• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

አርቲስቲክ ማተሚያ ድርጅት ከ328 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ገንዘብ ትላንት ወደ ግል ይዞታ ተዘዋወረ

አርቲስቲክ ማተሚያ ድርጅት ከ328 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ገንዘብ ትላንት ወደ ግል ይዞታ ተዘዋወረ፡፡ ድርጅቱ ወደ ግል ይዞታ የተዘዋወረው ትላንት ከሰዓት በኋላ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በተከናወነ የፊርማ ስነ-ሥርዓት ነው፡፡ አርቲስቲክ ማተሚያ ድርጀትን የገዛው ፈለቅ ትሬዲንግ PLC እና ኮርፓሬት ኮምፒዩተር ሴንተር PLC የህብረት ሽርክና ማህበር መሆኑን ሰምተናል፡፡

ሽርክና ማህበሩ ከአጠቃላይ ክፍያው 35 በመቶውን ወይም ከ115 ሚሊየን ብር በላይ በቅድሚያ መክፈሉ ተነግሯል፡፡ ቀሪውን 65 በመቶ ደግሞ በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ ይከፍላል ተብሏል፡፡ ወሬውን ለሸገር የነገሩት በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር የኮርፓሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንድአፍራሽ አሰፋ ናቸው፡፡

ንጋቱ ረጋሣ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጷግሜ 2፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የፌዴራሉ ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2008 ዓ.ም የሰራሁት ሥራ ውጤታማ አድርጎኛል ብሏል፡፡ ለመሆኑ ኮሚሽኑ ምን ሰርቶ በምን ውጤታማ ሆነ? ንጋቱ ረጋሣ
 • የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የበዓል ገበያው እየደራለት ነው ተባለ፡፡ ወንድሙ ኃይሉ
 • የአዲስ አበባ ቀይ መስቀል ማህበር ለችግረኛ ህፃናት የትምህርት መርጃ መሳሪያ ድጋፍ ላደርግ ነው አለ፡ንድሙ ኃይሉ
 • ለአመታት ገንዘብ ከፍለው ኤሌክትሪክ እንዲገባላቸው ሲጠባበቁ ከነበሩት 90 በመቶዎቹ ዘንድሮ ኤሌክትሪክ አግኝተዋል፡፡ ዮሐንስ የኋላወርቅ
 • የህክምና ባለሙያዎች ባለፀጋ የሆነው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለህክምና ፈላጊዎች የሚሰጠው አገልግሎት ግን ያን ያህል አርኪ አይደለም ፤ ምክንያቱ ምን ይሆን? እየተጠናቀቀ ባለው 2008 ዓ.ም የሆስፒታሉ አገልግሎት ምን ይመስል ነበር? ትዕግስት ዘሪሁን
 • ኢትዮጰያ የጫማ ምርቶቿን ቀጥታ ወደ አሜሪካ ገበያ ልትልክ ነው፡፡ ወንድሙ ኃይሉ
 • የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት በበዓላት ሰሞን ሊያጋጥም የሚችል የኃይል መቆራረጥ መጥፋት ችግርን ለማቃለል ከወዲሁ ዝግጅት አድርጌያለሁ አለ፡፡ ቴዎድርስ ወርቁ
 • አርቲስቲክ ማተሚያ ድርጅት ከ328 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ገንዘብ ትላንት ወደ ግል ይዞታ ተዘዋወረ፡፡ ንጋቱ ረጋሣ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ጷግሜ 1፣2008

ክፍል ዘጠኝ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር ጤናማ የሆነ የበዓል ቀን አመጋገብ ስርዓት እና የአልኮል መጠን አወሳሰድ ቀመር
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ፅጌረዳን እናስተዋውቃችሁ…

ባንድ ወቅት በአስከፊው የሴተኛ አዳሪነት ሕይወት ውስጥ ነበረች፡፡ ሲጋራና ጫቱ፤ ሐሺሹና መጠጡ ሕይወቷ ነበር፡፡ አሁን ላይ ግን ከአስከፊው ሕይወት ወጥታ በሊደርሺፕ ማኔጅመንት የማስተርስ ዲግሪዋን ይዛ ከሴተኛ አዳሪነት ሕይወት ለመውጣት እየተማሩ ያሉትን ትረዳለች…

WSG በተባለ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ድጋፍና የእርሷም ቁርጠኝነት ታክሎበት ከሴተኛ አዳሪነት ሕይወት መውጣቷን የምትናገረው ፅጌረዳ በመጀመሪያ በነርሲንግ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያዘች ይለናል የሸገሩ ዮሐንስ የኋላወርቅ ዘገባ፡፡ ከዚያ ደግሞ በሊደርሺፕ ማኔጅመንት ሁለተኛ ዲግሪዋን ያዘች፡፡

ከዛሬ 3 ዓመት ጀምሮ ደግሞ በWSG ድጋፍ ሌሎች ከሴተኛ አዳሪነት ለመውጣት የሚተጉ ወጣት ሴቶችን ተምረው እንዲለወጡ እየረዳች ነው፡፡

ፅጌረዳ አሁን ላይ የ WSG የዲቦራ ማዕከል ኃላፊ ነች፡፡

ባሳለፍነው ቅዳሜም በድርጅቱ ድጋፍ ተምረው ከሴተኛ አዳሪነት ሕይወት የተላቀቁ ወጣት ሴቶች በፋርማሲ በዲግሪ እንዲሁም በአካውንቲንግ በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡

ፅጌረዳ ከሕይወት ልምዴ እየጠቀስኩ፣ ስለ አላማና ስኬት፣ ስለ አደንዛዥ ዕፅና መጠጥ አደገኛነት አስተምራቸዋለሁ ትላለች፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአመት በዓል ገበያን ለማረጋጋት ዘይት ከግብፅና ከኢንዶኔዥያ መግባቱ ተሰማ፡፡ የዘይቶቹ አይነትም የሚረጉም፣ የማይረጉም ናቸው ተብሏል

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓት አቅራቢ ድርጅት ለአመት በዓል ገበያን የማረጋጋባቸውን ዘይቶች ከግብፅና ኢንዶኔዥያ አስገብቻለሁ አለ…የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደሳለኝ ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ ዘይቶቹ ሰኒና አቬና የሚባሉ ሲሆኑ የሚረጉም፣ የማይረጉም አይነት ናቸው ብለዋል፡፡

በድርጅቱ የአዲስ አበባ 15 እና የኢትዮጵያ 80 ቅርንጫፎች በኩል ዘይቶቹ ለገበያ የቀረቡ ሲሆኑ የሚረጋውን 5ቱን ሌትር በ115 ብር፣ የማይረጋውን አምስቱን በ270 ብር ዋጋ መሸመት ትችላላችሁ በማለት አቶ ዳንኤል ተናግረዋል፡፡

ከዘይት በተጨማሪ ከወንጂ ስኳር ፋብሪካና ከውጪ ሀገር ለኢትዮጵያ ለማከፋፈል 397 ሺህ ኩንታል ስኳር የተገዛ ሲሆን አንደ አሳይታ፣ ጋምቤላ፣ ያቤሎ ላሉ አካባቢዎች ርቀቱን ከግምት በማስገባት ትራንስፖርትን ታሳቢ አድርገን ኪሎ ስኳር በ18 ብር ከ40 ሣንቲም፣ ለአዲስ አበባና ዙሪያዋ ደግሞ ኪሎ በ15 ብር ከ40 ሣንቲም በሸማቾች ህብረት ሥራ በኩል መሸመት ትችላላችሁ በማለትም አቶ ዳንኤል ተናግረዋል፡፡

አቪና እና ሰኒ የተሰኙት ዘይቶች ከግብፅና ኢንዶኔዥያ የገቡት በጥራትና ደረጃዎች አስፈላጊው የጥራት ደረጃ ቁጥጥር ተደርጐላቸው ነው በማለትም የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ነግረውናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዘንድሮ ከ120 ሺህ በላይ የሚሆኑ አዳዲስ ደንበኞችን የአገልግሎት ተጠቃሚ አድርጌያለሁ አለ

ከአስር ዓመት በላይ የኤሌክትሪክ ሃይል ለማግኘት ገንዘብ ከፍለው ሲጠባበቁ ከነበሩ ከ140 ሺህ በላይ ግለሰቦችና ፋብሪካዎች መካከል 90 ነጥብ 2 በመቶ ያህሉ በዚህ አመት አገልግሎት ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ…

የኤሌክትሪክ ሃይል ለማግኘት ገንዘብ ከፍለው የሚጠባበቁ ግለሰቦችና ፋብሪካዎች እስከ 10 ዓመት ድረስ ጥያቄያቸው መልስ ሳያገኝ የተንገላቱ በርካታ ናቸው፡፡ ይህም በደንበኞች ዘንድ ቅሬታ የፈጠረ የመልካም አስተዳደር ችግር ተብሎ በአገልግሎቱ መለየቱን ሰምተናል፡፡

ገንዘባቸውን ከፍለው አገልግሎቱን የሚጠባበቁ የ140 ሺህ 587 ዜጐች ጥያቄ ለመፍታት ተወጥኖ ነበር ከመካከላቸው የ126 ሺህ ያህሉ ኤሌክትሪክ ሃይል ማግኘታቸው በአገልግሎቱ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገ/እግዚአብሔር ታፈረ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሙስና ተግባር ተሰማርተው አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን ሠራተኞቹን ከሥራ አሰናብቻለሁ አለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በነ አያ ጅቦ ሌቦ መንገድ ውስጥ ገብተው አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን ሠራተኞቹን ከስራ ማሰናበቱን ተናገረ፡፡

የቀድሞ የመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞችና የኤሌክትሪክ ሙያ ያላቸው ግለሰቦችም በገንዘብ እየተደራደሩ የተቋሙን ሥራ እንደማይሰሩ ለማረጋገጥ ችለናል ብለዋል፡፡

ከአቶ ገብረእግዚአብሔር ታፈረ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሸገር እንደሰማው በዓመቱ ገንዘብ እየተቀበሉ ሥራን ሲሰሩ የነበሩ ሠራተኞች እና የቢሮ ኃላፊዎች ተይዘዋል ሠራተኞቹም በቁጥር 24 ስለመሆናቸው ነግረውናል፡፡

ከዚህ ውጭም ማጣራት ስናደርግ እንዳየነው የተቋሙ ሠራተኛ ያልሆኑ እና የኤሌክትሪክ ሙያ ያላቸው እንዲሁም የቀድሞ የተቋሙ ሠራተኞች የሆኑ በስራው ውስጥ ተሳትፈው ተገኝተዋል ብለዋል፡፡

ዘንድሮ በድርድር ገንዘብ እየተቀበሉ ሲሰሩ ተደርሶባቸዋል የተባሉት 24ቱ ሠራተኞች ከሥራቸው የተሰናበቱ ሲሆን እንደ ጥፋታቸው አይነትም  ለፍርድ ይቀርባሉ ብለዋል፡፡

ቴዎድሮስ ወርቁ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ባለፈው ቅዳሜ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተነሣው ቃጠሎ ምክንያት የሞቱ ሰዎችን ማንነት የመለየቱ ሥራ እየተካሄደ ነው ተባለ

የመንግሥት ኮሙኒኬሸን ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው መሀመድ ሰይድ ዛሬ ለሸገር እንደተናገሩት የሟቹ ቁጥር በማህበራዊ ድረ-ገፆች የተባለውን ያህል አይደለም እስከ አሁን ድረስም ማወቅ የተቻለው 23 ሟቾችንና 9 ቁስለኞችን ነው ብለዋል፡፡

የሟቾች ማንነት ተለይቶ ባለመሰጠቱ እና ከሆስፒታል ምንጮች የሚሰማው ደግሞ በእሣት ተቃጥሎ የሞተ አለመኖሩን ነውና መለየቱ ለምን ጊዜ ወሰደ ያልናቸው ኃላፊው፣ “በተጨባጭ ጉዳቱ የደረሰው በእሣት ቃጠሎ አማካኝነት ነው፡፡በየማህበራዊ ድረ-ገፁ የሚናፈሰው ወሬም ሀሰት ነው” ብለዋል፡፡

የማጣራት ሥራው አብቅቶ ለሟቾች በተገቢው መንገድ የቀብር ሥነ-ሥርዓት እንዲደረግ ለቤተሰብ አስክሬን የሚሰጠው መቼ ይሆናል ያልናቸው አቶ መሀመድ፣ “የሟቾቹ ማንነት እየተጣራ ነው ያለው በዚህ ሰዓት በዚህ ጊዜ ለማለት ግን አሁን አልችልም፤ ቤተሰቦች በትዕግስት እንዲጠብቁን እንጠይቃለን” ብለዋል፡፡

ባለፈው ቅዳሜ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተነሣው ቃጠሎ ምክንያት የሞቱት ሰዎች አብዛኛዎቹ በመረጋገጥ በደረሰ አደጋ ነው ተብሏል፡፡

የኔነህ ሲሳይ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ጷግሜ 1፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የቃጠሎ አደጋ የሟቾችን አስክሬን የመለየት ተግባር እየተከናወነ ነው ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በማዕድን ማውጣት ሥራ የተሰማራው ኬፊ ሚንራልስ በቱሉ ቆጲ ለማከናውነው ወርቅ ማውጣት ሥራ አለም አቀፍ አበዳሪዎች ተስፋ እየሰጡኝ ነው አለ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • ጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ችግር ውስጥ ነኝ ደግፉኝ ብሏችኋል፡፡ ማህበሩ እስካሁን የደገፉትን እና ያበረቱትን ለማመሰገን ዝግጅት አሰናድቶ ነበር፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • በኢትዮጵያ በነሀሴ ወር አጠቃላይ አመታዊ ተንከባላይ የዋጋ ግሽበት ቀዝቀዝ ያለ ነበር ተባለ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • ግብፅ በአባይ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ መሰናክል እየፈጠረች ነው ብላ የምታቀርበው ክስ መሠረት ቢስ ነው ተባለ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • የአመት በዓል ገበያን ለማረጋጋት ዘይት ከግብፅና ከኢንዶኔዥያ መግባቱ ተሰማ፡፡ የዘይቶቹ አይነትም የሚረጉም፣ የማይረጉም ናቸው ተብሏል፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሙስና ተግባር ተሰማርተው አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን ሠራተኞቹን ከሥራ አሰናብቻለሁ አለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዘንድሮ ከ120 ሺህ በላይ የሚሆኑ አዳዲስ ደንበኞችን የአገልግሎት ተጠቃሚ አድርጌያለሁ አለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ወደ መሰናዶ ትምህርት የሚያስገባው የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መግቢያ ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል

በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ረዲ ሽፋ እንደተናገሩት ወንዶች ለመደበኛና የማታ ተማሪዎች 2 ነጥብ 86 እና ከዚያ በላይ ሴቶች ደግሞ 2 ነጥብ 57 አና ከዚያ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ለአይነ ስውራን እና መስማት ለተሳናቸው የመሰናዶ መግቢያቸው ደግሞ ለወንዶች 2 ነጥብ 29 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች ደግሞ 2 ነጥብ እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ለግል ተፈታኝ ወንዶች 3 ነጥብ 43 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ለሴቶች 3 ነጥብ 14 ሆኖ መወሰኑን ሰምተናል፡፡

የመደበኛ ተማሪዎችና የማታ ተማሪዎች 280 ሺህ 744ቱ ፣ ከአርብቶ አደርና ታዳጊ ክልሎች 6 ሺህ 446ቱ ፣ ከግል ተፈታኞች ደግሞ 11 ሺህ 620ዎቹ በድምሩ 299 ሺህ 60 ተማሪዎች ወደ መሰናዶ ትምህርት ቤት ገብቶ መማር የሚያስችላቸውን ነጥብ አስመዝግበዋል ተብሏል፡፡

40 ነጥብ 2 ከመቶዎቹ ሴቶች ሲሆኑ 52 ነጥብ 8 በመቶዎቹ ወንዶች ናቸው መባሉን ሰምተናል፡፡

ምስክር አወል

አስተያየት ይፃፉ (3 Comments)

በሶማሌ ክልል የበልግ ዝናብ ላላገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች መንግሥት ምግብና ውሃ እያቀረበ መሆኑ ተሰማ

የመኖ እጥረት በመከሰቱም እንስሳት መኖና ውሃ ወዳለባቸው አጎራባች ቀበሌዎች እየተላኩ መሆኑን ሰምተናል፡፡በሶማሌ ክልል ካሉ ዘጠኝ ዞኖች መካከል ሰባቱ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚዎች ሲሆኑ በእነዚህ ዞኖች አንዳንድ ወረዳዎች ባለፈው ሚያዝያና ግንቦት ወሮች ማግኘት የነበረባቸውን የበልግ ዝናብ አላገኙም፡፡

በዚህም ምክንያት የውሃ እጥረት ተከስቷል፡፡ የክልሉ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ቢሮ ለሸገር እንደተናገረው ከሰባቱ ዞኖች በተወሰኑ ቀበሌዎች የሚኖሩ ዜጐችም ካለፈው ወር መጀመሪያ ጀምሮ የዕለት ጉርሳቸውንና ውሃ ከመንግሥትና በክልሉ ከሚሰሩ በጐ አድራጊ ድርጅቶች እየቀረበላቸው ነው ብለዋል፡፡ካለፈው ወር ጀምሮ የምግብ እርዳታ የሚቀርብላቸው ዜጐች በ2007 ዓ.ም በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከመንግሥት ምግብ ከሚቀርብላቸው 475 ሺህ የሚሆኑ የክልሉ ዜጐች መካከል አይደሉም ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers