• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ስድስተኛው የቲካርድ ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡ ጃፓን ለአፍሪካ ልማት 300 ቢሊየን ዶላር መድባለች

ኢትዮጵያ በ6ኛው የቶኪዮ አፍሪካ ልማት ቲካድ ጉባኤ ላይ የነበራት ተሳትፎ መልካም ነበር ተባለ፡፡ጉባኤው በኢትዮጵያ አለመካሄዱ ያለመመረጥ እንጂ ከጀርባው ሌላ ምክንያት እንደሌለውም ተወርቷል፡፡ በኬንያ ርዕሰ መዲና ናይሮቢ የተካሄደው የቲካድ ጉባኤ በመጪዎቹ 3 ዓመታት ጃፓን ለአፍሪካ የ30 ቢሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገባችበት ሆኖ አብቅቷል፡፡  

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ በጉባኤው ላይ 3 መሰረታዊ ጉዳዮች ተነስተው እንደነበር ነግረውናል፡፡የቲካድ ጉባኤ በመጪዎቹ 3 ዓመታት ለአፍሪካ ከመደበው የ30 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት 10 ቢሊየኑ ለመሰረተ ልማት የሚውል መሆኑም ታውቋል፡፡

ፋሲል ረዲ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአማራ ክልል ዳግም በተነሳው ተቃውሞ ሰዎች መሞታቸውና የክልሉ መንግስትም የመከላከያ ሃይሉን እርምጃ እንዲወስድ ማዘዙ ተሰማ

የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በሶስት ቀናት በነበረው ተቃውሞ የሰዎች ህይወት መቀጠፉንና ንብረት መውደሙን ለሸገር ዛሬ ተናግረዋል፡፡ በክልሉ የተለያዩ ከተማዎች ውስጥ የአገልግሎት መስጪያ ተቋማት አገልግሎት ተቋርጦ ነበር ሲሉም ነግረውናል፡፡

ህዝቡ የሚያሳቸውን ህጋዊ የመብት ጥያቄዎችን በሌላ መንገድ የሚወስዱ ወገኖች በክልሉ ያለውን ጥፋት በማባባሳቸው የመከላከያ ኃይል እርምጃ እንዲወስዱ በክልሉ መንግስት መታዘዙንም አቶ ንጉሱ ይናገራሉ፡፡ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስር ከሚገኙ በደብረ ታቦር፣ በባህር ዳር፣ በጎንደርና በደብረ ታቦር የተነሱ ተቃውሞዎች ብዙ ንብረት መውደሙንና ህይወት መጥፋቱን የተለያዩ ወገኖች ሲናገሩ ተሰምቷል፡፡

ከ3 ቀናት በፊት በተነሳው ዳግም ግጭት ምክንያት  በደብረ ታቦር ብቻ ስድስት ሰዎች ሞተዋል ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ሲናገር ተሰምቷል፡፡ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አቶ ንጉሱ በበኩላቸው በ3ቱ ቀናት በታዩት ግጭቶች ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱና ንብረት እንደወደመ ተጠይቀው “ለጊዜው የሚባል ነገር የለም በቅርቡ ጥቅል መረጃዎች ይወጣሉ” ብለዋል፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በምግብና መጠጥ ዘርፍ የተሰማራችሁ ምርቶቻችሁን ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት የምትልኩ ኢትዮጵያውያን ላኪዎች አፍሪካውያን እህትና ወንድሞቻችሁም ምርቶቻችሁን ስለሚፈልጓቸው ብትጎበኟቸው መልካም ነው ተብላችኋል

ይህን ያሉት የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ /ኮሜሳ/ ስራ አስፈፃሚ ሚስ ሳንድራ አዌራ ናቸው፡፡ ይህንንም ያግዛል የተባለለትና ኢትዮጵያዊያን አነስተኛ እና ጥቃቅን አምራቾችን በክልሉ ያስተዋውቃል የተባለለት የምርት ናሙና ጉብኝትም በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ተካሂዷል፡፡

በአነስተኛ እና ጥቃቅን አምራቾች ተመርተው በአብዛኛው ህብረተሰብ ጥቅም ላይ ለሚውሉ ምርቶችና አምራቾቻቸው መንግስት ልዩ ትኩረት እንዲሰጣቸው ሚስ ሳንድራ ጠይቀዋል፡፡ አቅማቸውን እንዲያሳድጉም ከውጭ ከሚገቡ አስመጪዎች እና አቅማቸው ከፈረጠመ አምራቾች የሚደርስባቸውን ፈተና መቋቋም እንዲችሉ እገዛ እንደሚያስፈልጋቸውም ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 24፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአማራ ክልል ዳግም በተነሳው ተቃውሞ ሰዎች መሞታቸውና የክልሉ መንግስትም የመከላከያ ሃይሉን እርምጃ እንዲወስድ ማዘዙ ተሰማ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • ከመኪና መገልበጥ ጋር በተገናኘ የጨመረውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ አዳዲስ የመከላከያ ቴክኖሎጂዎችን ስራ ላይ ማዋል ያሻል ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪትን ለማስጀመር ዛሬም ስራዎቼን እያጠናቀቅኩ ነው ይላል፡፡ በዚህ ምክንያት ግን ህገ ወጥ ስደቱ እንደተጧጧፈ ይነገራል፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • ካለንበት ነሐሴ ወር አንስቶ እስከ ጥቅምት ወር ድረስ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው አየር በጣም እርጥበታማ ሊሆን መቻሉ ከ50 በመቶ በላይ ተረጋግጧል ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • የዝሆኔ ህመም ከሌሎች ክልሎች በበለጠ በደቡብ ክልል ይበረታል፡፡ ጫማ በመጫማት በሽታውን ተከላከሉት ተብሏል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምግብ ዋስትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር በመጭው ዓመት በዶክትሬት ዲግሪ ማስተማር ይጀምራል ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • ስድስተኛው የቲካርድ ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡ ጃፓን ለአፍሪካ ልማት 300 ቢሊየን ዶላር መድባለች፡፡ (ፋሲል ረዲ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ወጣቶች አገር አቀፍ ሸንጐ መካሄድ ጀመረ

ለአራት አመታት ያህል ተቋርጦ የቆየው ሀገር አቀፍ የወጣቶች የንቅናቄና ተሣትፎ ኮንፈረንስ በዛሬው እለት እየተካሄደ ነው…ሸንጐው የሚካሄደው አቃቂ በሚገኘው የአዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡ ከሰዓት በፊት ባለው ጊዜ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ስርጭት በኢትዮጵያ ያለውን ገፅታ የተመለከተ ውይይት ተካሂዷል፡፡

ውይይቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ከበደ ወርቁና የፌዴራል ኤች አይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ፈይሣ መርተውታል፡፡ በሽታውን ለመከላከል ወሣኙ ጉዳይ በተለይ በወጣቶች ዘንድ ግንዛቤ መፍጠር እንደሆነ ሁለቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ለልማት ተነሺዎች የቀበሌ ቤት ማቅረብ አለመቻሉ የመልሶ ልማት ሥራውን እያስተጓጎለው ነው ተባለ

የቀበሌ ቤት እጥረት በማጋጠሙ በዚህ አመት ለልማት የተፈለጉ ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ ነፃ ማድረግ እንዳልተቻለ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ተናገረ…ለዘጠኝ መቶ ለሚሆኑ የቀበሌ ቤት ፈላጊዎች ቤት ማቅረብ እንዳልቻለም ሰምተናል፡፡

በዚህ አመት ብቻ በአዲስ አበባ 1 ሺህ 737 ሄክታር መሬት ነፃ አድርጐ ለተለያየ የልማት ስራዎች እንዲውል ለመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽ/ቤት ማስረከቡን ኤጀንሲው ለሸገር ተናግሯል፡፡

በአመቱ ውስጥ የኮንዶሚኒየም ቤት መግዛት ለማይችሉ የልማት ተነሺዎች የቀበሌ ቤት ማቅረብ አለመቻሉ ለስራው እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን በኤጀንሲው ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ዘጠኝ መቶ ለሚሆኑት የቀበሌ ቤት ፈላጊዎች ቤት ማቅረብ ባለመቻሉም ለልማት በተፈለጉ አካባቢዎች ያሉና መፍረስ የነበረባቸው ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ማፍረስ አልተቻለም ብለዋል፡፡

የቀበሌ ቤት እጥረቱን ለመፍታትም በኪራይ የሚቀርቡ ቤቶችን የመገንባት ሥራ መጀመሩንና በዚህ አመት ያጋጠመውን የዘጠኝ መቶ የቀበሌ ቤት እጥረት ጨምሮ በመጭው አመትም ሊያጋጥም የሚችለውን የቤት እጥረት ሊፈታ በሚችል መጠን ይዘጋጃሉ መባሉንም ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 25፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጡ እየተተረማመሰ መሆኑ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ የነበረ 6 ሚሊየን 250 ሺህ ብር የሚገመት የብር ጌጣ ጌጥ ተያዘ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • ሰሞኑን በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት ለቡ አርሴማ አካባቢ ወንዝ ስር የሚገኝ የውሃ መስመር ተሰብሮብኛል በዚህም የተነሳ ውሃ የምትቸገሩ አካባቢዎች አላችሁና እወቁት ሲል የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ተናገረ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • በኢትዮጵያ በዓለም ባንክና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍ ከ36 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የምግብ፣ የጤናና የንፅህና አጠባበቅ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ተባለ፡፡ (ፍቅርተ መንገሻ)
 • የትግራይ አክሱም ከተማ ትናንት በአይነዋሪ ደምቃ ዋለች፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በአፍሪካ ቀንድ ደረጃ ኢትዮጵያውያን እንስሳት አርቢዎችንም ጭምር የሚያሳትፍ ክፍለ አህጉራዊ በዓል ለማክበር መታሰቡ ተሠማ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በአዲስ አበባ ለልማት ተነሺዎች የቀበሌ ቤት ማቅረብ አለመቻሉ የመልሶ ልማት ሥራውን እያስተጓጎለው ነው ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የኢትዮጵያ ወጣቶች አገር አቀፍ ሸንጐ መካሄድ ጀመረ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአክሱም ዘመናዊ የደም ባንክ አገልግሎት እየተሰጠ ቢሆንም የደም ለጋሾች መጠን ግን እንደተፈለገው አልሆነም ተባለ

የአክሱም ደም ባንክ ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን የማነህ ለሸገር ሲናገሩ ዘንድሮ ከበጐ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች 5 ሺህ ከረጢት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ የተገኘው 3 ሺህ 842 ከረጢት ብቻ ነው፡፡በአክሱም ከተማ በብዛት ደም የሚያስፈልጋቸው እናቶች ሲሆኑ ከወሊድና ከውርጃ ጋር በተያያዘ ከሆስፒታሎች ደም ለተጠየቀላቸው አንድ ሺህ ሁለት መቶ እናቶች ደም ቀርቦ ህይወታቸውን መታደግ ተችሏል ያሉት ዳይሬክተሩ ወባ እና አባላዛር በሽታዎች ሌሎቹ የደም ፈላጊን ቁጥር የጨመሩ ናቸው ብለዋል፡፡

ከእናቶች በተጨማሪ የመኪና አደጋም ተካቶ 3 ሺህ 600 ከረጢት ደም ተሰራጭቷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡በአክሱም 8 ነባር ሆስፒታሎችና በግንባታ ላይ ያሉ 7 አዳዲስ ሆስፒታሎች ሲኖሩ ደም ባንኩ ለሁሉም ሆስፒታሎች ደም ማቅረብ እንዲችል በጋራ እንስራ በማለት ከ90 በላይ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን ሰብስቦ ዛሬ በአክሱም ያሬድ ዜማ ሆቴል እየመከረ ነው፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

በትግራይ ክልል ለአተት ተጋልጠው ለነበሩ ከ700 በላይ ሰዎች ሕክምና መሰጠቱ ተሰማ

በትግራይ አተት ያጋጠማቸው ሰባት መቶ ሃያ ያህል ሰዎች ህክምና ማግኘታቸው ተሠማ፡፡ከ80 ዓመት በላይ ያስቆጠረውና ያረጀው የአድዋ ሆስፒታል በ185 ሚሊየን ብር ወጪ ፈርሶ እየተሰራ ነው፡፡የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጐይቶም ጊጋር ለሸገር ሲናገሩ ከሐምሌ 25 2008 ዓ.ም ወዲህ የአተት ህመም ያጋጠማቸው የመቐሌ፣ የእንደርታ ወረዳ፣ የቃፍታ እና የአፍገደር ፅምብላ ወረዳ የባሕላዊ ወርቅ ማዕድን ፈላጊዎች ናቸው ብለዋል፡፡

በተለይ በባህላዊ መንገድ የወርቅ ማዕድን የሚፈልጉት ሰዎች የንፁህ ውሃ ችግር እያጋጠማቸው ለበሽታ እንደሚጋለጡ የጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊው ነግረውናል፡፡ለህሙማኑ ህክምና ሰጥተናል አሁንም የመከላከል ሥራ ላይ ነን ያሉት አቶ ጐይቶም የክልሉ ጤና ቢሮ በሽታን ከመከላከል በተጨማሪ በ185 ሚሊየን ብር ወጪ የአደዋ ሆስፒታልን እንደገና እያሰራው ነው  የአዲግራትና ሌሎችም የጤና ተቋሞች ለማሳደስ በዝግጅት ላይ ነንም ብለዋል የቢሮው ምክትል ኃላፊ፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በመጪው አዲስ አመት ከ2 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ከተሜዎች አዳዲስ የሥራ እድል ተዘጋጅቷል ተባለ

እንዲህ ያለው የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ዛሬ የ2009 ዓ.ም እቅዱን በተመለከተ ከሠራተኞቹ ጋር ውይይት ባካሄደ ጊዜ ነው፡፡ከተዘጋጁት የሥራ እድሎችም ንግድና አገልግሎት አንዱ ሲሆን በዚህም 470 ሺህ ሰዎች ሥራ ያገኛሉ ተብሏል፡፡

322 ሺህ የሚሆኑትም በኮንስትራክሽን ዘርፍ ይሰማራሉ ተብሎ የታቀደ ሲሆን በከተማ ግብርና 232 ሺህ ሰዎች በሥራ ላይ ይውላሉ ተብሏል፡፡ከዚህም በተጨማሪ በመንግሥት ግዙፍ ፕሮጀክቶች ከ800 ሺህ በላይ ሰዎች ሥራ ይፈጠርላቸዋል ነው የተባለው፡፡ በጥቃቅን ማኑፋክቸሪንግ 258 ሺህ ሰዎች እንዲሰማሩ የታቀደ ሲሆን በአጠቃላይ በሥራ ለሚሰማሩትም 6 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ብድር ተዘጋጅቶላቸዋል ተብሏል፡፡

የሥራ እድል የሚሰጣቸው ከተሜዎች 5 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ይቆጥባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ሰምተናል፡፡ ከሚፈጠረው የሥራ እድልም ወደ 9 ቢሊየን ብር ለሀገር ውስጥ ገበያ ትስስር እንደሚፈጠርላቸውም ተነግሯል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ዕውቅና ሳያገኙ ለሙያ ምዘና ፈተና እናበቃለን ሲሉ የተገኙ ተቋማት በሕግ ሊጠየቁ ነው ተባለ

በአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ እውቅና ሳያገኙ ለCOC ፈተና እናበቃለን የሚሉ 13 ህገ-ወጥ ተቋማትን መያዙን የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ተናገረ…ተቋማቱን ህግ ፊት ለማቅረብም በዝግጅት ላይ ነው ተብሏል፡፡በማዕከሉ የምዘና አገልግሎት ዝግጅትና አሰጣጥ ዋና ሥራ ሂደት መሪ የሆኑት አቶ አበራ አመንቴ ለሸገር እንደተናገሩት እውቅና ሳይኖራቸው ለCOC ፈተና እናዘጋጃለን ብለው ከህብረተሰቡ ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 13 ተቋማት ተለይተዋል፡፡

ለCOC ፈተና ብቻ ለማዘጋጀት እውቅና የሚሰጥበት አሰራር እንደሌለ የተናገሩት አቶ አበራ የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን አሟልተው በተለያዩ ሙያዎች ላይ ለማሰልጠን በአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ እውቅና የተሰጣቸው ብዙ ማሰልጠኛ ተቋማት አሉ ብለዋል፡፡ በማዕከሉ የምሥራቅ ቅ/ጽ/ቤትሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ይትባረክ ከሃሊ በበኩላቸው ለCOC ፈተና እናዘጋጃለን ብለው በማጭበርበር ከህብረተሰቡ ገንዘብ የሚሰበስቡት ተቋማት በፈተና ላይ ብቻ ያተኮሩ ስለሆኑ ለሙያ ብቃት ምዝናውም  ራሳቸው ፈተና እየሆኑ ነው  ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers