• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ሐምሌ 19፣2008

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ክፍል ሶስት

በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር ጤናማ አመጋገብ እና ሳይንሳዊ ህጎች ሐምሌ 19፣2008
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በፀደቀው የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት ማንኛውም ተቀጣሪ ከቅጥር ውጭ በተለያዩ ሥራዎች የሚያገኘውን ገቢ ግብር የሚከፍልበት ከደሞዙ ጋር ተደምሮ በሚገኘው መጠን ልክ ይሆናል ተባለ

ተሻሽሎ በቀረበውና ዛሬ በፀደቀው የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት ማንኛውም ተቀጣሪ ከቅጥር ውጭ በተለያዩ ሥራዎች የሚያገኘውን ገቢ ግብር የሚከፍልበት ከደሞዙ ጋር ተደምሮ በሚገኘው መጠን ልክ ይሆናል ተባለ…

ለምሣሌ አንድ ተቀጣሪ በተቀጠረበት ድርጅት የ3 ሺህ ብር ደመወዝተኛ ቢሆን ከቅጥር ውጭ በትርፍ ጊዜው ሰርቶ 10 ሺህ ብር ቢያገኝ በወሩ መጨረሻ ከስራው ውጭ ያገኘው 10 ሺህ ብር ከመደበኛ ደሞዙ ጋር ይደመራል፡፡ ግብር ሲከፍልም ለዛ ወር የ13 ሺህ ብር ደሞዝተኛ የሚከፍለውን ያህል ግብር ከደሞዙ ላይ ይቆረጣል ማለት ነው፡፡ አዋጁን ለማፅደቅ ዛሬ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባደረገው ውይይት ይህ አሰራር ተቀጣሪውን የሚጎዳ ነው የሚል አስተያየት ተሰጥቶ ነበር፡፡

በተሻሻለው የገቢ ግብር መሠረት ከ585 ብር በታች የሚያገኝ ደሞዝተኛ ከግብር ነፃ ይሆናል፡፡ ከ586 ብር እስከ 1 ሺህ 650 ብር ደሞዝተኛ የሆነ ደግሞ ከደሞዙ 10 በመቶ ግብር ይከፍላል፡፡

ከ1 ሺህ 653 እስከ 3 ሺህ 145 ብር የሚከፈለው ደሞዝተኛ 15 በመቶ የገቢ ግብር በየወሩ ይቀረጥበታል፡፡

ከ5 ሺህ 196 እስከ 7 ሺህ 758 ደሞዝ የሚያገኝ ደግሞ 25 በመቶ ፣ ከ7 ሺህ 759 እስከ 10 ሺህ 833 ብር ደሞዝተኛ ደግሞ 30 በመቶ የገቢ ግብር የሚከፍል ሲሆን ከ10 ሺህ 833 ብር በላይ የሚያገኝ ደሞዝተኛ ከደሞዙ 35 በመቶ የሚሆነው የገቢ ግብር መክፈል የሚጠበቅበት ይሆናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ከተገቢው ጊዜ በላይ በሞጆ ደረቅ ወደብ ተቀምጠው የቆዩ ከ300 የሚበልጡ የኮንቴይነር ዕቃዎች መወረሳቸው ተሰማ

በሞጆ ደረቅ ወደብ በጊዜ ያልተነሱ የተባሉ 398 ኮንቴነር ንብረቶች በመንግሥት ተወረሱ ተባለ..የወደቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ታዬ ጫላ ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ ባለሃብቶች ከጅቡቲ አስገብተው በሞጆ ደረቅ ወደብ ያሳረፏቸውን ንብረቶች በ2 ወር ጊዜ ውስጥ ማስገባት ሲጠበቅባቸው ከዚያ በላይ እያቆዩ ወደቡ ከፍተኛ መጨናነቅ ገጥሞታል፡፡

መንግሥት 6 ወር የታገሳቸውንና 398 ኮንቴነር ንብረቶችንም በዚህም ምክንያት ወርሷል ብለዋል፡፡አሁንም በወደቡ 12 ሺህ 800 ኮንቴይነር ንብረቶች ያሉ ሲሆን ከ2 ወር ያለፉ ስላሉ ከመወረሳቸው በፊት በባለሃብቶች በጊዜ እንድታነሱ ሲሉ ሥራ አስኪያጁ አሳስበዋል፡፡ በሞጆ ደረቅ ወደብ በቀን 240 ኮንቴነሮች ወጪ ገቢ ቢሆኑም ከሚወጣው የሚገባው ብቻ እየጨመረ የወደብ መጨናነቁ ቀጥሏል ተብሏል፡፡

ወደቡ 14 ሺህ 900 ኮንቴነሮችን የማስተናገድ አቅም አለው ያሉት አቶ ታዬ 85 በመቶ ቦታው ለኮንቴነር ሲውል ቀሪው ቦታ ለማስተናገጃ የታሰበ ቢሆንም 90 በመቶ የሚሆንው ቦታ በኮንቴነር ተሞልቶ ስራችንን አክብዶብናል ብለዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

በአዲስ አበባ ከሳምንት በኋላ በሚወጣው የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ የ40/60 ተመዝጋቢዎችን አይመለከትም ተባለ

ከዚህ ቀደም በቤቶች ቆጠራ የተገኘ የማንም ያልሆኑ ባለቤት አልባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሚቀጥለው ሳምንት በሚወጣው እጣ ውስጥ አይካተቱም ተባለ…በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝግባችሁ ቤታችሁን እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ ቤት ፈላጊዎች አትጠብቁ በመጪው ሳምንት ይወጣል የተባለው ዕጣ እናንተንም አይመለከትም ተብላችኋል፡፡ ይሄንን የሰማነው ከአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊ ነው፡፡ ስማቸውን ያልነገሩን የጽ/ቤቱ አንድ የሥራ ኃላፊ ከአንድ ሳምንት በኋላ ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ከ39 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኞች ለማስተላለፍ ቀጠሮ እንደተያዘለት ነግረውናል፡፡

ከሳምንት በኋላ የሚተላለፉት ቤቶች የ20/80 እና የ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮግራሞች መሆናቸውን አውቀናል፡፡ ኃላፊውን ተመዝግበው ክፍያንም ከፍለው ቤታቸውን አየተጠባበቁ ያሉ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ፈላጊዎች በዕጣው ተካትተዋል ወይ ብለን ጠይቀን አለመካተታቸውን ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (5 አስተያየት)

የኢትዮጵያ የብረት የነፍስ ወከፍ ድርሻ ጨምሯል

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 24 የብረት አምራቾች ምርታቸውን ማምረት ጀምረዋል፡፡ አምራቾቹ ከዘመናዊ የቤት ቁሣቁስ እስከ ኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር ማምረት ላይ የተሰማሩ እንደሆኑ ሰምተናል፡፡ በግንባታ ላይ ቆይተው በዚህ አመት የኢንጂነሪንግና የብረት ምርቶችን ማምረት የጀመሩት 24 ኢንዱስትሪዎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር በተጨማሪ የነፍስ ወከፍ የብረት ፍጆታን ከፍ አድርገውታል ተብሏል፡፡

የብረታ ብረት ኢንዲስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ፊጤ በቀለ ለሸገር እንደተናገሩት በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አዳዲስ አምራቾች በዓመት 2 ሺህ 312 ቶን ዘመናዊ የቤት ቁሣቁሶችን ያመርታሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 19፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ኢትዮጰያ ከ11 የግብፅ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎች መድኃኒት ማስገባት ለጊዜው ማቆሟ ተሠማ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • በደቡብ ክልል ሰሌዳ አልባ ሞተር ሳይክሎች የትራፊክ አደጋ ስጋት እየሆኑ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የወደቁትን አንሱ የነድያን መርጃ ማህበር የለጋሾችን እጅ እየተጠባበቀ ነው፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የመድኃኒት አቅርቦት እና ፈንድ ኤጀንሲ ከዚህ በፊት ተፈጥሮ የነበረው የኤች.አይቪ ምርመራ አጋዥ ቁስ ቴስት ኪት እጥረት ስጋት አይኖርም አሁንም ከ130 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ  የመመርመሪያዎችን ግዢ አጠናቅቄያለሁ ብሏል፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • አራት የመንግሥት የንግድ ድርጅቶችን በስሩ የያዘው የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በይፋ ሥራ ጀምሬያለሁ አለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የአፍሪካ የንግድ አየር መንገዶችን ሊጠቅም የሚችል ያልተነካ እድል መኖሩ ተነገረ፡፡ (ምስክር አወል)
 • በአዲስ አበባ ከሳምንት በኋላ በሚወጣው የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ የ40/60 ተመዝጋቢዎችን አይመለከትም ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • የኢትዮጵያ የብረት የነፍስ ወከፍ ድርሻ ጨምሯል፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • ከተገቢው ጊዜ በላይ በሞጆ ደረቅ ወደብ ተቀምጠው የቆዩ ከ300 የሚበልጡ የኮንቴይነር ዕቃዎች መወረሳቸው ተሰማ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ዛሬ ፀደቀ፡፡ ከሐምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም አንስቶ በተገኘ ገቢም ላይ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ሐምሌ 5፣2008

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ክፍል አንድ

ከምሳ ሰዓት ጥዑም ሙዚቃዎች ጋር ነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ የምግብ ምርጫ በምን በምን ነገር ሊወሰን ይችላል በሚል ዙሪያ ሳይንሱ ምን እንደሚል ነግሮናል...
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ዛሬ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርቦ በሙሉ ድምፅ ፀደቀ

አዋጁ ከሐምሌ 1፣2008 ጀምሮ በተገኘ ገቢ ላይ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል፡፡ዛሬ የፀደቀውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማስፈፀም አዲስ መመሪያና ደንብ እንስኪወጣለት ድረስ በተሻረው ህግ መሠረት የወጡ ደንቦችና መመሪያዎች ተፈፃሚ እንደሚሆኑ ሰምተናል፡፡

የተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ በተበታተነ መልኩ ሲተገበሩ የነበሩ የግብር ህጐችን ወደ አንድ በማሰባሰብ እና ግብር የማይከፈልባቸው የገቢ ዓይነቶች ወደ ግብር መረብ በማስገባት ወጥና ፍትሐዊ የግብር አከፋፈል ሥርዓት እንዲኖር ይረዳል ተብሏል፡፡

የገቢ ግብር አዋጁ በመሻሻሉ መንግሥት በአመት ከተቀጣሪው ህብረተሰብ ያገኝ የነበረውን 3 ቢሊየን ብር ያሳጣዋል፡፡ ይሁን እና እስካሁን ግብር የማይከፈልባቸው የሥራ ዘርፎችም ወደ ግብር ከፋይነት በማስገባት ከተቀጣሪው የሚታጣውን ገንዘብ የሚያካክስ አንቀፅ በአዋጁ ታክሎበታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካንሰር በሽታ ሥር ሰዶ ችግር ከማስከተሉ በፊት ለቅድመ መከላከሉ ትኩረት እንዲሰጥ የጤና ምክርና ትምህርቱን ማስፋት ያሻል ተባለ

ካንሰር ለብዙዎቹ የኢትዮጵያ ዜጐች የጤና ብቻ ሳይሆን የስነ-ልቦና ችግር ነው ተባለ…ብዙዎቹ ስለ በሽታው ለቤተሰቦቻቸው እንኳ መናገሩን አይፈቅዱትም ተብሏል፡፡ በዚህም ምክንያት በሽታው ለስነ-ልቦና ችግር እንደሚዳርጋቸው ተነግሯል፡፡ ወሬውን የሰማነው ሁለተኛ ቀኑን በያዘውና በአስረኛው የማህፀን በር ጫፍ፣ የጡትና የፕሮስቴት ካንሰርን ከአፍሪካ እናጥፋ ኮንፈረንስ ላይ ነው፡፡ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ እንዳሉት በተለይ የአገራችን ሴቶች የካንሰርን ህመምና ሥነ-ልባናዊ ጫናውን ለብቻቸው ይሸከሙታል፡፡ በኢትዮጵያ በየአመቱ 66 ሺህ ሰዎች በካንሰር በሽታ እንደሚያዙ ወ/ሮ ሮማን ተናግረዋል፡፡

የበሽታው ስርጭት እንዲህ ከፍተኛ የሆነው በአገራችን ስለ ካንሰር በሽታ ያለው ዕውቀት አነስተኛ ስለሆነ ነውም ብለዋል፡፡ ለካንሰር በሽታ ህክምናውን በተሻለ ሁኔታ ይሰጣል የሚባለውና አንድ ለእናቱ ሆኖ በቆየው የጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ሰዎች አገልግሎቱን ለማግኘት ለወራት ወረፋን መጠበቅ፣ ለቀናትም መሰለፍ ግድ እንደሆነባቸው ቀዳማዊት እመቤቷ አንስተዋል፡፡ ብዙዎችም ተራቸው ሳይደርስ ይህችን አለም በሞት ይሰናበቷታል ብለዋል፡፡ ይህንን አሣዛኝ ሁኔታ ለመቀየር ህክምናውን በተለያዩ አካባቢዎች ለመስጠት እየተሰራ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ የቆዳ ኢንዱስትሪ አልሆንልህ ብሎታል..ከመስኩ የሚገኘውም ገቢ እያዘቀዘቀ ነው፡

የኢትዮጵያ የቆዳ ኢንዲስትሪ አሁንም ቁልቁለቱን ተያይዞታል ተባለ፡፡ ከውጪ ሃገር የሚጠበቀው ገቢ እየቀነሰ ነው፡፡ ከቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲቲዩት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ሰርጃቦ እንዳሉት ዘንድሮ በበጀት ዓመቱ 185 ሚሊዮን ዶላር ይገኛል ተብሎ ቢጠበቅም የተገኘው ግን 116 ሚሊዮን 353 ሺህ ዶላር ነው፡፡

አምና ከቆዳና የቆዳ ውጤቶች የውጪ ገበያ የተገኘው ገንዘብ ከዘንድሮው የበዛና 132 ሚሊዮን ዶላር ነበር ያሉት አቶ ብርሃኑ ዘንድሮ በውጪው ገበያ መጠነኛም ቢሆን ገበያ ያገኛው የፍየል ቆዳ ነው እርሱም ወደ ቻይና ፣ ሆንግኮንግ ፣ እንግሊዝ ፣ ታይዋን  እየተሸጠ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ክረምቱ ለቆዳ ምርትና የውጪ ገበያ ያልተስማማ መሆኑንም ከቆዳ ኢንዲስትሪ ልማት ኢንስቲቲዩት ሰምተናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ተዘግቶ የቆየው የረጲ የቆሻሻ መጣያ ሥፍራ ዳግም የአዲስ አበባን ቆሻሻ እየተረከበ ነው ተባለ

ዳግም ቆሻሻ እንዳይጣልበት ሆኖ ተዘግቷል የተባለው የረጲው ቆሼ እንደገና ቆሻሻ መቀበል ጀምሯል… በአዲስ አበባ ተከምሮ የሰነበተው ደረቅ ቆሻሻ ወደ ረጲ ተወስዶ እየተደፋ መሆኑን በፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የምክትል ሥራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ያረጋል ጋሻው ለሸገር ተናግረዋል፡፡ አዲስ አበባን ከላይ እስከ ታች አትረክርኳት የሰነበተው የደረቅ ቆሻሻ ክምር ያለዕረፍት እየተደፋ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ደረቅ ቆሻሻ ከያለበት ወጥቶ በመኪና ተጭኖ ሰንዳፋ ወዳለው የቆሻሻ ዘመናዊ መከተሪያ እንዲጣል የነበረው አሰራር ከተቋረጠ በኋላ ከተማዋ በቆሻሻ ታፍና ሰንብታለች፡፡ ጊዜያዊ ቆሻሻ መጣያ ቦታ ሲያፈላልግ የነበረው የፅዳት ኤጀንሲ ባለፈው ሣምንት በዋና ሥራ አስኪያጁ በኩል ለሸገር እንደተናገረው ቦሌና አቃቂ ላይ ወደተገነቡት ጊዜያዊ የቆሻሻ መጣያ ጣቢያዎች የተከማቸውን ቆሻሻ ለማጓጓዝ መወሰኑን ነግረናችኋል፡፡ የአዲስ አበባን ደረቅ ቆሻሻ ከዚህ ዓመት ታህሣስ ወር ጀምሮ ሲረከብ በነበረው የሰንዳፋ ላንድ ፊል አካባቢ ያሉ አርሶ አደሮች ቆሻሻው እንዳይመጣብን ሲሉ ማገዳቸውም ይታወሳል፡፡

አርሶ አደሮችና ሌሎች ነዋሪዎች የሚያቀርቡትን ጥያቄ መርምሮ ለመንግሥት የመፍትሄ ኃሣብ የሚያቀብል ኮሚቴ መቋቋሙንና ከነዋሪዎቹ ጋር ድርድር መጀመሩን በቀደመ ወሬያችን ነግረናችኋል፡፡ እንዳይከፈት ሆኖ የተዘጋውን ረጲ መልሶ ለቆሻሻ መጣያነት ማዋል የአካባቢውን ነዋሪ የበሽታ ስጋት ላይ እንደጣለው የሸገር አድማጮች ነግረውናል፡፡
 
ሕይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers