• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሐምሌ፣15 2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የገንዘብ ዝውውር ላይ ሊሰራ ኃሣብ አለው ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • ባለፈው ማክሰኞ በአርሲ በደረሰ የመኪና አደጋ 5 ሰዎች ሞቱ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ከዘመን ርቀው የኤሌክትሪክ ኃይልና ብርሃን ላልነበራቸው የኢትዮጵያ የገጠር ነዋሪዎች በፀሐይ ብርሃን የሚሰራ መብራት ተገዛላቸው፡፡ (ዮኋንስ የኋላወርቅ)
 • በቅርቡ ህይወታቸው ላለፈው ሰዓሊ አለፈለገ ሰላም ትላንት የመታሰቢያ ዝግጅት ተካሄደላቸው፡፡ (ምስክር አወል)
 • ኢትዮጵያ ከካሜራ ጀርባ የሚል የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን ትላንት ተከፈተ፡፡ (ፍቅርተ መንገሻ)
 • ከይዞታቸው ለሚነሱ ተነሺዎች የሚከፈለው ካሣ ከወቅቱ የገበያ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ክለሳ እየተደረገበት መሆኑ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ቢፀድቅም ሥራ ላይ የሚውለው ከዓመት በኋላ እንደሆነ እወቁት ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • ኢትየጵያ ባለፈው ዓመት ወደ ውጭ ከላከቻቸው የብረት ምርቶች ከ22 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • የቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የግብርናና የጤና ዘርፎችን ለመደገፍ ሥራ ላይ የሚያውለው የገንዘብ መጠን እየጨመረ ይሄዳል ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • የሄሎ ካሽ ኔትወርክ በኢትዮጵያ በሚገኝ የፋይናንስ ተቋም የባንክ ሂሳብ ቁጥር የደንበኞች ቁጥር ከፍ ብሏል አለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ጊዜያቸውን ጠብቀው ፍቃድ ያሳደሱ የበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት 66 በመቶ ብቻ ናቸው ተባለ

የበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት በየሶስት ዓመቱ ፍቃዳቸውን ያሣድሣሉ፤ ፍቃዳቸውን የሚያሳድሱት ወደ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በመቅረብ ነው፡፡ ከቀናት በፊት በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም 1 ሺህ 225 የበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ፍቃዳቸውን ያሳድሳሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ ፈቃዱን ያሳደሱት ግን 803ቱ እንደሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መስፍን ታደሰ ነግረውናል፡፡ ፍቃዱን ያሳደሱት ድርጅቶችና ማህበራት ከታሰቡት 66 በመቶው ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡

የተቀሩት በስልክና በመገናኛ ብዙሃን ጥሪ ቢደረግላቸውም ቀርበው ፍቃዳቸውን እንዳላሳደሱ ነው የነገሩን፡፡ የሥራ ዕቅዳቸውንና አፈፃፀማቸውን በወቅቱ ባለማቅረባቸው እና ፍቃድ በወሰዱባቸው ሦስት ዓመታት ምንም ሥራ ያልሰሩ ድርጅቶችና ማህበራትም ፍቃዳቸው እንደልታደሰ ከአቶ መስፍን ሰምተናል፡፡ ዳይሬክተሩ እንዳሉት ጊዜውን ጠብቀው ፍቃድ ያላሳደሱ ድርጅቶችና ማህበራት ስራ ላይ እንደሌሉ ነው የሚቆጠረው፡፡ በዚህም ምክንያት ዕጣ ፈንታቸው መሰረዝ ይሆናል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ ፍቃድ ወስደው እየሰሩ ያሉ የበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ከሦስት ሺህ በላይ እንደሆኑ አቶ መስፍን ጨምረው ነግረውናል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ አለኝ የምትለው ትልቁ መራሄ ተውኔት የመጨረሻ ስንብት ትናንት አመሻሽ ላይ ተሠማ

ከኢትዮጵያ አልፎ ለምሥራቅ አፍሪካ የቲአትር ጥበብ ብርቱ ተቆርቋሪና ተሟጋች የነበረው የቲአትር አዘጋጅ መምህርና ሙሉ የመድረክ ሰው አባተ መኩሪያ ትናንት ህይወቱ አልፏል፡፡ ከ50 ዓመታት በላይ ታላላቆቹ የኢትዮጵያ ሊቃውንት የደረሷቸውን ቲአትሮች ወደ መድረክ የለወጠው የመራውና ያዘጋጀው አባተ መኩሪያ በጠና ህመም ሲሰቃይ ሰንብቷል፡፡ ከጥበብ ውጭ ማሰብም ሆነ መናገር አይችልም ሙሉ ተፈጥሮው የቲአትር ነው ሲሉ የሙያ አጋሮቹ የሚመሰክሩለት መራሄ ተውኔት አባተ መኩሪያ የብሉይ ዘመን አንጋፋ የውጭ ሀገር ቲአትሮች ወዘናቸውና ሥሪታቸው ሣይሸራረፍ የኢትዮጵያ ለዛ ይዘው እንዲመደረኩ ከፍተኛ አበርክቶ ነበረው፡፡

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን፣ ፀሐፊ ተውኔት መንግሥቱ ለማና ሌሎችም የፃፏቸውን ብዙ ቲአትሮች ሁነኛ አድርጎ አዘጋጅቶና መርቶ ህዝብ እንዲመለከታቸው አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን አለም አቀፋዊ ቅርፅ እንዲኖራቸው አድርጎ ካዘጋጃቸው ቲአትሮች ድንበር ተሻግረው አድናቆት የተቸራቸው ሽልማት የጎረፈላቸው ሥራዎችም ይጠቀሣሉ፡፡ ኢትዮጵያ ጭምር ማህበርተኛ የሆነችበትን የምሥራቅ አፍሪካ ቲአትር ኢንስቲትዩትን በማቋቋምና የምሥራቅ አፍሪካን የቲአትር ጥበብ በመወከል ለአለም በማስተዋወቅ የለፋ ሰውም ነው አባተ መኩሪያ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ፣14 2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • ለአተት ያጋልጣሉ የተባሉ የምግብ እና መጠጥ ቤቶች ታሸጉ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • ለአተት በሽታ ተገቢውን ትኩረት ያልሰጡ እና ምልክቱ የታየባቸውን ታማሚዎች አላስፈላጊ ምርመራን ያዘዙ 12 የግል የጤና ተቋማት የተለያዩ እርምጃዎች ተወሰደባቸው ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • አባተ መኩሪያ ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ትስስር ለማጠናከር አበክረው እንደሚሰሩ በመግባባት ስምምነት ፈረሙ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ያለባችሁ ኑ በነፃ ታከሙ ተብላችኋል፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለመጀመሪያ ጊዜ የህግ ትምህርትን በዶክትሬት ድግሪ ለማስተማር እየተዘጋጀሁ ነው አለ፡፡ (ምስክር አወል)
 • በአዲስ አበባ የጤና መኮንን ተማሪዎች ትምህርታችንን ሳንጨርስ ውጡ ተባልን አሉ፡፡ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ ተማሪዎቹን አሰናብት ተብያለሁ ምክንያቱን አላውቅም ብለዋል፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • በአዲስ አበባ የጤና ተቋማትን እና ባለሙያዎችን እንዲሁም የምግብና የመጠጥ ንግዶችን የሚቆጣጠሩ ባለሙያዎች እጥረት አጋጥሟል ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • በተጠናቀቀው የበጀት አመት ጊዜያቸውን ጠብቀው ፈቃድ ያሣደሱ የበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት 66 በመቶ ብቻ ናቸው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • ለፓርኪንሰን ህመም ብዙም ትኩረት አልሰጠሁም ሲል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ካለፈው ሣምንት ጀምሮ ለ7 ቀናት በዋና ዋና የከተማዋ አውራ ጎዳናዎች፣ መንደሮች እንዲሁም ገንዳዎች ቆሻሻ ተከማችቶ ሰንብቷል

የቆሻሻ ማንሻ መኪኖች የተሸከሙትን ቆሻሻ የሚያራግፉበት አጥተው ቆመዋል፡፡ ለወትሮው የከተማዋን ደረቅ ቆሻሻ ሸክፈው ሰንዳፋ ወደሚገኘው ዘመናዊ የቆሻሻ መጣያ ቦታ መሄድ የነበረባቸው እነዚሁ መኪኖች ወደ ሰንዳፋ ማቅናት አልሆነላቸውም፡፡ ሸገር የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከሆኑት አቶ ዳዊት አየለ ጋር ስለ ሰሞኑ የፅዳት ችግር ተነጋግሯል፡፡ አቶ ዳዊት ከመኖሪያ ቤትና ድርጅቶች ከሌሎችም ተቋማት የተሰበሰበው ቆሻሻ በወጉ ሊወገድ አለመቻሉን ተናግረው የቆሻሻ ክምር ወደ ሰንዳፋ ወስዶ ለመጣል ጊዜያዊ የተባለ ችግር ተፈጥሯል፡፡

በሰንዳፋ ያሉ አርሶ አደሮችና ነዋሪዎች የአዲስ አበባ ቆሻሻ ከዚህ በኋላ እንዳይመጣብን ሲሉ መከልከላቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ የየዕለት ደረቅ ቆሻሻ እየተረከበ በዘመናዊ መንገድ ለማስወገድ እንዲረዳ ተብሎ በሰንዳፋ የተገነባው የቆሻሻ መረከቢያ ማዕከል በዚህ ሰሞን አገልግሎቱን አቋርጧል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ህጋዊ የውጪ ሀገር የሥራ ሥምሪትን በተመለከተ እና የዜጐችን ደህንነት ያስጠብቃል ተብሎ በወጣው አዋጅ ደንብና መመሪያው ተዘጋጅቷል ተባለ

የውጭ ሀገር ሥምሪትን በምን መንገድ ማስፈፀም ይቻላል በሚለው ዙሪያ ደንበና መመሪያው እንደተጠናቀቀ ሰምተናል፡፡ አዋጁ ከወጣም አመት ያለፈው ሲሆን የተጠናቀቀለት መመሪያ መፅደቅ ብቻ ቀርቶታል ያሉን በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና አውሮፓ ህብረት ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል ፕሮጀክት ሚዲያ ኤክስፐርት አቶ ሀብታሙ ደምስ ናቸው፡፡ የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት ህግና ደንቡን ጠብቆ የዜጐች መብት ሳይጣስ እንዲቀጥል በተለያዩ የሀረብ ሀገሮች ስምምነቶች እየተደረጉ ነው ተብሏል፡፡
በውጪው ሀገር እንጀራ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ጥቅማቸውን እና ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ በሚደርሱባቸው ሀገሮች ባሉ ኤምባሲዎች በሙሉ ደህንነታቸውን የሚከታተል መመሪያ አና ባለሙያ እየተዘጋጀ መሆኑንም ሰምተናል፡፡ በዚህ ቀን የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ይጠናቀቃል ለማለት እንደማይቻል አቶ ሀብታሙ ነግረውናል፡፡ ምክንያቱን የጠየቅናቸው ባለሙያ በየክልሉ ሥራውን ሊያስፈፅሙ የሚችሉ ባለሙያዎች ተመድበው መጠናቀቅ ስላለባቸው ነው ብለውናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር ያላት ግንኙነት በአባይ ወንዝ ላይ ብቻ የተመሠረተ አይደለም ሲሉ በግብፅ የኢትዮጵያ አምባሣደር መሃመድ ድሪር ተናገሩ

አምባሣደር መሃመድ ድሪር ከትናንት በስቲያ ከግብፁ የግል ቴሌቭዥን አል ናሀር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው ይህን ያሉት፡፡ ሦስቱ ሀገሮች ግንኙነት ከአፍሪካ ዕድሜ ጠገቡ በመሆኑ እንዲህ በጠባብ ሁኔታ መታየት የለበትም ብለዋል፡፡ በርግጥ አሉ አምባሣደር መሃመድ ድሪር በርግጥ ሦስቱም ሀገሮች በአባይ ወንዝ የየራሳቸው ፍላጐት አላቸው ይህን ፍላጐታቸውን እንዴት ወደ አንድ የጋራ ጥቅም ማምጣት ይቻላል የሚለው ላይ ነው ትኩረት መደረግ ያለበት ብለዋል፡፡ አምባሣደር መሃመድ ጨምረውም ኢትዮጵያ እየገነባቸው ያለው የአባይ ግድብ ግንባታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ነው የቀረው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የግብፅ መገናኛ ብዙሀን የታችኛው የተፋሰሱ ሀገሮችን ይጐዳል በሚል የሚያወሩት ተገቢ አለመሆኑንም በቃለ ምልልሳቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በተከሰው ድርቅ ምክንያት ከብቶቻቸው የሞቱባቸው የሶማሌ ክልል ነዋሪዎችን መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት 75 ሚሊየን ብር መድቧል ተባለ

የሶማሌ ክልል ነዋሪዎችም በበኩላቸው 35 ሺህ ፍየሎችን ለመለገስ ቃል መግባታቸውን ሰምተናል፡፡ በሶማሌ ክልል አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ሃሰን አደም ለሸገር እንደተናገሩት ከተጎዱ 475 ሺህ የክልሉ ዜጎች መካከል ከብቶቻቸው የሞቱባቸው 100 ሺህ ያህል ይደርሳሉ፡፡ የሚተዳደሩትም ከብት በማርባት በመሆኑ መልሶ ለማቋቋም 75 ሺህ ብር ተመድቧል ብለዋል፡፡ በተመደበው ገንዘብም የሚያስፈልጓቸው ፍየሎችና ግመሎች ተገዝተው እንደሚቀርቡላቸው ሰምተናል፡፡
አቶ ሃሰን እንደሚሉት በመጀመሪያው ዙር 50 ሺህ ፍየሎችን ገዝቶ ለማከፋፈል ተወጥኗል፡፡ በአንድ ቀበሌም በቅርቡ 5 ሺህ ፍየሎች ተከፋፍለዋል ብለዋል፡፡

በመጭው ጊዜም ከብቶችን ገዝቶ የማቅረቡና በክልሉ ነዋሪ ቃል የተገቡ 35 ሺህ ፍየሎችን ሰብስቦ የማከፋፈሉ ሥራ ይቀጥላል ተብሏል፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 13፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • በአዲስ አበባ ከተማ አውራ ጎዳናዎችና መንደሮች ተከማችቶ ለሰነበተው ደረቅ ቆሻሻ ጊዜያዊ የመጣያ ቦታ ተገኝቶለታል፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • የተራቀቀ የልብ ህክምናን በመጀመር የመቐሌው ሀይደር ቀዳሚው የመንግሥት ሆስፒታል ሆኛለሁ ሲል ተናገረ፡፡ ህክምናው በግል ሆስፒታሎች ከዘጠና እስከ አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር ያስወጣል ተብሏል፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • በኢትዮጵያ የጐርፍ ተጋላጮች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን በላይ ነው ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ከአንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር ሰጠ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በደቡብ ክልል የሚገኙና ከዚህ ቀደም በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ደረጃ ተሰጥቷቸው በደረጃው ቅር የተሰኙ ሁለት ሆቴሎች ደረጃ እንደተስተካከለላቸው ሰማን፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • የአባይ ግድብ ግንባታ ሊጠናቀቅ ጥቂት ነው የቀረው ሲሉ በግብፅ የኢትዮጵያ አምባሣደር ተናገሩ፡፡ (ፋሰል ረዲ)
 • የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አዋጅን ማስፈፀሚያ ደንብና መመሪያ ተዘጋጅቷል ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • በድርቁ ምክንያት ከብቶቻቸው ለሞቱባቸው የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች የማቋቋሚያ ድጋፍ ሊደረግ ነው፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • ትናንት ምሽት በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት አንጋፋዋ ሁለገብ የጥበብ ሰው አሰለፈች አሽኔን የማመስገኛ ዝግጅት ተሰናድቶ ነበር፡፡ በህይወት ታሪኳ ላይ የተሰራ ሙዚቃና ተውኔትም ቀርቧል፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በዚህ አመት መንግሥት ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ ግዥ ፈፀመ

በድርቅ ለተጎዱ ዜጐች እርዳታ የተፈፀመው የስንዴ ግዢ ትልቁን ድርሻ ወስዷል ተብሏል፡፡ በዚህ አመት ከተፈፀመው 18 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የመንግሥት ግዢ መካከል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚሆን 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ሜትሪክ ቶን ስንዴ በ11 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መገዛቱን የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ተናግሯል፡፡ በተለያዩ ክልሎች በድርቅ ለተጐዱ ዜጎች ለምግብ ይሆን ዘንድ ከተፈፀመው የስንዴ ግዥ በተጨማሪ ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ በ32 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የትምህርት ቁሳቁሶች ተገዝተው መከፋፈላቸውን ከአገልግሎቱ ሰምተናል፡፡

በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የህዝብ ግንኙት ኃላፊ የሆኑት አቶ መልካሙ ደፋልኝ ለሸገር እንደተናገሩት በምንዛሬ እጥረት ምክንያት የስንዴ ግዥው እንዳይዘገይ አስመጭ ድርጅቶች ወረፋ ሳይጠብቁ የሚጠቀሙበት 60 ሚሊዮን ዶላር ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ አግኝተው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ትላንት አመሻሽ 12፡30 አካባቢ በጅማ ዞን በደረሰ የመኪና አደጋ የ9 ሰው ህይወት አልፏል ተባለ

አሳዛኝ ነው፡- ትላንት አመሻሽ 12፡30 አካባቢ በጅማ ዞን በደረሰ የመኪና አደጋ የ9 ሰው ህይወት አልፏል ተባለ፡፡ ከጅማ ዞን ናዳ ከተማ ወደ ኦሞ ሲጓዝ የነበረው ቅጥቅጥ አይሱዙ ጨለለቃ ዱንጋ ወረዳ ላይ ሲደርስ ተገልብጦ 9 ሰዎች የሞት፣ 18 ሰዎች ከባድ ጉዳት እና 11 ሰዎች ቀላል ጉዳት ገጥሟቸዋል ሲሉ የኦሮሚያ ፖሊስ የትራፊክ ደህንነት ባለሞያ ኮማንደር ንጉሴ ግርማ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ቅጥቅጥ አይሱዙው በመደበኛ 24 ሰው ጭኖ መጓዝ ሲገባው 38 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ ነበር ተብሏል፡፡ ከባድና ቀላል ጉዳት የገጠማቸው ሰዎች ወደ ጅማ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ሲሉ ኮማንደር ንጉሴ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

መሰረት በዙ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers