ማስታወቂያ

programs top mid size ad

እንተላለፍ

እንተላለፍ
ሚኒባስ ታክሲ ውስጥ ነኝ ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ እየሄደኩኝ፡፤ ታክሲው በአዲሱ ገበያ አድርጐ መድረሻው አስኮ ነው፡፡ ረዳቱ ደምስሩ እስኪግተረተር ይጠራል፡፡በአዲሱ ገበያ በቀለበት አስኮ እያለ፡፡ ሹፌሩም አንገቱን ወጣ አድርጐ ከጐኑ መጥተው ከሚቆሙ ሌሎች ታክሲዎች ውስጥ በቀለበት አስኮ አዲሱ ገበያም ይቻላል እያለ ይጠራል አንድ ሰው ሲገባለት ‹‹ እ የታለህ እኔ ወርጄ ልጥራ እንዴ›› ብሎ በረዳቱ ላይ ይጮሀል በመጨረሻ ሞላና ጉዞ ተጀመረ፡፡ ታክሲው መሙላቱን ያላወቀው ሹፌር እያሽከረከረ አንገቱን ወጣ አድርጐ በቀለበት አስኮ ይላል ረዳቱ ‹‹ፍሬንድ ሞላኮ ለማን ነው የምትጠረው›› አለው፡፡ አትናገርም አለ ሹፌር አንተ በስፖኪዬ አታይም ረዳት መለሠ፡፡ በእንዲህ መልኩ የጀመረው አለማግባባት ወደለየለት ፀብ ተቀየረ፡፡ 
ሹፌር አንድ ይላል ረዳት ሌላ ይመልሳል፡፡ ብቻ በደቂቃዎች ውስጥ በሚኒባሱ ውስጥ ያለው ተጓዥ ስለሁለቱም ኑሮ፣ ቤተሠብ፣ የገቢ ደረጃ ሁሉንም ሠማ፡፡ ከዛ በስንት ማባበል አስኮ ከደረሱ በኋላ ረዳት ገቢ አስረከክቦ ሊሊያዩ ተስማምተው እኛን ያሠብንበት አደረሱን፡፡
ሁለተኛ ታክሲ መያዝ ነበረብኝ ወደ ሌላኛው ታክሲ ገባው፡፡ ሞልቶ የተነሳው ታክሲ በየመሀሉ ሲጭን ሲያወርድ ወደ መጨረሻ ላይ ታክሲ ውስጥ ሶስት ሰዎች ብቻ ቀረን፡፡
ከፊት ለፊቴ ያሉትና በግምት እድሜያቸው ከ50 እስከ 55 የሚሆኑም እናት ወራጅ አሉ ታክሲው ፍጥነቱን ቀነሠ ወዲያው መልሠው ይቅርታ ትንሽ ፈቅ አድርገኝ አሉ፡፡ ሹፌሩ ፍጥነቱን ጨመረ በቃአሉ መውረድ የፈለጉት እናት፡፡ እሱ ግን አልበቃውም መውረድ ከሚፈልጉበት 15 ሜትር ያክል አርቆአቸው አቆመ፡፡ምነው አቁም አሉ ጮሁ የቤት ቁጥሮትን ቢነግሩኝ ቤት አስገባዎት ነበር ብሎ አሾፈ፡፡ ስራህ መሠለኝ አሉ፡፡ አንቱ ብሎ ሲያናግራቸው የነበረው ሾፌር አንቺን እያስቀደመ የስብድ መአቱን አዘነበባቸው፡፡
በተሳፈርኩባቸው ሁለትኛ ተከታታይ ታክሲዎች አንዲት ቃል እሳት አስነስታ በዛም ማንነት ሰዋረድ የእድሜ ልዩነት እና ታላቅነት ክብር ሲያጣ አስተዋልኩኝ፡፡ ግን ‹‹ትእግስታችን የት ገባ፣ መቻቻል ለምን ተሳነን፣ መተላለፍ ለምን አቃተን፡፡
በየቀኑ በየቦታው መተላለፍ እየተሳነን ብዙ ችግር ሲከሠት እናያለን፡፡ ጓደኛ ከአንደኛው ባለመግባባት እና ባለመተላለፍ ይጣላል፡፡ አሽከርካሪ ከእግረኛ ተሳፋሪ ከረዳትና ሠራተኛ ከአሠሪው ባል ከሚስቱ ሌላውም ወደ ኋላ ተመልሶ መነሻው ሲታይ ለምክንያት እንኳን ለመቅረብ በማይቻል ተራ ነገር ይጋጫል፡፡
በተለይ በዚህ ጊዜ በየፖሊስ ፕሮግራሙ የወንጀል ታሪክ እየተባሉ በሚቀርቡት ታሪኮቹ የሚበዙት የማበዛቱ ነገሮች እንዲህ ብሎ ተናገረኝ እንዲህ ብላ ተናገረቸኝ በሚል ተራ ነገር የሚነሳና መተላለፍ ባለመቻል ትእግስት በማጣት የሚከሠት ነው፡፡
በቅርቡ ከሶስት እና 4 ወር በፊት ይመስለኛል እዚህ አዲስ አበባ ላይ የተሰማ አንድ አሳዛኝ ታሪክ ነበረ፡፡
ልጁ የቅጣት ጊዜውን ጨርሶ ከእስር ከተፈታ ገና ቀኖች ማለፋቸው ነው፡፡ ወደ ታክሲ ሹፍርና ስራውም ተመልሷል፡፡
በአንደኛው ቀን በስራ ላይ እንዳለ አንዲት የቤት መኪና ከኋላው መጥታ ገጨቸው (ተደገፈቸው) የታክሲው ሹፌር ሞተር አጥፍቶ ፈጥኖ ወረደ፡፡ ገጨህኝ አለው አውቄያለው አለ ወርደህ እንኳን አታይምና ገንዘብ አይደል ይከፈላል አለ ገጪው ንግግር በታክሲው ሹፌር ላይ እልህን ወለደ ቃሎቹን መነዘራቸው እናም እጁን ጨብጦ በመስታወት ወደተቀመጠው ወጣት ሰነዘረ፡፡ ከዛ ሌላ ምንም ተጨማሪ ምልልስ አልነበረም ተመቺው በአንድ ቡጢ በተቀመጠበት ለዘለዓለም አሸለበ፡፡ በአንዲት ቃልና ንግግር ህይወት ጠፋ ከማረሚያ ቤት ከቀናት በፊት የወጣው ወጣት ደግሞ ወደዘብጥያ ተወረወረው፡፡
ግን መተላለፋችን ትእግስታችን ለምን ጠፋ ልዩነታችን ለምን በዛ በየታክሲው የሚፃፉ ፅሁፎች መቻቻልን መስበክ ትተው በፆታ በሌላውም ስልዩነት እና መለያየት ያወራሉ፡፡ ትእግስትና ታጋሽነትን የሚያስተምሩት አባባሎቻችን ‹‹የቤትህን አመል እዛው በሚልና በሌላም ያልተገቡ አባባልች ተተክተዋል፡፡
ይህንን ክፍተት ይሞላሉ ተብለው የሚጠበቁትና ይህንን ማድረግም ስራቸው የሆኑት የእምነት ተቋማት ሁሉ አንዳንዴ ፍቅር፣ መቻቻል፣ ትእግስትን በመስበክ ፋንታ እገሌ የተባለው እምነት ተከታይ እንዲህ አለ እያሉ እነሱም ሲያጠፋ ይታያል፡፡
ወደ ፖለቲካውም እንምጣ እገሌ ፓርቲ እንዲህ አለ እኔም እንዲህ ተናገረኝ እያሉና አንዱ በአንዱ ላይ ይነሳል፡፡ ልዩነትን መቀበል ተስኖን መተላለፍ አቅቶት ብዙ ጥፋት ይደርሳል፡፡
ግን ይህ ሁሉ ለምን ‹‹ ጐበዝ እረ አንተላለፍ››
ቁልፍ ቃላት
Fri, 07/04/2014 - 11:42