ሸገር ከእሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለሥልጣን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደሰማው ሚኒባስ ታክሲው ከፒያሳ ወደ ጥቁር አንበሳ ቁልቁል እየወረደ እንዳለ ቴዎድሮስ አደባባይ ሲደርስ መንገዱን ለቅቆ ለግንባታ የተቆፈረ ቦታን ጥሶ ገብቷል፡፡ አደጋው ማለዳ 1 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ገደማ መከሰቱንም ሸገር በአካባቢው ከነበሩ መንገደኞች ሰምቷል፡፡ አቶ ንጋቱ እስከ ረፋድ 3 ሰዓት ድረስ ተሽከርካሪው ከገባበት ወንዝ ውሰጥ ስድስት ሰዎችን በህይወት እና የሁለት ሰዎችን አስክሬን ማውጣት መቻላቸውን ነግረውን ነበር፡፡ ከቆይታ በኋላ አቶ ንጋቱን ጠይቀን እንደሰማነው በተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ የ4 ሰዎች (የ3 ሴትና የ1 ወንድ) አስክሬን ማውጣት ተችሏል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.
የሰማያዊ ፓርቲ ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አስቸኳይ ጉባዔ መጥራቱን ዛሬ ተናገረ፡፡የፓርቲው የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ብርሃኑ መሰለ ፓርቲያቸው የጠራውን ልዩ አስቸኳይ ጉባዔ አላማ በተመለከተ ሲናገሩ እንደሰማነው የምክር ቤቱን የመተማመኛ ደምፅ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባላት በማጣታቸው የተጠራ ጉባኤ መሆኑን ነው፡፡፡
የምክር ቤቱን የመተማመኛ ድምፅ ከýሬዝዳንቱ ውጪ ሌሎች የራ አስፈፃሚ አባላት በማጣታቸው ለተጠራው ጉባዔ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽኑን ኃላፊነት በተመለከተ አቶ ብርሃኑ እንዲህ ይላሉ፡፡የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ነሀሴ 8 ቀን 2008 ዓ.ም ባደረገው 4ተኛ አመት 6ተኛ መደበኛ ስብሰባው የፓርቲውን ሥራ አስፈፂሚ ኮሚቴ አባላትን የመተማመኛ ድምፅ መንፈጉንም ኃላፊው ነግረውናል፡፡
ከቀናት በኋላ በተጠራው ልዩና አስቸኳይ የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሚገኙ አባላት በፓርቲው ህግና ደንብ መሠረት የጉባኤው አባላት የሥልጣን ዘመን 3 አመት በመሆኑ የአሁኑ የመጨረሻቸው ጊዜያቸው ነው መባሉንም ከአቶ ብርሃኑ ሰምተናል፡፡የሰማያዊ ፓርቲ አሁንም እየተመራ ያለው በኢንጂነር ይልቃል ጌትነት መሆኑንም ኃላፊው ጨምረው ነግረውናል፡፡
የኔነህ ሲሣይ