• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ነሐሴ 28፣ 2011/ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ያለው የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራትን ማጠናከርና አሰራራቸውን ማሻሻል ይገባል ተባለ

ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ያለው የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራትን ማጠናከርና አሰራራቸውን ማሻሻል ይገባል ተባለ፡፡በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 28፣ 2011/ የኢትዮጵያ ወሬ ነጋሪ ተቋማት ተአማኒነታቸው ምን ያህል ነው?

የኢትዮጵያ ወሬ ነጋሪ ተቋማት ተአማኒነታቸው ምን ያህል ነው? ለብሮድካስት ሚዲያዎች ፈቃድ የሚሰጠውንና የሚቆጣጠረውን አካል ንጋቱ ሙሉ አነጋግሯል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 28፣2011/ በመጪው ጳጉሜ 5 ቀን 2011 የሚከበረውን የፍትህ ቀን አስመልክቶ የቀድሞ ማዕከላዊ እስር ቤት ለህዝብ ጉብኝት ክፍት እንደሚደረግ ተነገረ

ማዕከላዊ እስር ቤት በተለይ በፖለቲካ እስረኞች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈፀምበት ነበር በሚል ተዘግቶ ወደ ሙዚየምነት እንዲቀየር በመንግስት መወሰኑ ይታወሳል፡፡እየተከበረ የሚገኘውን የፍትህ ወር ምክንያት በማድረግ እስር ቤቱ ከጳጉሜ አንድ እስከ አራት ለጉብኝት ክፍት እንደሚሆን የፍትህ ቀን ክብረ በዓል የኮሚዩኒኬሽን ሚዲያና መድረክ ዝግጅት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዝናቡ ቱኑ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በፍትህ ቀን በጠቅላይ ፍርድ ቤት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በፍትህ ላይ ያተኮረ የስዕል ኢግዚቢሽን እንደሚቀርብም ሰምተናል፡፡በመሆኑም ከጳጉሜ 1 እስከ 4 ድረስ የማዕከላዊ እስር ቤት ለማንኛውም ዜጋ ለጉብኝት ክፍት መሆኑን ከፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሰምተናል፡፡

ምህረት ሥዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 28፣2011/ በቢሊየን ብር ዕዳ የሚያናጥርበት የስኳር ኮርፖሬሽን ብድሬን እየከፈልኩ ነው አለ

በቢሊየን ብር ዕዳ የሚያናጥርበት የስኳር ኮርፖሬሽን ብድሬን እየከፈልኩ ነው አለ፡፡ ብድሬን የምከፍለው ግን እኔ ራሴ ተበድሬ ነው ብሏል፡፡ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 28፣2011/ አንዳንድ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ክፉኛ በመክሰራቸው፣ መንግስትን በቢሊየን የሚቆጠር ብር ኪሳራ ዳርገውታል...

አንዳንድ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ክፉኛ በመክሰራቸው፣ መንግስትን በቢሊየን የሚቆጠር ብር ኪሳራ ዳርገውታል፡፡እንደነልማት ባንክና የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን የመሳሰሉትን ድርጅቶች ከተዘፈቁበት የክስረት አረንቋ ጎትቶ ለማውጣት ዕገዛ ለማድረግ እየታሰበ መሆኑ ሲነገር መስማታችን በ2011 ዓ.ም ከነገርናችሁ ወሬዎች አንደኛው ነበር፡፡ ታዲያ ከሰሩ የተባሉት የመንግስት የልማት ድርጅቶች እንዴት ሆኑ? ትዕግስት ዘሪሁን ተከታትላዋለች

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 28፣ 2011/ በሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪው የተሰማራችሁ ባለሀብቶች አንደኛው ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት ዛሬ ይካሄዳልና ኑ እና በችግሮቻችን ዙሪያ እንወያይ ተብላችኋል

በሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪው የተሰማራችሁ ባለሀብቶች አንደኛው ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት ዛሬ ይካሄዳልና ኑ እና በችግሮቻችን ዙሪያ እንወያይ ተብላችኋል፡፡ይህን ያለው የኢትዮጵያ ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ አሰሪዎች ፌደሬሽን ነው፡፡አስፋው ስለሺ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 27፣2011/ በበዓል ምክንያት ከውጪ አገር በሚገቡ ምርቶች ሳቢያ ወደብ ላይ መጨናነቅ ተፈጥሯል

በበዓል ምክንያት ከውጪ አገር በሚገቡ ምርቶች ሳቢያ ወደብ ላይ መጨናነቅ ተፈጥሯል፡፡ወንድሙ ሀይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 27፣2011/ የወላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ወህዴግ) ሰላም ባለባቸው የወላይታ አካባቢዎች የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይነሳ ሲል ዛሬ መጠየቁ ተሰማ

የወህዴግ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ኢዮኤል ለሸገር እንደተናገሩት በደቡብ ክልል ችግር ባለባቸው ቦታዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መጣሉን እንደግፋለን ይሁንና ሰላማዊውነረ የወላይታ አካባቢ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማካተቱ አግባብ አይደለም ብለዋል፡፡የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር የወላይታን የክልልነት ጥያቄ ጉዳይ ህገ መንግስቱ በሚያዘው መልኩ መቀበልና ማስተናገድ ይገባዋል ሲል ፓርቲው አቋም መያዙንም ከአቶ ፍቃዱ ሰምተናል፡፡

ወህዴግ የህዝብን ፍላጎት በመያዝ ነው የክልልነት ጥያቄን ያነሳው ያሉት አቶ ፍቃዱ ክልሉን የሚመራው ፓርቲ ለህዝቡ የክልልነት ጥያቄ ተገቢውን መልስ ከመስጠት ይልቅ ጥናት አስደርጋለሁ በሚሉና በሌሎች ምክንያቶች ጥያቄውን ወደኋላ ለማስቀረት መሞከር ተገቢ አይደለም ሲሉም አቶ ፍቃዱ ነግረውናል፡፡ የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ወህዴግ) በተለያዩ ነጥቦች ዙሪያም ዛሬ መግለጫ መስጠቱ ተነግሯል፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 27፣2011/ የኢትዮጵያ ቱሪዝምን የማነቃቃት አቅም እንዳለው የተነገረለት የጉዞ መርሃ ግብር በይፋ መጀመሩ ተነገረ

መርሃ ግብሩ “ወርቃማው ጉዞ” የሚል መሪ ቃል ይኖረዋልም ተብሏል፡፡በናብሊስ ኮሚዩኒኬሽንና በተጉለት ሚዲያና ፕሮሞሽን መሰናዳቱንም ሰምተናል፡፡አዘጋጆቹ ዛሬ በእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሰማነው ኢትዮጵያውያን የቱሪዝም መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ በማድረግ በባህል፣ በመልእአ ምድር፣ በታሪክ፣ በተፈጥሮ ሀብትና በሰው ሰራሽ መስህቦች የተሳሰሩ እና ተመጋጋቢ እንዲሆኑ ማገዝ የጉዞው ዓላማ ነው፡፡

ህብረተሰቡ አንድነቱን ጠብቆ እንዲጓዝ ያሉት እሴቶች አንደኛው ከአንዱ ጋር የተሳሰረ መሆኑን ማስተዋወቅም የጉዞው ሌላው ተግባር እንደሆነ አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡ፕሮጀክቱ በ2012 12 የጉዞ መሰናዶዎች ይኖሩታል ተብሏል፡፡በታሪክ፣ በቋንቋና ባህል እንዲሁም በቱሪዝሙ ስራ ላይ የተሰማሩ የታሪክ ተመራማሪዎችና የኢንዱስትሪው አካላት ታግዞ ይካሄዳልም ተብሏል፡፡የጉዞው መርሃ ግብር የመጀመሪው ወደ አንጎለላ እንደተካሄደ ሰምተናል፡፡

አስፋው ስለሺ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 27፣2011/ በኢትዮጵያ የተደራጀ የጤና መረጃ ሥርዓት ባለመኖሩ ሰባት መቶ ሺህ ያህል ዜጎች ይሞታሉ ተባለ

ይህንን ችግር ያስቀራል የተባለና በኢትዮጵያ በማህበረሰብ ጤና ድንገተኛ የጤና ችግሮችና ባዮሜዲካል ላይ የተሰሩ የጥናትና ምርምር መረጃዎች በቀላሉ እንዲገኙ ያስችላል የተባለ የመረጃ ማዕከል መመስረቱ ተነግሯል፡፡በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተመሰረተው የብሔራዊ የጤና ጥናትና ምርምር መረጃ ማደራጃ ማዕከል፣ በአገሪቱ የማህበረሰብ ጤና የድንገተኛ የጤና ችግሮች እንዲሁም ባዮሜዲካል ጉዳዮች ላይ የተሰሩ የጥናትና ምርምር መረጃዎችን በመሰብሰብ እና በማደራጀት ላይ ያተኩራል ነው የተባለው፡፡በተጨማሪም የዘመኑ ሳይንስ የደረሰበትን ጥበብ በመጠቀም የህብረተሰቡን ጤና በማሻሻል ማገዝ ሌላው ተግባሩ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በአገሪቱ በጤናው ዘርፍ በርካታ የሚባሉ የጥናትና ምርምር ስራዎች ተሰርተው ለአመታት ቢሰበሰቡም መረጃዎቹ በተለያዩ ተቋማትና በተመራማሪዎች እጅ ተበታትነው በመገኘታቸው በጤናው ዘርፍ የሚደረጉ የምርምር ስራዎች በአግባቡ ጥቅም ላይ ሳይውሉ እንዲቀሩ አድርጓቸዋል ተብሏል፡፡በተለይ ላለፉት አራት አመታት በጤና ሚኒስቴር የጤና መረጃዎችን ለማደራጀት በርካታ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል ያሉት የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን በአገሪቱ በጤና መረጃ እጥረት ሰባት መቶ ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ይሞታሉ፣ በሚሊየን የሚቆጠሩ ደግሞ አላስፈላጊ በሆነ መልኩ በተደጋጋሚ ወደ ጤና ተቋማት ይሄዳሉ ብለዋል፡፡

የጤና መረጃ ሥርዓት ማዕከል መኖር ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ለሁሉም እንዲዳረስ የሚያግዝ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡የጤናና ምርምር ማዕከሉ፣ ኢንስቲትዩት ፎር ኸልዝ ሜትሪክ ኤንድ ኢቫልዌሽን ከተባለ ከአሜሪካ ተቋም ጋር በትብብር የተሰራ ሲሆን የፕሮጀክቱን ግንባታ ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስት ፋውንዴሽን የአስራ ሁለት ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አድርጎበታል፡፡ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደግሞ 6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንዳወጣበት ሰምተናል፡፡

ምህረት ሥዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 27፣2011/ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቺፍ ኢኮኖሚስት ቦታ እና የምክትል ዋና ገዥ ከፍተኛ ቦታዎች ማንም አልተሰየመባቸውም

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቺፍ ኢኮኖሚስት ቦታ እና የምክትል ዋና ገዥ ከፍተኛ ቦታዎች ማንም አልተሰየመባቸውም፡፡ምሁራን ቦታው ክፍት መሆን እንደሌለበት ይናገራሉ፤ የብሔራዊ ባንክስ ምን ይላል? ሸገር የባንኩን ዋና ገዥ ዶክተር ይነገር ደሴን ጠይቋል፡፡ተህቦ ንጉሴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers