• Slider One

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ ለ7 ቀናት በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሰጥ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተናገረ

የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ ለ7 ቀናት በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሰጥ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ሀገር አቀፍ የኩፍኝ መከላከያ ክትባቶች በዓይነት በዕርዳታ ማግኘቱን ደግሞ የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ለሸገር ተናግሯል፡፡

ከ23 ሚሊዮን በላይ ህፃናትና ታዳጊዎችን ሊያስከትቡ ይችላሉ የተባሉ የኩፍኝ መከላከያ መድሃኒቶች ከ147 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እንደቀረበለት የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ተናግሯል፡፡የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ አድና በርሄ ለሸገር እንደተናገሩት ከዚህ በፊት ከ6 ወር እስከ 5 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ለሚገኙ ህፃናት የሚሰጠው ክትባት በ17 የኤጀንሲው ቅርንጫፎች ተሰራጭተዋል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የስርጭት መርሀ-ግብር መሠረት ከ6 ወር እስከ 5 ዓመት ለሆኑ ህፃናት በሁሉም ክልሎች ክትባቱ የሚሰጥ ሲሆን ጤና ጥበቃ ሚኒስትር በመረጣቸው ልዩ ቦታዎች ደግሞ ከ6 ወር እስከ 15 ዓመት ክትባቱ ለ7 ቀናት እንደሚሰጥ ሰምተናል፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካቲት 16፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በሀገራችን 17 የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሊገነቡ ነው ተባለ፡፡ ከ17ቱ ሦስቱ በደቡብ ክልል ይገነባል፡፡ ፓርኮቹ በጥራት ጉድለት ከውጭ የሚመለሱትን ምርቶች ይታደጋል ተብሏል፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • በግንባታ ላይ ካሉት የ40/60 ቤቶች ውስጥ ከ3 በመቶ በላይ የንግድ ቤቶች በጨረታ ሊተላለፉ ነው፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የእንስሣት ሐብትን ይበልጥ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ውጥን ተበሠረ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • በአገር አቀፍ ደረጃ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት መሥጠት ተጀመረ፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • ኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብቷን ለማሳደግ የቱሪዝም ዘርፍ ተጠቃሚነቷን ከፍ ማድረግ ይኖርባታል ተባለ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • አዲስ አበባ የመልካም አስተዳደር ችግሮቿ አንድ ሁለት ተብለው ተቆጥረው ከአገልግሎት አሰጣጧ ችግር ጋር ተደምረው አምስት ሺ መሆናቸው ተነገረ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ተገቢው ክብር ተነፍጎት የይስሙላ የተከበረው የትላንቱ የየካቲት 12 የሰማዕታት ቀን አከባበር ብዙዎችን አሳዝኗል

ተገቢው ክብር ተነፍጎት የይስሙላ የተከበረው የትላንቱ የየካቲት 12 የሰማዕታት ቀን አከባበር ብዙዎችን አሳዝኗል…ከአንድ ቀን በፊት የተከበረውን የሕወሃት ምስረታን የሚዘክሩ መፈክሮችና ባንዲራ በሰማዕታት ሐወልቱ ላይ መቀመጣቸው የብዙዎችን ልብ ሰብሯል የሚለው የሸገሩ ተህቦ ንጉሴ ዘገባ የትላንቱ አከባበር በተለይ በግፍ የተጨፈጨፉትን ሰማዕታት የማይመጥን ነው ይላል፡፡

የካቲት 11ን የሚዘክሩ ባንዲራዎችና መፈክሮችን በየካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት ላይ ማኖርም አሳዛኝ ነው የሚለው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው የታሪክ መምህርና ተመራማሪው አቶ አበባው አያሌው ከጊዜ ወደ ጊዜ የመታሰቢያ ስነስርዓቱ አከባበር እየተቀዛቀዘ ቢመጣም የዘንድሮው ደግም እጅጉን አሳዛኝ በሆነ መልኩ የግብር ይውጣና በሩጫ የተካሄደ ነው ይላል…

ፋሺስት ጣልያን የዛሬ 80 ዓመት የካቲት 12 ቀን 1929 ነበር በአዲስ አበባ እና በአካባቢዋ ዘር ከሐይማኖት ሳይለይ ከ30 000 በላይ ኢትዮጵያውያንን የጨፈጨፈው፡፡ይህንን ጭፍጨፋም ለማስታወስ ፋሺስት ከተወገደ በኋላ ከ1934 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ ሰማዕታቱን በሚዘክረው ሐውልት ስር የመታሰቢያ ስነ ስርዓት ይካሄዳል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም የካቲት 14፣2009

በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ከተማ መሬት ወስደው ግንባታ ያልጀመሩና የሊዝ ዋጋ ያልከፈሉ ዘጠኝ መቶ አልሚዎች እርምጃ ተወሰደባቸው

በአዲስ አበባ ከተማ መሬት ወስደው ግንባታ ያልጀመሩና የሊዝ ዋጋ ያልከፈሉ ዘጠኝ መቶ አልሚዎች እርምጃ ተወሰደባቸው፡፡ይህ የተነገረው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2009 ዓ.ም የ6 ወር ሪፖርት ዛሬ በቀረበበት ወቅት ነው፡፡

የከተማዋ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳሉት፤ በግማሽ ዓመቱ በሊዝ ውል መሠረት ግንባታ ያልተከናወነባቸውና የሊዝ ክፍያ በወቅቱ ያልተፈፀመባቸው 13 ሺ ቦታዎች ላይ ክትትል ለማድረግ ታቅዶ እንደነበር ጠቅሰው ይሁንና ክትልል ማድረግ በተቻለባቸው ዘጠኝ ሺ ቦታዎች ላይ በተደረገ ክትትል ለዘጠኝ መቶ አልሚዎች ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡

በውላቸው መሠረትም የሊዝ ክፍያ ያልፈፀሙ 42 አልሚዎች ላይ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ከዚህም በተጨማሪ ምንም ዓይነት ግንባታ ያላከናወኑ 14 አልሚዎች ውላቸው እንዲቋረጥ ተደርጐ መሬታቸውን ተነጥቀው ወደ መሬት ባንክ ገቢ ተደርጓል፡፡

ዛሬ የተጀመረው 4ተኛው ዓመት 2ተኛ መደበኛ ጉባዔ እስከ አርብ ድረስ ይቀጥላል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በመሠረት በልማት ግንባታ ምክንያት ከአዲስ አበባ ዙሪያ ከተነሱ ከ20 ሺ በላይ አርሶ አደሮች መካከል 30 በመቶዎቹ በከፋ ማህበራዊ ችግር ውስጥ ናቸው

በመሠረት በልማት ግንባታ ምክንያት ከአዲስ አበባ ዙሪያ ከተነሱ ከ20 ሺ በላይ አርሶ አደሮች መካከል 30 በመቶዎቹ በከፋ ማህበራዊ ችግር ውስጥ ናቸው… ቀሪዎቹ 70 በመቶዎቹም የተሰጣቸው ካሣ በህይወታቸው ላይ ምንም ለውጥ እንዳላመጣ በጥናት መረጋገጡ ይታወሣል…

የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን መልሶ ያቋቁማል የተባለው ፕሮጀክት ጽ/ቤት ለሥራ የሚያስፈልገው በጀት እስካሁን እንዳልፀደቀለት ተናገረ፡፡

ባለፈው አመት መጨረሻ የተቋቋመውና ከ3 ወር በፊት በይፋ ሥራ የጀመረው የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በዚህ አመት በአዲስ አበባ ዙሪያ በልማት ምክንያት የተነሱ 20 ሺ አርሶ አደሮችን መልሼ አቋቁማለሁ የሚል እቅዱን ነግሮን እኛም ለናንተ ነግረናችሁ ነበር፡፡

ይሁንና መልሶ የሚያቋቁምበት ገንዘብ እስካሁን በከተማ አስተዳደሩ እንዳልፀደቀለት ተናግሯል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መንግሥት በህገ-ወጥ መንገድ ታንዛኒያ ገብተዋል ተብለው በቁጥጥር ሥር ስለዋሉት ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተልኩኝ ነው አለ

መንግሥት በህገ-ወጥ መንገድ ታንዛኒያ ገብተዋል ተብለው በቁጥጥር ሥር ስለዋሉት ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተልኩኝ ነው አለ…የታንዛኒያ ፖሊስ በህገ-ወጥ መንገድ ሀገሬ ገብተዋል ያላቸውን 13 ኢትዮጵያዊያንን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የተናገረው ትላንት ማክሰኞ ነበር፡፡

በአሩሻ ስለተያዙት 13 ኢትዮጵያዊያን የጠየቅናቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ መረጃው እንደደረሳቸውና ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉት እንደሚገኙ ለሸገር ተናግረዋል፡፡በቅርቡም በዛምቢያ የተያዙ 130 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ያስታወሱት አቶ ተወልደ መዳረሻቸውን ደቡብ አፍሪካ ያደረጉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በተደጋጋሚ በፖሊስ እጅ ይወድቃሉ ብለዋል፡፡

በህገ-ወጥ መንገድ ታንዛኒያ ውስጥ ገብተዋል ተብለው በቁጥጥር ሥር የዋሉት ኢትዮጵያዊያን የጉዟቸው መዳረሻ የት እንደሆነ እስካሁን አለመታወቁን የነገሩን ቃል አቀባዩ ኬኒያ ባለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ማጣራት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካቲት 15፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • አብይ ፆሙ ለአሣ በሊታዎች እንጂ ለአሳዎች እንደማይመች ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • የታንዛኒያ ፖሊስ ሕገ-ወጥ ናቸው ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን አስሬአለሁ አለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • ከ92 በመቶ በላይ የሚሆኑ ዩኒቨርስቲዎች እና የጤና ተቋማት ሲገነቡ የአካባቢ ተፅዕኖ እና የአዋጭነት ግምገማ አያደርጉም ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • ሌኖቮ የተሰኘው አለም አቀፍ ኩባንያ ለኢትዮጵያ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርቶችን አስተዋውቃለሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የኢንዱስትሪዎችን የሰለጠነ የሰው ኃይል ክፍተት ለመሙላት አዲስ መላ እየታሰበ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • ከአንድ ወር በኋላ የሙከራ የህዝብና ቤት ቆጠራ ይካሄዳል ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የራሴ ሕንፃ ባለቤት ልሆን ነው አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በአዲስ አበባ የከተማ መሬት ወስደው ግንባታ ያልጀመሩና የሊዝ ዋጋ ያልከፈሉ 900 አልሚዎች እርምጃ ተወሰደባቸው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • ባለፈው ዓመት መጨረሻ የተቋቋመው የልማት ተነሺዎች አርሶ አደሮች መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በጀቱ እስካሁን አልፀደቀለትም፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በትምህርት ሥራ ላይ የተሰማሩ የኢትዮጵያ ተቋሞች ከባህር ማዶ የትምህርት ማዕከሎች ጋር ሊገናኙ የነሀሴን ወር መርጠውታል

በትምህርት ሥራ ላይ የተሰማሩ የኢትዮጵያ ተቋሞች ከባህር ማዶ የትምህርት ማዕከሎች ጋር ሊገናኙ የነሀሴን ወር መርጠውታል፡፡በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ ተማሪ ቤቶችን ከፍተው የሚያስተምሩ የየትኛውም ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ ማሰልጠኛዎችና የትምህርት መሣሪያ አምራችና አቅራቢ ድርጅቶች ሳይቀሩ በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በአንድነት ይገናኛሉ ተብሏል፡፡

በሌላው ሀገር የተለመደውና ብዙ የተሰራበት ባክ ቱ ስኩል የተባለ ልማድ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥም ሊተዋወቅ እንደሆነ የነገሩን የባክ ቱ ስኩል ኢትዮጵያ ዝግጅት አስተባባሪና የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሮቤል በቀለ ናቸው፡፡በዚህ ዝግጅት የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች፣ ዩኒቨርስቲዎች የተለየ ሙያ ላይ ስልጠና የሚሰጡ ተቋሞች ከነሐሴ 4 እስከ 7 ድረስ ቀን ቆርጠው ለመገናኘት ተቀጣጥረዋል ተብሏል፡፡

ትምህርት ቤቶች በቆይታቸው ያዳበሩትና ለሌሎች የሚያጋቡት ድንቅ የተባሉ ልምዶቻቸውን የሚለዋወጡበት የወደፊት ኃሣባቸውን ይፋ የሚያደርጉበት በትምህርት አሰጣጥ ስመ ጥር ከሆኑ የውጭ ሀገር ዩኒቨርስቲዎች ጋር የሚተዋወቁበትና ለትብብር የሚያመቻቸውን ቃል የሚለዋወጡበት የመገናኛ አጋጣሚ እንደሆነ አቶ ሮቤል ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ወቅቱ ለአዲሱ የትምህርት ዓመት መዘጋጃ እንደመሆኑ ተማሪዎች ወደፊት የሚያጠኑትን የትምህርት መስክ ባህሪ ለመመርመር የተለያዩ የምክር ኃሣቦችን የሚያገኙበት ይሆናል የሚሉት የባክ ቱ ስኩል ኢትዮጵያ ዝግጅት አስተባባሪ ከዚህ ተጨማሪ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥናቶችና ኃሣቦች የሚቀርቡባቸው ጉባዔዎች መሰናዳታቸውን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ ይመረመራል፣ ያለፈው የኢትዮጵያ የትምህርት ሂደት መለስ ተብሎ ይቃኛል፡፡የኢትዮጵያን ትምህርት በሌሎች ሀገሮች ተወዳዳሪ የሚያደርጉት የመፍትሄ ኃሣቦችም ይዋጡበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው የባክ ቱ ስኩል ዝግጅት በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚደረግ አሰናጆቹ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በመንግሥት የሚሰሩ ፕሮጀክቶች የሚሰሩበት ዋጋ እየናረ የሚጠናቀቁበትም ጊዜ እየተጓተተ ነው ተባለ

በመንግሥት የሚሰሩ ፕሮጀክቶች የሚሰሩበት ዋጋ እየናረ የሚጠናቀቁበትም ጊዜ እየተጓተተ ነው ተባለ…የኮንስትራክሽን ሴክተር ትራንስፖረንሲ ኢንሼቲቭ ወይም ኮስት ኢትዮጵያ የተባለው ተቋም ይፋ ባደረገው ጥናት እንዳለው በተለይም የመስኖ፣ የውሃ ግድብ ግንባታዎች በተያዘላቸው በጀትና ጊዜ እየተጠናቀቁ አይደለም፡፡

ከ36 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 52 ፕሮጀክቶች ላይ በተደረገው ጥናት እንደተባለው በመስኖ እና በግድብ ግንባታዎች በአማካይ ከተያዘላቸው ገንዘብ በላይ በመቶ ሰማንያ ፐርሰንት ወይም ወደ 2 እጥፍ ገደማ ወጪያቸው ንሯል፡፡መንግሥት የሚያሰራቸው የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ግንባታ ከ106 በመቶ በላይ ወጪያቸው የናረ ሲሆን የመንገድ ግንባታዎችም ከ42 በመቶ በላይ አሻቅበዋል፡፡የትምህርትና የጤና ተቋማት ህንፃዎችም ከ16 በመቶ በላይ ከተያዘላቸው ወጪ ከፍ ማለቱ ተነግሯል፡፡

ለፕሮጀክቶቹ ወጪ መናር አብይ ምክንያት ግንባታዎቹ ባልተሟላ ዲዛይን እየተጀመሩ እና በመሀልም የዲዛይን ለውጥ እየተደረገባቸው በመሆኑ እንደሆነ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ፕሮጀክቶቹ ከተጀመሩ በኋላ የዋጋ ግሽበትና የግንባታዎቹ ቁጥር መጨመር ሌላው ምክንያት መሆኑ ተነግሯል፡፡

የግንባታዎቹ ከዋጋቸው መናርም በላይ የጊዜ መጓተት ያለባቸው እንደሆነ የተነገረ ሲሆን የመስኖ እና የግድብ ግንባታዎች 151 በመቶ ያህል ከተያዘላቸው ጊዜ በላይ ይጓተታሉ፡፡የኢንዱስትሪ ግንባታዎችም 100 ፐርሰንት ሲንጓተቱ የጤና እና የትምህርት፣ የህንፃ ግንባታዎችም ከ105 በመቶ በላይ እንደሚጓተቱ ተነግሯል፡፡የመንገድ ግንባታዎቹ 48 በመቶ ያህል የጊዜ መጓተት እንደሚታይባቸው በጥናቱ ተነግሯል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካቲት 14፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃሕፍት ኤጀንሲ ውስጥ ያሉ ሥነ-ፅሁፎችን ጥናትና ምርምር አድራጊዎች በሚገባ እየተጠቀሙባቸው አይደለም ተባለ፡፡ (ንጋቱሙሉ)
 • በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለመደው ትምህርት ነኩ የ‘ባክ ቱ ስኩል’ ዝግጅት በኢትዮጵያም ሊከናወን እንደሆነ ሰምተናል፡፡ (ሕይወትፍሬስትሃት)
 • ድርቅ በቦረና ዞን በእንስሣት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ (ምሥክርአወል)
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመስኩ ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባዔ በአስተናጋጅነት ተመረጠ፡፡ (ንጋቱሙሉ)
 • በኢትዮጵያ የሚከናወኑ ግንባታዎች መጓተት የዋጋ ንረት እያስከተሉ ነው ተባለ፡፡ (ዮሐንስየኋላወርቅ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers