• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በመጪው አመት የሚደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ ምንም አይነት ስህተት እንዳይኖር በዘመናዊ አሰራር የታገዘ ይሆናል

የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በመጭው አመት የኢትዮጵያን ህዝብ ለመቁጠር ቅድመ ዝግጅት እያደረግኩ ነው አለ…ከዚህ ቀደም በተካሄደው የህዝብ ቆጠራ ውጤት ምክንያት የተፈጠረው ጭቅጭቅና አለመግባባት እንዳይደገም በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

በኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ሳፊ ገመዲ ለሸገር እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት ለህዝብ ቆጠራው ውጤት ትክክለኛነት ይረዳ ዘንድ ባሳተላይት በመታገዝ ከ150 እስከ 200 ቤተሰብ የሚገኝባቸው ቦታዎች እየተለዩ የማካለል ሥራ እየተሰራ ነው፡፡ እስከ 200 ቤተሰብ የሚኖርባቸውን ቦታዎች ማካለሉ በመላው ኢትዮጵያ የሚሰራ ሲሆን እስከ አመቱ አጋማሽ ስራው ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በካርታ የማካለል ስራው ሲጠናቀቅም 145 ሺህ የቆጠራ ቦታዎች ይፈጠራሉ ተብሎ እንደሚገመት አቶ ሳፊ ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ መጠጥ ጠጥቶ ማሽከርከርን ለማስቀረት ይረዳል የተባለው ዘመቻ ዛሬ ተጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ ጠጥቶ ማሽከርከርን ለማስቀረት ቫይታል ስትራቴጂ ከተሰኘው አለም አቀፍ ተቋም ጋር በጋራ በመሆን የታቀደው ዘመቻ ዛሬ ይፋ ሆነ...ይህን የሰማነው ዛሬ የዘመቻውን መጀመር አስመልክቶ በጌት ፋም ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ተገኝተን ነው፡፡

በቫይታል ስትራቴጂ እና በብሉምበርግ ፊላንትሮፒስ ኢኒሼቲቭ ፎር ግሎባል ሮድ ሴፍቲ ፕሮግራም ትብብር የተዘጋጀው የፀረ ጠጥቶ ማሽከርከር የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ጠጥቶ ማሽከርከር በአሽከርካሪው፣ በተጐጂው አካል ላይ እና የሁለቱንም ወገን ቤተሰቦች ላይ የሚያስከትላቸው ችግሮች ላይ ትኩረቱን አድርጐ ይሰራል ተብሏል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ ላይ አደጋዎች ሞትን በማስከተል ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው እና ከነዚህም ውስጥ ጠጥቶ በማሽከርከር የሚደርሱት አብላጫውን እንደሚይዙ ተነግሯል፡፡ ችግሩም በአጭሩ ካልተቋጨ ስፋቱ እየጨመረ እንደሚሄድ በስጋት ተቀምጧል፡፡

በመግለጫው የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው እና የአቤት ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር በዘመቻው ላይ ድጋፋቸውን በማድረግ በጋራ የሚሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ  ዛሬ የሚጀመረው የፀረ-ጠጥቶ ማሽከርከር ዘመቻ ለውጥ እንዲያመጣና ግንዛቤ እንዲፈጥር በተለይ በመገናኛ ብዙሃን በኩል ብዙ ሥራዎች እንዲሰሩበትና ህግ የማስከበሩንም ሥራ በማጠናከር የከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ድጋፍ ያደርጋል ሲሉ ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

አዲስ አበባም በቅርቡ የአልኮል መጠጥን በትንፋሽ መለየት የሚያስችሉ መሣሪያዎችን ወደ ሀገር ቤት እንደሚገቡና በተጨባጭ ጠጥቶ የማሽከርከር አደጋ በሚደጋገምባቸው በከተማዋ ያሉ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚደረግም ሰምተናል፡፡

ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 13፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአዲስ አበባ መጠጥ ጠጥቶ ማሽከርከርን ለማስቀረት ይረዳል የተባለው ዘመቻ ዛሬ ተጀመረ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • መንግሥት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የቤት ችግርን በኮንዶሚኒየም ፕሮግራም መፍታት አልችልም አለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • በመጪው አመት የሚደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ ምንም አይነት ስህተት እንዳይኖር በዘመናዊ አሰራር የታገዘ ይሆናል ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • በቀን እስከ አምስት ሺህ የሚደርሱ በጎችና ፍየሎች እርድ ማከናወን የሚችል ቄራ ግንባታ ወደ መጠናቀቁ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በ2009 ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች ምደባ ትናንት ምሽት ላይ መታወቅ ጀመረ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የቆዳ ገበያ ተፎካካሪ ለመሆን ለጥራት ትኩረት መስጠት አለባት ሲሉ አንድ ምሁር ተናገሩ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የህይወት ዘመን የመሪነት ስኬት ሽልማት ስነ-ሥርዓት ትናንት ምሽት ተከናውኗል፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ዘንድሮ ከ7 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በየኮሌጆቻቸውና ኢንስቲቲዩቶቻቸው ምድብ ወጥቶላቸው በጋራ እንዲወያዩና የውይይታቸውን ጭምቅ ኃሣብ እንዲያቀርቡ የቡድን ሥራ ተሰጥቷቸው የነበሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን እንደ መሰንበቻው ሁሉ ዛሬም ከመንግስት ተወካዩ አቶ ካሣ ተክለብርሀን ጋር ተገናኝተዋል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ምሁራኑ የቀረበላቸውን የመንግሥት ሰነድ መነሻ አድርገው የራሳቸውን አስተያይ አክለው ነፃ ኃሣባቸውን ጠቅልለው ማቅረባቸውን የጉባዔው መሪ አቶ ካሣ ተክለብርሀን ተናግረዋል፡፡ ምሁራኑን ለማነጋገር አንደሞከርነው በየቡድን አባት ሆነው ፍሬ ነጥቦች ናቸው ያሏቸውን  በትላንቱ ውይይታቸው አንስተዋል፡፡ ከነጥቦቹ መካከል የመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ የምናጠፋው ውይይት ቀርቶ ነባራዊውን የሀገሪሏን ሁኔታ እያነሣን በደንብ እንከራከርበት የሚል ይገኝበታል፡፡ ጥልቅ ተሃድሶና የስርዓት ግምገማ ላይ ነኝ የሚለው ፓርቲ ነባራዊውን ሁኔታ ነክቶታል ወይ የሚል ጥያቄም ነበራቸው፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ሚዛን ያልጠበቀ የኑሮ ልዩነት ለማጥበብ እንዲሁም የሀብት ይዞታ የበላይነት በተመለከተ ሰፋ አድርገን ትርጉም ባለው መንገድ እንነጋገርበት ሲሉም ኃሣባቸውን ለአወያዩ አቅርበዋል፡፡
 
ከብሔር ፖለቲካ ስርዓት ጋር ተያይዞ የሚመጣ አደጋም ይታየናል የሚሉት እነዚህ የዩኒቨርስቲው ምሁራን ብሔርን መሠረት ያላደረገ የሀገር አስተዳደር ዘይቤ ዕይታ ቢኖር የሚል ኃሣባቸውን አጉልተው ለመወያያነት አቅርበዋል፡፡ ምሁራኑ ህገ-መንግሥቱ እንዲሻሻልም ጠይቀዋል፡፡ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ተከታታይ የሊቃውንት ጉባዔ ማካሄድ የበለጠ ለውጥ እንደሚያመጣ እናምንበታለንም ይላሉ፡፡ የጉባዔው መሪ እነዚህንና በምሁራኑ የተነሱ ሌሎች ኃሣቦችንና ጥያቄዎችን ጠቅለል አድርገው ትንታኔ ሲሰጡ አርፍደዋል፡፡ ምሁራኑ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ እንከራከር ብለው ፅኑ ፍላጐት ማሣየታቸውን አድንቀው አመስግነዋቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መንግስት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር የሚያደርገውን ውይይት ቀጥሏል

በኮሌጆችና ኢንስቲቲዩቶች ምድብ ወጥቶላቸው በጋራ እንዲወያዩና የውይይታቸውን ጭምቅ ሃሳብ እንዲያቀርቡ የቡድን ስራ ተሰጥቷቸው የነበሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ዛሬም ከመንግስት ተወካዩ አቶ ካሳ ተክለብርሃን ጋር ተገናኝተዋል፡፡ ምሁራኑ የቀረበላቸው የመንግስት ሰነድ መነሻ አድርገው የራሳቸውን አተያይ ጨምረው ነፃ ሃሳባቸውን ጠቅልለው መናገራቸውን የጉባኤው መሪ አቶ ካሳ ተክለብርሃን ተናግረዋል፡፡

ምሁራኑ ባነሷቸው ጥያቄዎች ላይ ሃሳባቸውን ሲሰጡ ያረፈዱት አቶ ካሳ ለአብዛኞቹ ጥያቄዎች የሰጡት መልስ ምሁራኑም ሆኑ የሚመለከታቸው ጥልቅ ጥናት እንዲያደርጉበት የሚጋብዝ መሆኑን ነው፡፡ የቦርድ ሰብሳቢው በጉባኤው ሲናገሩ በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚታዩ ችግሮች የማይካዱ ቢሆኑም በመንግስት በኩል ለችግሮቹ መፍትሄ ይሆናሉ ተብለው የተሰሩ ስራዎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ሰብሳቢው ጠቅለል ያሉ ችግሮችን እያነሱ ጥናት ያስፈልጋቸዋል በሚል አልፈዋቸዋል፡፡ ሸገር የዩኒቨርስቲ ምሁራኑን ላቀረቧቸው ጥያቄዎችና ሃሳቦች በቂ መልስ ተሰጥቷቸው እንደሆነ ለመጠየቅ ሞክሯል፡፡ያነጋገርናቸው ምሁራን እንደሚሉት በትናንትናው የቡድን ውይይቶች ወቅታዊውን የሃገራቱን ጉዳይ ከምሁራዊ አስተያየቶች ጋር በማገናዘብ እንዳቀረቡና ለአብዛኞቹ ጥያቄዎቻቸውም መልስ ሳይሆን የለመዷቸው ሃሳቦች እንዲሰሙና ከሁነኛ መልስ ይልቅ ጥናት ይመልሳቸው የተባሉ ነጥቦች መብዛታቸውን አልሸሸጉም፡፡

አቶ ካሳ፣ ምሁራኑ ከመማር ማስተማር ስራው ይልቅ በወቅታዊው ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ለመወያየት ያላቸውን ፅኑ ፍላጎት አድንቀው ምስጋናም ቸረዋቸዋል፡፡ ምሁራኑ ካቀረቧቸው ሃሳቦች መካከል ነባራዊው የሀገሪቱ ችግሮች ላይ እንከራከር፤ ሀገር ውስጥ የሚታይ ሰፊ የኢኮኖሚ ልዩነት ላይ መወያየት እንፈልጋለን የሚሉ ይገኙበታል፡፡

የብሄራዊ ፖለቲካው ጉዳይ ጠለቅ ብሎ እንዲነሳም ጠይቀዋል፡፡ የሀገሪቱ የሃብት ድርሻ የበላይነት የመወያያ ርዕስ እንዲሆን ጥያቄያቸውን ያቀረቡም ነበሩ፡፡ ውይይቱ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ምሁራኑም በተሰጡት መልሶች ላይ ሃሳባቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜዎቹ ግጭቶች ስለጠፋው የሰው ህይወትና የንብረት ውድመት እንዲሁም ዜጎች ለእስር የተዳረጉበትን ሁኔታ በልዩ ትኩረት እከታተላለሁ አለ

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜዎቹ ግጭቶች ስለጠፋው የሰው ህይወትና የንብረት ውድመት እንዲሁም ዜጎች ለእስር ለተዳረጉበት ሁኔታ በልዩ ትኩረት እከታተላለሁ አለ…ለጠፋው የሰዎች ሕይወትም ከልብ ማዘኑን በኢትዮጵያ የህብረቱ አምባሳደር ተናግረዋል፡፡

በአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ አምባሳደሯ ቻንታን ሀብርቻት የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ ቢውል ምርጥ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡በመሆኑም አለመግባባቶች ሲፈጠሩ መንግስት ራሱን ከዜጎች ጋር ለመነጋገር ማዘጋጀት ነበረበት መፍትሄውም ኃይልን ከመጠቀም ይልቅ ጥያቄዎቻችሁ ምንድን ናቸው፣ ምን ላድርግ ማለት ነበረበት ብለዋል፡፡ የፖለቲካ ልዩነቶች ቢኖሩም እንኳን መንግስት ጥያቄዎችን ለማዳመጥ ጆሮውን ክፍት ማድረግ እንደነበረበት አክለው ጠቁመዋል፡፡መንግስት በቅርብ ጊዜ አደርገዋለሁ ብሎ ቃል የገባው ምን ላይ እንዳደረሰው እና የሚያደርገውን ለውጥ እንጠብቃለን ብለዋል፡፡

በስደተኞች ጉዳይም ሁለት አይነት እቅዶችን ማስቀመጣቸው ጠቅሰዋል፡፡በአምባሳደሯ የቅርብ ጊዜ እና የረጅም ጊዜ እቅድ ተብለው ከተቀመጡት መካከል ወደ አውሮፓ መዳረሻቸውን አድርገው በስደት የሚሞቱ አፍሪካውያንም በሜዲትራንያን ባህር ከመስጠም መታደግ የአጭር ጊዜ ዕቅድ ሲሆን የረጅም ጊዜ እቅዳቸው ደግሞ እስከ መንደር ድረስ በመዝለቅ የስራ ዕድል በመፍጠር ወደ ስደት እንዳያማትሩ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም ከአፍሪካ 5 አገሮች የተመረጡ ሲሆን ኒጀር፣ ሴኔጋል፣ ናይጄሪያና ማሊን ተከትላ ኢትዮጵያም ተቀምጣለች፡፡ ህብረቱ ጋዜጠኞችን ዛሬ በደሳለኝ ሆቴል ጠርቶ ስለ ሰላምና ፀጥታና ስደትን ስለመቆጣጠር ሽብርተኝነትን ስለመከላከል፣ ስለኢንቨስትመንትና የአየር ንብረት ለውጥ እየሰራ ስላለው ስራ እና ስለወደፊት እቁዱም መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ምስክር አወል
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 11፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜዎቹ ግጭቶች ስለጠፋው የሰው ህይወትና የንብረት ውድመት እንዲሁም ዜጎች ለእስር የተዳረጉበትን ሁኔታ በልዩ ትኩረት እከታተላለሁ አለ፡፡ (ምስክር አወል)
 • አሜሪካ በማንዴላ ዋሽንግተን ፌሎውሺፕ ለምትሰጠው ነፃ የትምህርት እድል የተመረጡ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ዝርዝር ይፋ ይሆናል ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • መንግስት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር የሚያደርገውን ውይይት ቀጥሏል፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • በሰሜን ሸዋ ቅንብቢት በሕዝብ መጓጓጓዣ አውቶብስ ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ ብዙ ተሳፋሪዎች የአካል ጉዳት ገጠማቸው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የዓየር ሁኔታ ተከታታዩ መስሪያ ቤት 3ኛውን ብክለት ጠቋሚ መሳሪያ ልተክል ነው አለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአፍሪካ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች 16ኛ ወጣ ብሎ መፈንደቅ አይገባም

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአፍሪካ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች 16ኛ ወጣ ብሎ መፈንደቅ አይገባም፤ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ይህንን ብስራት ብለው በየኢሜይላችን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ልከውልናል፤ ጉዳዩ ግን የሚያኩራራ አልነበረም ይላሉ ትላንት መንግሥት እንወያይ ብሎ ከጠራቸው የዩኒቨርስቲው ምሁራን አንዱ…

16ኛነት ለቀድሞው የቀዳማዊ ሀ/ስላሴ ዩኒቨርስቲ ለ60 ዓመቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሚገባወም፣ የሚመጥነውም አለመሆኑን ይናገራሉ፡፡

መንግሥት ከምሁራን ጋር ለመነጋገር ቀን ቆርጦ በጀት መድቦ ውይይት የጀመረው ትላንት ሲሆን፤ ለመወያያና ኃሳብ ማጫሪያነት ያገለግላሉ ተብለው በመንግሥት ከተሰናዱት ሰነዶች ይልቅ ወጣ ያሉና የሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች የነካኩ አስተያየቶች ነበሩ ከምሁራኑ አንደበት የተደመጡት፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተዳዳሪዎችና በቦርድ ሰብሣቢው አቶ ካሣ ተክለብርሃን የተመራው ይህ ጉባዔ የኢትዮጵያ ትምህርት ከኢህአዴግ ጋር ለ25 ዓመታት እንዴት እንደተጓዘና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ አበርክቶ ምን እንደሚመስል አሃዛዊ ማስረጃዎችን እያጣቀሰ የቀረበበት ነበር፡፡

የዩኒቨርስቲው ምሁራን የቀረበው ፅሁፍ ደረጃቸውን ያላከበረና ዝቅ ያለ በመሆኑ ተችተውታል፡፡

እንደነሱ ኃሳብ ከሆነ ስለ ሀገሪቱ ትምህርት የአሁን ጊዜ ሁኔታ ለመናገር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያለው ዩኔስኮ አልያም ትምህርትን ስራዬ ብለው የሚመራመሩ ሊቃውንት እያሉ ከዚህ ራቅ ያሉት የዩኒቨርስቲው ኃላፊ ማቅረባቸው እንዳላስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም መስከረም 10፣2009

ክፍል አስር

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር የስታርች እና ፋይበር ምግቦች ስትሮክ እና የስኳር ህመም ላለባቸው
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢሬቻ ባህል በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ተብሎ ሊመዘገብ ነው ተባለ

የዘንድሮው የኢሬቻ በአል በመስከረም 22 ሲከበር አመታዊ በአሉ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት የባህልና የሣይንስ ማዕከል ዩኔስኮ በአለም ቅርስነት ይመዘገባል ተባለ…ሸገር ወሬውን የሰማው ከአባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ሮቢ የቱለማ አባ ገዳና የኦሮሚያ አባገዳዎች ሰብሣቢ ነው፡፡

የኦሮሞ የገዳ ስርአት በማይዳሰስ ቅርስነት ዘንድሮ ኢሬቻን ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአባ ገዳዎቹ ሰብሣቢ ነግረውናል፡፡ ከወራት በፊት በኦሮሞ የገዳ ስርአት የሚከበረው የኢሬቻ በአልን በተመለከተ የመንግሥታቱ ድርጅት ከዩኔስኮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል ያሉት አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ሮቢ ከቀናት በኋላ የሚከበረው የኢሬቻ በአል በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት ይመዘገባል የሚል ሙሉ እምነት አለን ብለዋል፡፡

የኢሬቻ በአል በየአመቱ መስከረም 22 ቀን በታላቅ ድምቀት በቢሾፍቱ ሲከበር በርካታ አመታትን ማስቆጠሩ ይታወቃል፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ረቂቅ የንግድ ህጉ የሌላ ነጋዴን የንግድ ዋጋ ለማወቅ መሰለል ህገ-ወጥነት ነው አለ

አዲሱ ረቂቅ የንግድ ህግ ሚስጥራዊ የሆኑ የሌላ ነጋዴ የንግድ መረጃዎችን በሰራተኞች አማካይነት ለማግኘት መሞከርንም በህገ-ወጥነት ይፈርጃል ተባለ…ወሬውን የሰማነው ረቂቅ ህጉን አስመልክቶ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዛሬ በኢሊሌ ሆቴል ባዘጋጀው የግሉ ዘርፍ የግብአት ማሰባሰቢያ ዐውደ ጥናት ላይ ተገኝተን ነው፡፡ ረቂቁ የተዘጋጀው በ1952 ዓ.ም የወጣውን የንግድ ህግ እንዲተካ ታስቦ ነው ተብሏል፡፡የቀደመው ህግ አሁን ካሉ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር የተጣጣሙ ድንጋጌዎች እንደሚጐሉት ተነግሯል፡፡

ፈጣን ከሆነው የንግድ እና ኢንቨስትመንት እድገት ጋርም በተገናኘ በህጉ መመለስ ያለባቸው ጉዳዮች ስላሉ ረቂቁ እንደተዘጋጀ በአውደ ጥናቱ ላይ ሲነገር ሰምተናል፡፡ ረቂቁ ለንግድ ማህበራትና ባንኮች አደራጃጀትም አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ የሚያበጅ ነው ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ የአለም አቀፉ የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለጀመረችው ጥረትም የንግድ ህጉ መሻሻል አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን በአውደ ጥናቱ ላይ ሲነገር ሰምተናል፡፡
 
ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers