• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ከዱባይ ወደ አዲስ አበባ ሲበር የነበረና ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን ተከሰከሰ በሚል የተሰራጨው መረጃ ሃሰት መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ እወቁልኝ አለ

አየር መንገዱ ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ ከዱባይ ወደ አዲስ አበባ የበረራ ፕሮግራም የነበረው ሲሆን 150 ተሳፋሪዎችን ይዞ በሰላም አዲስ አበባ ቦሌ አየር መንገድ መድረሱን ሰምተናል፡፡

ሰኞ ከሌሊቱ 6 ሰዓት ከ55 ደቂቃ ከዱባይ የተነሳው 787 AOO ተብሎ በሚታወቀው የአየር መንገዱ አውሮፕላን ከጥዋቱ 1 ሰዓት ከ32 ደቂቃ ሲሆን በሰላም ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፉን በአየር መንገዱ የኮርፕሬሽን ኮሙኒኬሽን ማኔጀር የሆኑት ወ/ሮ ሃና አጥናፉ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ዛሬ የተሰራጨው የሃሰት መረጃም ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር መንገድ ውስጥ ለልምምድ የተሰራን የአደጋ መከላከል ሥራ የሚያሳየውን የቪዲዮ ምስል ተጠቅመው የተሰራጨ መሆኑን ወ/ሮ ሃና ተናግረዋል፡፡

ቪዲዮው የተቀረፀው አደጋ ቢከሰት በምን ያህል ፍጥነት የአደጋውን ተጐጂዎች ሆስፒታል መውሰድ ይቻላል የሚለውን ለመፈተሽና ለልምምድ እንደነበር የተናገሩት ወ/ሮ ሃና መረጃውን እውነት ለማስመሰል ያንን ቪዲዮ መጠቀማቸው አየር መንገዱን አሳዝኗል ብለዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ባለፉት 3 ወራት በ2 ነጥብ 46 ቢሊዮን ብር የተለያዩ ንብረቶችን ገዝቶ ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ማቅረቡን የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ተናገረ

ከተፈፀመው ግዥ ትልቅ ወጭ የተደረገውም ለመለስ ዜናዊ ሊደርሺፕ አካዳሚ የሚውል የህንፃ ግንባታ ግዥ ሲሆን 1 ነጥብ 39 ቢሊዮን ብር እንደወጣበት ሰምተናል፡፡

ይህም ማለት የመለስ ዜናዊ ሊደርሺፕ አካዳሚ ህንፃን በ1 ነጥብ 39 ቢሊዮን ብር ለመገንባት ጨረታውን ላሸነፈ የሥራ ተቋራጭ ስራው ተሰጥቷል ማለት ነው፡፡

ለፌድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚሆኑ ሁለት ቪ-8 ተሽከርካሪዎችም በ10 ነጥብ 84 ሚሊዮን ብር ግዥ መፈፀሙን ሰምተናል፡፡

ለቁጠባ ቤቶች ግንባታ ይውል ዘንድም ከ783 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የአርማታ ብረት ግዥ ተፈፅሟል፤ የአርማታ ብረቶችንም የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር እንደሚረከብ አገልግሎቱ ለሸገር ተናግሯል፡፡

ለመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች በሩብ አመቱ ከተፈፀመው 2 ነጥብ 46 ቢሊዮን ብር ግዥ መካከል ለተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚሆኑ የማጣቀሻ መፅሐፎችና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዓለም የጤና መስፈርት ላኪ ኢንስቲትዩት የ2015 የሀገራትን የጤና ሚዛን መስፈርት ጥናት ይፋ ማድረጉና በሪፖርቱ መሠረትም በኢትዮጵያ በወሊድ ጊዜ የነበረው የእናቶች የሞት መጠን መቀነሱ ተሠማ

በአለም ላይ በ130 ሀገራት በተደረገውና 1 ሺህ 800 የጤና ባለሙያዎች ባቀረቡት የምርምር ወረቀታቸው መሠረት ለጤና መታወክ መንስኤና ምክንያቶች ናቸው የተባሉ ነጥቦች በመለየት የየሀገራቱ ውጤት በጤና ጥናት ኢንስቲቲዩቱ በኩል ተነግሯል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፉት አመተት የነበረው የእናቶች የወሊድ ጊዜ የሞት መጠን ከ100 ሺ እናቶች 796 ነጥብ 7 መሆኑን የተናገረው ሪፖርቱ በ2015 እንደ ጐርጐሮሣዊያን አቆጣጠር ወደ 409 ነጥብ 8 ዝቅ ማለቱን ተናግሯል፡

ከ5 አመት ዕድሜያቸው በፊት ህይወታቸውን በሞት ይነጠቁ ከነበሩ ከ1 ሺ ህፃናት መሀከል በጥናት ሪፖርቱ መሠረት 189 ነጥብ 66 የነበረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ግን ቁጥሩ ወደ 60 ነጥብ 27 ዝቅ ማለቱን ሪፖርቱ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ በ2015 ለሞት ዋነኛው መንስኤና ምክንያት ተብለው ከተዘረዘሩት መሀከል ተቅማጥ፣ ኢንፌክሽንና የመተንፈሻ አካላት ቀዳሚዎቹ መሆናቸውን ከሪፖርቱ ተመልክተናል፡፡

በአለም የጤና መስፈርት ኢንስቲትዮት ጥናት መሠረት በኢትዮጵያ ቀዳሚዎቹ የጤና እውክ ተብለው ከተዘረዘሩት በተጨማሪ በመለስተኛ ደረጃ የበሽታ አምጪ ምክንያቶች ናቸው የተባሉም ተቀምጠዋል፡፡

በኢትዮጵያ በወሊድ ጊዜ ይደርስ የነበረው ከእናቶችና ከጨቅላ ህፃናት ሞት በተጨማሪ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑት ህፃናት ሞት መቀነስ ዋናው ምክንያት በጤና ተቋማት የሚደረገው የእናቶች የወሊድ አገልግሎት መብዛቱ ነው ሲልም የአለም አቀፉ የጤና መስፈርት ኢንስቲትዩት መናገሩ ተሰምቷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ ያለው የእናቶችና የህፃናት ሞት የቀነሰው በቅድመ መከላከል በተዘረጋው አሰራር መሠረት ነውም ብሏል፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ጥራት ያለው ነዳጅ ያቀርባሉ የተባሉ 60 የማደያ ጣቢያዎች በመንግሥት ሊገነቡ መሆናቸውን ሰማን

በአዲስ አበባ 10ሩም ክ/ከተሞች በመንግሥት ይገነባሉ የተባሉትን የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች በጊዜያዊነት እንዲያስተዳድርና የግንባታ ስራውን እንዲከታተል ለነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አደራ ተሰጥቶታል፡፡አሁን በአዲስ አበባ ከሚገነቡ 60 የማደያ ጣቢያዎች በተጨማሪ ወደፊት በመላ ሀገሪቱ የሚሰሩ ማደያዎች እንደሚኖሩ ሰምተናል፡፡

በመንግሥት ባለቤትነት ለሚገነቡ የነዳጅ ማደያዎች እስካሁን 5 ክ/ከተሞች ቦታ አዘጋጅተው ማሰረከባቸው ተወርቷል፡፡በነዳጅ ማደያ ሥራ ላይ በግላቸው ተሰማርተው ከሚገኙ ድርጅቶች መካከል ጥራቱ የተጓደለና የተደባለቀ ነዳጅ በማቅረብ የሚወቀሱ ድርጅቶች መኖራቸውን የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ይናገራል፡፡

ይህንን ችግር ይቀርፋሉ ጥራቱ የተረጋገጠ ነዳጅ በማቅረብ የተሽከርካሪዎችን ብልሽት በመቀነስ እድሜያቸውን ያረዝማሉ የተባሉ የነዳጅ ማደያዎች ናቸው በመንግሥት የሚገነቡት ተብሏል፡፡ በየወሩ መገባደጃ በነዳጅ ማደያዎች የሚያጋጥመውን የነዳጅ ዕጥረትና ወረፋ ችግር ለመቀነስ አዳዲሶቹ ጣቢያዎች መፍትሄ ይዘዋል ተብሏል፡፡

በተያያዘ ወሬ የማዕድን ነዳጅና ባዬፊውል ኮርፖሬሽን የነዳጅ ዕደላ የሚሰጥባቸውን ጣቢያዎች ለመገንባት ዕቅድ እንዳለው የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ ሰዒድ ኮርፖሬሽኑ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ሲናገሩ ሰምተናል፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 2፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የአፍሪካ የድንችና የስኳር ድንች ዐውደ ጥናት በኢትዮጵያ እየተደረገ ነው፡፡ (ተኅቦንጉሴ)
 • ዘንድሮ በአዲስ አበባ ከተማ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ወስደው በሙያና ቴክኒክ ዘርፍ ገብተው የሚሰለጥኑት ሰልጣኞች ቁጥራቸው ከ35ሺ በላይ ነው ተባለ፡፡ ተማሪዎች የተወሰኑ ማሰልጠኛ ተቋሞች ላይ ትኩረት ስላደረጉባቸው መጨናነቅ መፈጠሩንም ሰምተናል፡፡ (ምሥክርአወል)
 • የጌጣ ጌጥ ማዕድናትን አስውቦ እና ቅርፅ አስይዞ ለመሸጥ ዝጅግቱ ተጠናቋል ተባለ፡፡ (ዮሐንስየኋላወርቅ)
 • በደቡብ አፍሪካ የተካሄደው የዱር እንስሳት መታደጊያ ስብሰባ ህገ-ወጥ የእንስሳትና አካሎቻቸው አዘዋዋሪዎችን ከድርጊታቸው የሚገታ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • በአዲስ አበባ ጥራቱ የተጠበቀ ነዳጅ የሚያቀርቡ 60 አዳዲስ ማደያዎች ሊገነቡ ነው ተባለ፡፡ (ሕይወትፍሬስብሃት)
 • ባለፈው ሩብ ዓመት ለመንግሥታዊ የግዢ ክንውን ከ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ተሠማ፡፡ (ትዕግስትዘሪሁን)
 • በኢትዮጵያ በወሊድ ወቅት የሚደርስ የእናቶች የሞት መጠን እየቀነሰ መምጣቱን ዓለም አቀፍ ጥናት አሣየ፡፡ (የኔነህሲሣይ)
 • በአዲስ አበባ ተሰራጭቶ የቆየው የአተት በሽታ ስጋት ቢወገድም ተመልሶ እንዳያገረሽ ጥንቃቄ መለየት እንደማይገባው ምክር ተሰጠ፡፡ (መሠረት በዙ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ኮማንድ ፖስት

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስቱ የሕዝቦችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን ፅሁፍ ማዘጋጀት፣ ማተምና ማሰራጨት፣ ትዕይንትን ማሳየት፣ በምልክት መግለፅ ወይም መልዕክትን በማንኛውም መንገድ ለህዝብ ይፋ ማድረግ ሊከለክል እንደሚችል የተናገሩት ዋና አቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አንባዬ ናቸው…

ማናቸውንም የመገናኛ ዘዴዎች እንዲዘጉ ማድረግ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል፤ በእነዚያ በተለዩ ቦታዎች፡፡ በሦስተኛ ደረጃ የህዝቦችና የዜጐችን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ሲባል ስብሰባና ሰልፍ የማድረግ ጉዳዮችን ሊያግድ ይችላል፤ መደራጀትና በቡድን መንቀሣቀስን ሊከለክል የሚችልበት ሁኔታም በአዋጁ ውስጥ ተቀምጧል፡፡

አቶ ጌታቸው ይህን ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በህገ-መንግሥቱ መሠረት የተዘጋጀ መሆኑን በተናገሩ ጊዜ ነው፡፡የህዝብን ሰላምና ፀጥታ በማደፍረስ ተግባር ላይ ተሣትፏል ተብሎ የሚጠረጠር ማንኛውም ሰው ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዝ ይቻላል፡፡ በእነዚህ ቦታዎች ላይ የተጠረጠረ ሰው ካለ የፍርድ ቤት መያዣ ትዕዛዝ ይምጣ እንደዚህ ይደረግ ተብሎ ሊጠየቅ አይችልም፤ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ሥር ለማድረግ ይቻላል፤ እያጣራና እየመረመረም እያስተማረ መልቀቅ የሚችልበት ሁኔታም ክፍት ነው፡፡ ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝ ደግሞ በመደበኛው ህግም ተጠያቂ ማድረግ የሚችልባቸው ሁኔታዎችም ሊፈፅም የሚችልባቸው ሁኔታዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ቼሻየር ሰርቪስ ኢትዮጵያ ከፌሲንግ አፍሪካ ጋር በተመባበር ከእንግሊዝ ሀገር ያስመጣቸው የቀዶ ጥገና ሀኪሞች ዛሬ በኮሪያ ሆስፒታል ህክምና መስጠት ጀምረዋል ተባለ

ቼሻየር ሰርቪስ ኢትዮጵያ ከፌሲንግ አፍሪካ ጋር በተመባበር ከእንግሊዝ ሀገር ያስመጣቸው የቀዶ ጥገና ሀኪሞች ዛሬ በኮሪያ ሆስፒታል ህክምና መስጠት ጀምረዋል ተባለ፡፡የቼሻየር ሥራ አስኪያጅ አቶ ገ/መድህን በቀለ ለሸገር ሲናገሩ እንግሊዛዊያኑ ሀኪሞች ለ10 ቀን የፊት ቀዶ ጥገና ህክምና ይሰጣሉ፤ በእሳትና በተለያዩ አደጋዎች የፊት ገፃቸው የተበላሸ ሰዎች ወደ ኮሪያ ሆስፒታል እየሄዳችሁ ሃኪሞቹ ያይዋችኋል ብለዋል፡፡

እስካሁን ህክምናውን ፍለጋ 50 ሰዎች ተመዝግበዋል ያሉት አቶ ገ/መድህን ህክምናው በመናገሻ የቼሻየር ማገገሚያ ይሰጣል ተብሎ የነበረ ሲሆን በወቅቱ ሁኔታ ወደ ኮሪያ ሆስፒታል እንዲዘዋወር ተደርጓል ሲሉም ነግረውናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ኢትዮጵያ እና ቶጐ በተለያዩ መሥኮች በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸውን ሥምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና የቶጐ ፕሬዝዳንት ፋውሬ ና ሲንጊቤ በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ዛሬ የሁለትዬሽ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ሁለቱ ሀገራት መሠረታዊ በተባሉ ሦስት ነጥቦች ላይ ስምምነት ማድረጋቸውን ሰምተናል፡፡በባህል፣ በቱሪዝምና በግብርና መስኮች መተባበር የሚያስችል የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ ለመመስረት መፈራረማቸውንም መሪዎቹ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

በአፍሪካ በሚነሱ ፖለቲካዊ ነክ ግጭቶች መፍትሄ ለማስገኘት ሁለቱ ሀገሮች ለአፍሪካ ህብረት ድጋፍ ያደርጋሉ መባሉንም ሰምተናል፡፡የቶጐና የኢትዮጵያ መሪዎች የተስማሙባቸውን የባህልና ቱሪዝም ዘርፎች ስምምነቶችን በኢትዮጵያ ወገን ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ሲፈርሙ በጋራ ኮሚቴው ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድኤታው አምባሣደር ታዬ አፅቀስላሴ እና የቶጐ አቻቸው ተፈራርመዋል፡፡

የቶጐ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ቆይታቸው በነገው እለት የሚመረቀውን የኢትዮ ጅቡቲ የምድር ባቡር መስመር አካል የሆነው የሰበታ መኤሶ መሥመር ሲመረቅ በክብር እንግድነት እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ፕሬዝዳንት ፋውሬ የሜቴክ ኢንጂነሪንግን ጨምሮ ሌሎች ቦታዎችንም ይጐበኛሉ ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያና ቶጐ የፓን አፍሪካኒዝም ኃሣብ ከተሰማበት ዘመን አንስቶ የዲፕሎማሲያዊ  ግንኙነት የጀመሩ ሀገሮች መሆናቸው ለትውስታ ተነስቷል፡፡የቶጐ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉም ሰምተናል፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

አፍሪካ የዘመኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በሚገባ ለመጠቀም የሳተላይት አማራጯን እያፈላለገች ነው

ዛሬ በሸራተን አዲስ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የመጡ የመንግሥት ኃላፊዎችና የሳተላይትና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ባለቤቶች በጉዳዩ ላይ ምክክር ጀምረዋል፡፡በመገናኛ እና ኢንፎርሜሸን ሚኒስቴር የግሉ ዘርፍ የአይ.ሲቲ ልማት ዳይሬክተር የሆኑት ኢንጂነር ተሾመ ወርቁ እንዳሉት በተለይም በመደበኛ ኔትዎርክ መገናኘት የማይችሉት ከከተማ የወጡ አካባቢዎችን ለማገናኘት ሳተላይት እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ከአየር ትንበያ አንስቶ እስከ መገናኛ እና የተለያዩ መረጃዎችን ለማሰባሰብ ያለ ሳተላይት የማይቻል መሆኑ ይታወቃል ያሉት ኢንጂነር ተሾመ የሳተላይት ኪራይ ዋጋ እጅግ ውድ በመሆኑ የአፍሪካ ሀገራት በተሻለ ዋጋ የተሻለ የሳተላይት አገልግሎት የሚያገኙበትን ዘዴ ዛሬ በተጀረው ጉባዔ እንደሚመከርበት ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያም በየአመቱ ከሳተላይት ኪራይ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የምታወጣ ሲሆን ወጪውን ለመቀነስና በአነስተኛ ወጪ አገልግሎቷን የምታስፋፋበትን መንገድ ታፈላልጋለች ብለዋል፡፡በጉባዔው ላይ የተገኙት የመገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ኢትዮጵያ የራሷን ሳተላይት ለማምጠቅ እያሰበችበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ዛሬ የተጀመረውና ፊውቸር ሳት አፍሪካ የተባለው ጉባዔ ብዙ ልምድ ይገኝበታል የተባለ ሲሆን በጉባዔው ላይም የሣተላይት ባለቤቶችና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችም ተገኝተዋል፡፡በአፍሪካ ግብፅ፣ ናይጄሪያ፣ ኬኒያና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ 7 ሀገሮች የራሳቸው ሳተላይት ያላቸው መሆኑን ሰተምናል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 24፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በኢትዮጵያ ለአይነ-ስውርነት ከተጋለጡ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሰዎች ያህሉ አብዛኞቹ ታክመው መዳን ይችሉ ነበር፡፡ ይሁንና ያሉን ሃኪሞች ቁጥር ዝቅተኛ መሆንና ህክምናው በገጠሩ አካባቢ አለመሰጠቱ ችግሩን ሰፋ አድርጐታል ተባለ፡፡ (ትዕግስትዘሪሁን)
 • ወርልጅ ቪዥን ኢትዮጵያ ኤልኒኖ ጠባሳውን ጥሎ ባለፈባቸው የሀገራችን ክልሎችና ወረዳዎች ለዳግም ችግር እንዳይጋለጡ ለ71 ሺህ 900 አባወራዎች ምርጥ ዘር አቅርቤያለሁ አለ፡፡ (ምሥክርአወል)
 • የብሔራዊ የደም ባንክ አፋጣኝ ደም ለሚፈለጉ የጤና ተቋሞች ደም ልኬያለሁ አለ፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • ኢትዮጵያና ቶጐ በተለያዩ መሥኮች በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸውን ሥምምነት ተፈራረሙ፡፡ (የኔነህሲሣይ)
 • የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቢሾፍቱው የኢሬቻ በዓል ወቅት በተፈጠረው አደጋ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስለመኖሩ አጣራለሁ አለ፡፡ (ትዕግስትዘሪሁን)
 • ከአምቦ አዲስ አበባ መሥመር የሕዝብ መጓጓዣ አለመኖር የትራንስፖርት ፈላጊዎችን እያጉላላ ነው ተባለ፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ከክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመሆን መፍትሄ አፈላልጋለሁ ብሏል፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • በኢትዮጵያ የአፍሪካ ገጠሮችን በሳተላይት መላ ለማገናኘት የታለመ ምክክር እየተካሄደ ነው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)

 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ወንጀል ነክ የሆኑ ጉዳዮችን ምርመራና ክስ ወደ ሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ለማስተላለፍ ዝግጅቴን ጨርሻለሁ አለ

ባለሥልጣኑ የምርመራ ስራውን ወደ ፌደራል ፖሊስ የክስ ሂደቱን ደግሞ ወደ ፌዴራል አቃቤ ህግ እንደሚያስተላልፍ ሰምተናል፡፡የፍትሃ-ብሔር ምርመራና ክሶች ግን ከባለሥልጣኑ ስር ሆነው ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡ሸገር መረጃውን የሰማው ከባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው ፀጋዬ ነው፡፡

አቶ እንዳልካቸው እንዳሉት ወንጀል ነክ የሆኑ ጉዳዮችን ምርመራና ክስ የማስተላለፍ ሥራ ባለሥልጣኑ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ እንዲጨርስ ነበር የታሰበው፡፡በአራት ወር ጊዜ ውስጥ ግን ዝግጅቱን ሙሉ ለሙሉ አጠናቋል ብለዋል፡፡ይህንኑ ዝግጅቱን መጨረሱን ለማሣወቅ ዛሬ በኢትዮጵያ ሆቴል ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት እያደረጉ እንደሚገኙ ነግረውናል፡፡ባለሥልጣኑ ወንጀል ነክ ጉዳዮችን ምርመራና ክስ ሙሉ ለሙሉ ከዚህ ወር ጀምሮ ለሁለቱ ተቋማት እንደሚያስተላልፍም ሰምተናል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers