• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ጷግሜ 1፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የቃጠሎ አደጋ የሟቾችን አስክሬን የመለየት ተግባር እየተከናወነ ነው ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በማዕድን ማውጣት ሥራ የተሰማራው ኬፊ ሚንራልስ በቱሉ ቆጲ ለማከናውነው ወርቅ ማውጣት ሥራ አለም አቀፍ አበዳሪዎች ተስፋ እየሰጡኝ ነው አለ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • ጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ችግር ውስጥ ነኝ ደግፉኝ ብሏችኋል፡፡ ማህበሩ እስካሁን የደገፉትን እና ያበረቱትን ለማመሰገን ዝግጅት አሰናድቶ ነበር፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • በኢትዮጵያ በነሀሴ ወር አጠቃላይ አመታዊ ተንከባላይ የዋጋ ግሽበት ቀዝቀዝ ያለ ነበር ተባለ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • ግብፅ በአባይ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ መሰናክል እየፈጠረች ነው ብላ የምታቀርበው ክስ መሠረት ቢስ ነው ተባለ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • የአመት በዓል ገበያን ለማረጋጋት ዘይት ከግብፅና ከኢንዶኔዥያ መግባቱ ተሰማ፡፡ የዘይቶቹ አይነትም የሚረጉም፣ የማይረጉም ናቸው ተብሏል፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሙስና ተግባር ተሰማርተው አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን ሠራተኞቹን ከሥራ አሰናብቻለሁ አለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዘንድሮ ከ120 ሺህ በላይ የሚሆኑ አዳዲስ ደንበኞችን የአገልግሎት ተጠቃሚ አድርጌያለሁ አለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ወደ መሰናዶ ትምህርት የሚያስገባው የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መግቢያ ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል

በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ረዲ ሽፋ እንደተናገሩት ወንዶች ለመደበኛና የማታ ተማሪዎች 2 ነጥብ 86 እና ከዚያ በላይ ሴቶች ደግሞ 2 ነጥብ 57 አና ከዚያ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ለአይነ ስውራን እና መስማት ለተሳናቸው የመሰናዶ መግቢያቸው ደግሞ ለወንዶች 2 ነጥብ 29 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች ደግሞ 2 ነጥብ እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ለግል ተፈታኝ ወንዶች 3 ነጥብ 43 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ለሴቶች 3 ነጥብ 14 ሆኖ መወሰኑን ሰምተናል፡፡

የመደበኛ ተማሪዎችና የማታ ተማሪዎች 280 ሺህ 744ቱ ፣ ከአርብቶ አደርና ታዳጊ ክልሎች 6 ሺህ 446ቱ ፣ ከግል ተፈታኞች ደግሞ 11 ሺህ 620ዎቹ በድምሩ 299 ሺህ 60 ተማሪዎች ወደ መሰናዶ ትምህርት ቤት ገብቶ መማር የሚያስችላቸውን ነጥብ አስመዝግበዋል ተብሏል፡፡

40 ነጥብ 2 ከመቶዎቹ ሴቶች ሲሆኑ 52 ነጥብ 8 በመቶዎቹ ወንዶች ናቸው መባሉን ሰምተናል፡፡

ምስክር አወል

አስተያየት ይፃፉ (3 Comments)

በሶማሌ ክልል የበልግ ዝናብ ላላገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች መንግሥት ምግብና ውሃ እያቀረበ መሆኑ ተሰማ

የመኖ እጥረት በመከሰቱም እንስሳት መኖና ውሃ ወዳለባቸው አጎራባች ቀበሌዎች እየተላኩ መሆኑን ሰምተናል፡፡በሶማሌ ክልል ካሉ ዘጠኝ ዞኖች መካከል ሰባቱ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚዎች ሲሆኑ በእነዚህ ዞኖች አንዳንድ ወረዳዎች ባለፈው ሚያዝያና ግንቦት ወሮች ማግኘት የነበረባቸውን የበልግ ዝናብ አላገኙም፡፡

በዚህም ምክንያት የውሃ እጥረት ተከስቷል፡፡ የክልሉ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ቢሮ ለሸገር እንደተናገረው ከሰባቱ ዞኖች በተወሰኑ ቀበሌዎች የሚኖሩ ዜጐችም ካለፈው ወር መጀመሪያ ጀምሮ የዕለት ጉርሳቸውንና ውሃ ከመንግሥትና በክልሉ ከሚሰሩ በጐ አድራጊ ድርጅቶች እየቀረበላቸው ነው ብለዋል፡፡ካለፈው ወር ጀምሮ የምግብ እርዳታ የሚቀርብላቸው ዜጐች በ2007 ዓ.ም በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከመንግሥት ምግብ ከሚቀርብላቸው 475 ሺህ የሚሆኑ የክልሉ ዜጐች መካከል አይደሉም ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ባዕድ ነገርን ከምግብ ጋር የቀላቀሉ እና ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒት እና የታሸጉ ምግቦችን ለገበያ ያቀረቡ በተለያየ ደረጃ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ሲል የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለሥልጣን ተናገረ

ባዕድ ነገርን ከምግብ ጋር የቀላቀሉ እና ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒት እና የታሸጉ ምግቦችን ለገበያ ያቀረቡ በተለያየ ደረጃ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ሲል የኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለሥልጣን ተናገረ፡፡

ከቅጣቱ መካከል 84 የሚሆኑት ፈቃዳቸው ተሰርዟል ተብሏል፡፡

በ2008 ዓ.ም ጥቆማ በሚቀበልበት 8482 ነፃ የስልክ መስመር 22 ሺህ ጥቆማዎች ተቀብሎ 7 ሺህ በሚሆኑት ላይ በቂ ማስረጃ አግኝቶ የ84ቱን ፈቃድ ሰርዟል ሲሉ የባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሳምሶን አብርሃም ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ከ3 ወር እስከ 3 ዓመት የታገዱ እንዳሉም ሰምተናል፡፡

ህብረተሰቡ ህገ-ወጥ ነገር ሲመለከት የመናገር እና የመጠቆም ልምዱ ጨምሯል ያሉት አቶ አብርሃም ባለሥልጣኑ 8482 ነፃ የስልክ መስመርን ለጥቆማ ካዘጋጀ በኋላ ብዙ የሚባለው ጥቆማ ያገኘው በዚህ ዓመት ነው ብለዋል፡፡

ከመጡት 22 ሺህ ጥቆማዎች ፣ 7 ሺህ ማስረጃ ተገኝቶባቸዋል ቀሪዎቹ ላይ ደግሞ ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጐ የቅሬታውን መንስኤ ለማወቅ እየተሞከረ ነው መባሉን ሰምተናል፡፡

መሰረት በዙ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የብሮድካስት ባለሥልጣን ከአገር ውስጥ የሳተላይት የቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር የጠየቁ 2 ተጨማሪ ድርጅቶች የተሟላ ሰነድ ካቀረቡ ፍቃድ ሊያገኙ ይችላሉ አለ

ተጨማሪ ማስተካከያ(ጷግሜ 1፣2008)

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ከሀገር ውስጥ የሣተላይት ቴሌዥን ስርጭት ለመጀመር የጠየቁ ሁለት ተጨማሪ ድርጅቶች የተሟላ ሰነድ ካቀረቡ ፍቃዱን ሊያገኙ ይችላሉ አለ…በባለሥልጣኑ የመገናኛ ብዙሃን ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ሲሣይ ለሸገር እንዳሉት ድምጸ ወያኔ ትግራይ ሐላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር እና ኢስት አፍሪካ ፊልም ፕሮዳክሽን የተባሉ ድርጅቶች የተሟላ ሰነድ ካቀረቡ ፍቃዱን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

ድርጅቶቹ ፍቃድ እንዲያገኙ ያልተወሰነው ያቀረቡት ሰነድ የተሟላ ባለመሆኑ እንደሆነ አቶ ሙሉጌታ አስታውሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን፣ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እና አርኪ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ ከሀገር ውስጥ የሣተላይት ቴሌቭዥን ስርጭት እንዲጀምሩ ፍቃድ እንዲሰጣቸው መወሰኑ ይታወሳል፡፡

ፍቃዱ የሚሰጣቸው ግን የፍቃድ ክፍያ ሲፈፅሙ እና ባለሥልጣኑ ያዘጋጀውን ውል ሲፈርሙ እንደሆነ አቶ ሙሉጌታ ነግረውናል፡፡ በሌላ ሀገር በሳተላይት አማካይነት የቴሌቭዥን ፕሮግራም የሚያሰራጩ ድርጅቶች ፍቃዱን ካሉበት ሀገር ያገኛሉ ተብሏል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 30፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • የሚከፍሉት ገንዘብ አጥተው በህክምና እጦት ሳቢያ ለስቃይና ለሞት የሚዳረጉትን የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው ህሙማንን ተስፋ የሚያለመልም የምሥራች በአዲስ አመት ዋዜማ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ፈተና በዝቶብኛል አለ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
 • ባዕድ ነገርን ከምግብ ጋር የቀላቀሉ እና ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒት እና የታሸጉ ምግቦችን ለገበያ ያቀረቡ በተለያየ ደረጃ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ሲል የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለሥልጣን ተናገረ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የብሮድካስት ባለሥልጣን ከአገር ውስጥ የሳተላይት የቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር የጠየቁ 2 ተጨማሪ ድርጅቶች የተሟላ ሰነድ ካቀረቡ ፍቃድ ሊያገኙ ይችላሉ አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ የበካይ ጋዞች የልቀት መጠንን የተመለከቱ መረጃዎችን ለሌሎች አካላትም እያጋራሁ ነው አለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • በሶማሌ ክልል የበልግ ዝናብ ላላገኙ ቀበሌዎች ነዋሪዎች በመንግሥት ምግብና ውሃ እየቀረበላቸው መሆኑ ተሠማ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ተቋርጦ የነበረው የካንሰር የጨረር ህክምና መስጫ ማሽን ሥራ ጀምሯል፡፡ ሌላኛው ቢታደስም ሥራ አለመጀመሩን ሰምተናል

በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነውና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ብቻ የሚሰጠው የካንሰር የጨረር ህክምና በማሽኖቹ እርጅና ምክንያት በተፈለገው ፍጥነት ህክምና እየተሰጠ አልነበረም… በእድሜ ምክንያት የጨረር አመንጭ ቁሱ በውጤታማነት መሠራት ያልቻለው አንደኛው ማሽን ከካናዳ በመጣ መለዋወጫ ጥገና ተደርጐለት ሥራ እንደጀመረ የሆስፒታሉ ኃላፊ ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃን ለሸገር ተናግረዋል፡፡

መለዋወጫውን ለማስመጣትም ከ3 አመት በላይ አንደወሰደ ሰምተናል፡፡ የካንሰር የጨረር ህክምና መስጫ ማሽኑ ከተጠገነ በኋላ ለአንድ ሰው ህክመና በሚሰጥበት ያህል ጊዜ አሁን እስከ አራት ሰዎችን ማከም አስችሏል ተብሏል፡፡ ለኢትዮጵያ የካንሰር የጨረር ህክምና ብቸኛ የሆነው የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አንዱ የተጠገነ ሲሆን ሁለተኛው ማሽን ተበላሽቷል የተባሉ እቃዎቹ በአዲስ ቢተኩለትም እስካሁን መሥራት እንዳልቻለ ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ23ተኛው ዙር የሊዝ ጨረታ በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች አዘጋጅቼያለሁ አለ…

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ23ተኛው ዙር የሊዝ ጨረታ በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች አዘጋጅቼያለሁ አለ…በቦሌ፣ በአቃቂ፣ በየካ፣ በንፋስ ስልክ እና በኮልፌ ክፍ ከተማዎች ቦታዎቹ ተዘጋጅተዋል ተብሏል፡፡ አጠቃላይም 124 ቦታዎች እንደተዘጋጁ ሰምተናል፡፡

በአምስቱም ክፍለ ከተማ ለቅይጥ፣ ለቢዝነስ ለመኖሪያም ጭምር መሬቶቹ እንደተዘጋጁ የነገሩን በአዲስ አበባ መሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ አቶ አዲስ የሸዋስ ናቸው፡፡ በ23ተኛ ዙር የመሬት ሊዝ ከቀረቡት ቦታዎች ውስጥም ለትልልቅ የገቢያ ማዕከል መገንቢያዎች ቦታዎቹ ተዘጋጅተዋል፡፡

ተህቦ ንጉሴ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ነሐሴ 27፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

 • አፍሪካ ኃይል የምታገኝባቸው ወንዞቿና ደኖቿ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት አቅም እያጡ ስለሆነ ታዳሽ ኃይሎች ላይ ብታተኩር መልካም ነው ተባለ፡፡ (ምስክር አወል)
 • የእብድ ውሻ በሽታ መከላከያ ክትባት ፍላጐትን በአገር ውስጥ ምርት ማሟላት አልተቻለም ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ከወጣቶች ለተነሱ ኢኮኖሚ ነክ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በህገ-መንግሥቱ አንቀፅ 49 ቁጥር 5 ውስጥ ያለው ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላት ልዩ መብት በአዋጅ ሊፀድቅ ነው፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • በጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ተቋርጦ የነበረው የካንሰር የጨረር ህክምና መስጫ ማሽን ሥራ ጀምሯል፡፡ ሌላኛው ቢታደስም ሥራ አለመጀመሩን ሰምተናል፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የኢትዮ ቻይና የንግድ ልውውጥ ምጣኔ የተራራቀ ነው ተብሏል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ23ኛው ዙር የሊዝ ጨረታ በተለያዩ ቦታዎች መሬት አዘጋጅቻለሁ አለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ለልማት ተነሺዎች የሚሰጠው የካሣ መጠን ሊሻሻል ነው ተባለ

ለመጭው አመት በአዲስ አበባ ከተማ ለልማት ተነሺዎች የማሰጠው ካሳ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናት እያደረገ መሆኑን የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ተናገረ…ኤጀንሲው ህዝብ ተማሮባቸዋል ተብሎ ከለያቸው አስራ ስድስት የመልካም አስተዳደር ችግሮች መካከል ለልማት ተነሺዎች የሚሰጠው የካሳ መጠን አንዱ መሆኑንም ከኤጀንሲው ሰምተናል፡፡

ችግሩን ለመፍታትም በየአመቱ የሚሰጠው የካሳ መጠን በየጊዜው ከሚኖረው የገንዘብ የመግዛት አቅም ጋር የተጣጣመ ለማድረግ እየተሞከረ መሆኑን በኤጀንሲው ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

አቶ ግርማ እንዳሉት የከተማዋን የልማት ተነሺዎች የካሳ አነሰኝ ጥያቄ ለመመለስ ካለፈው ሚያዝያ ወር ጀምሮ የግንባታ ነጠላ ዋጋ እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡

በማሻሻያ ዋጋው መሰረትም ዝቅተኛው የካሣ ክፍያ ከ115 ሺህ ብር ወደ 144 ሺህ ብር ከፍ እንዳለ ተናግረዋል፡፡

የሰብል ካሳ ዋጋም በካሬ 28 ብር የነበረ ሲሆን ወደ 34 ብር ከፍ ማለቱንና አጠቃላይ የካሳ አከፋፈል መጠኑም በ14 በመቶ እንዳደገ ከአቶ ግርማ ሰምተናል፡፡

በ2008 ዓ.ም 7 ሺህ 898 ቤቶች ፈርሰው 92 ሄክታር መሬት ለልማት ነፃ ተደርጓል፡፡

የካሳ ክፍያው መጠን ከሚያዝያ ወር ጀምሮ የተሻሻለ ሲሆን ለ5 ሺህ 549 የልማት ተነሺዎችም ለቤት መስሪያና ለዕቃ ማጓጓዣ የተሰጣቸውን ጨምሮ 598 ሚሊየን ብር ካሳ መከፈሉን ሰምተናል፡፡

በመጭው 2009 ዓ.ም ለልማት ተነሺዎች የሚሰጥ ካሳ ለማሻሻል ጥናት መጀመሩን የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ለሸገር ተናግሯል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በያዝነው ዓመት ብቻ 1 ሚሊየን 334 ሺህ 329 ተገልጋዬችን ማስተናገዱን የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ተናገረ

በያዝነው ዓመት ብቻ 1 ሚሊየን 334 ሺህ 329 ተገልጋዬችን ማስተናገዱን የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ተናገረ፡፡ ለመስተንግዶ አስቸጋሪ የሆነውን ወረፋ ለማቃለልም አስራ አራተኛ ቅርንጫፌን በመካኒሳ አካባቢ ልከፍት ነው ብሏል…

የቅርንጫፉ መከፈት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ያለውን ወረፋ በመጠኑ ይቀንሰዋል ተብሎ ታምኖበታል ሲሉ የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ረዳት ኃላፊ አቶ አለምሸት መሸሻ ተናግረዋል፡፡

በየቀኑ ሰነድን ለማስመዝገብ እና ለማረጋገጥ በአማካይ 4 ሺህ 970 ሰዎች ኤጀንሲውን ይጐበኛሉ ተብሏል፡፡

ሰነዶችን የመመዝገብና የማረጋገጥ ኃላፊነት የተሰጠው ኤጀንሲ ወክልና ለመስጠትም ሆነ ለማንሳት በድረ-ገፅ በwww.daro.gov.et ላይ የነፃ አገልግሎት እየሰጠሁ ነው ብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም በዋና መሥሪያ ቤት ብቻ ይሰጥ የነበረው የሚንቀሳቀስ እና የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፉን ሥራ አሁን በተጨማሪ በቅርንጫፍ አምስትም ይሰጣል፡፡ የማህበራትን ሰነድ መመዝገብ እና ማረጋገጥ ከዋና መሥሪያ ቤት በተጨማሪ በቅርንጫፍ 12 እየተሰጠ ነው መባሉን ሰምተናል፡፡

መሰረት በዙ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers