀል አጥፍተሻል ብሎ ጐዳናውን ከመለካት እና አስፋልቱን ከማስመር በፊት ዜብራ ላይ ቆመሀል ደርበህ አቁመሀል ከማለት ውጪ ልጠጣ ገብተሀል ባይሉ እንኳን እየጠጣህ ነው ብለው ቢሟገቱ መኪናቸውን አቁመው ሊጠጡ እንደሚገቡ እየታወቀ አሽከርካሪዎችንስ ልብ ቢሉ አደጋው ፋታ የሚያገኝ ይመስላል ከጠጡ አይንዱ ግዴታ ወይስ ምክር?
 
ቁልፍ ቃላት
Wed, 08/06/2014 - 20:01