• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በሳተላይት የሚሰራጭ የቴሌቭዥን ጣቢያ ለመክፈት የማመልከቻ ሰነድ ከገዙት መካከል የሥራ ኃሳባቸውን ዝርዝር ያቀረቡት 5ቱ ብቻ ናቸው ተባለ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በሳተላይት አማካይነት የሚሰራጭ የቴሌቭዥን ጣቢያ ለመክፈት የሚፈልጉ የሀገር ውስጥ ድርጅቶች የማመልከቻ ሰነድ እንዲወስዱ ጋብዞ ነበር፡፡

ድርጅቶቹ ማመልከቻውን ከወሰዱ በኋላ እስከ ሰኔ 30፣ 2008 ድረስ የፕሮጀክት ሰነዳቸውን እንዲያስገቡም የጊዜ ገደብ አስቀምጧል፡፡

የማመልከቻ ሰነዱን 28 የሀገር ውስጥ ድርጅቶች እንደወሰዱ በባለሥልጣኑ የመገናኛ ብዙሃን ምዝገባና ፍቃድ ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ሲሣይ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

የፕሮጀክት ሰነዱን አዘጋጅተው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለባለሥልጣኑ ያስገቡት ግን አምስት ድርጅቶች ብቻ እንደሆኑ ከአቶ ሙሉጌታ ሰምተናል፡፡

እነዚህ አምስት ድርጅቶች ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል፣ ድምፀ ወያነ ትግራይ፣ አርኪ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ እና ኢስት አፍሪካ ፊልም ፕሮዳክሽን እንደሆኑ ዳይሬክተሩ ነግረውናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ወንዝ ውስጥ የወደቁ ወይዘሮ ሕይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ቸርቸል ጐዳና አካባቢ በህገ-ወጥ መንገድ ለገበያ የቀረቡ 65 ጥንታዊ የብራና መፃህፍት ተገኙ ተባለ፡፡

በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የቅርስ ኢንቨንተሪ ደረጃ ማውጣት ዳይሬክተሩ አቶ ኤፍሬም አማረ ለሸገር ሲናገሩ በቅርቡ የፌዴራል ፖሊስ ባደረገው ክትትል ጥንታዊ የብራና መፃህፍቱን ያገኘው በስጦታ ዕቃዎች መሸጫ ሱቅ ውስጥ ነው ብለዋል፡፡

የብራና መፃህፍቱን ለገበያ ያቀረበው ግለሰብ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ እንደሆነም ሰምተናል፡፡

እነዚህ የብራና ፅሁፎች ባልተገባ መንገድ ለገበያ ሲቀርቡ ከጉራጌ ዞንና ከስልጤ 113 ጥንታዊ የብራና መፅህፍት ማይክሮ ፊልም ተቀርፀው መጥተዋል  ተብሏል፡፡

ከብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃህፍት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙት ኃላፊ አቶ እንዳለው አዳሙ ለሸገር ሲናገሩ 113ቱ የብራና ፅሁፎች በእስልምና ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ናቸው ብለዋል፡፡

ጥንታዊ የብራና ፅሁፎቹን ከተለያዩ መስጊዶች ነው በፊልም  ያሰባሰብነው ያሉት አቶ እንዳለው ባሉበት ስፍራ በጥንቃቄ አንዲጠብቁትም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተናል ብለዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 2፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ትላንት በባህርዳር ከተማ በተጠራው የተቃውሞ ህዝባዊ ሰልፍ ላይ የሰው ህይወት ጠፋ፤ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በሳተላይት የሚሰራጭ የቴሌቭዥን ጣቢያ ለመክፈት የማመልከቻ ሰነድ ከገዙት መካከል የሥራ ኃሳባቸውን ዝርዝር ያቀረቡት 5ቱ ብቻ ናቸው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በአዲስ አበባ ወንዝ ውስጥ የወደቁ ወይዘሮ ሕይወት አለፈ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በሕገ-ወጥ መንገድ ለገበያ ሊቀርቡ የነበሩ 65 የብራና መፃህፍት በፖሊስ መያዛቸው ተሠማ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ሰዎችን አጭበርብሮ ወደ 27 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት የወሰደው ግለሰብ የ5 ዓመታት የእሥራት ቅጣት ተፈረደበት፡፡ (ተክለማርያም ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በልተው ማደር የተሣናቸውን 20 በመቶ ያህል አዲስ አበቤዎች ለመደገፍ በአስተዳደሩ 450 ሚሊዮን ብር መመደቡ ተሠማ

ከአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መካከል 20 በመቶ የሚደርሱት ከድህነት ወለል በታች በሚባል የድህነት ደረጃ የሚኖሩ ናቸው ተባለ…

እነዚህ ዜጐች የምግብ ዋስትና ያልተረጋገጠላቸውና በልተው ማደር የከበዳቸው ናቸው ተብለዋል፡፡

የደሀ ደሀ የተባሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በልተው ማደር እንዲችሉ የከተማው አስተዳደር ከመጪው አመት ጀምሮ ለ10 አመት የሚዘልቅ የከተማ የምግብ ዋስትና መርሃ-ግብር ይጀምራል መባሉን ሰምተናል፡፡

ለዚህም 450 ሚሊዮን ብር መመደቡን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ግዛው ተናግረዋል፡፡

350 ሚሊዮን ብሩ ከዓለም ባንክ የተገኘ ብድር ሲሆን መቶ ሚሊየን ብሩን የኢትዮጵያ መንግሥት በጅቶታል፡፡

ኃላፊው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በመጪው 3 አመት ብቻ 66 ሺህ 150 ያህል የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በልተው ለማደር የሚያስችላቸው ገንዘብ በየወሩ ይሰጣቸዋል፡፡

እነዚህ ዜጎች ጧሪ ቀባሪ የሌላቸውና በጤናና በዕድሜ ምክንያት መስራት የማይችሉ አረጋውያን የሚሳተፉበት ነው ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ከደረጃ በታች ናችሁ የተባሉ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋሞች ተዘግተዋል ተባለ

በአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ በተደረገ ክትትል 21 የመንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛ ተቋሞች ተሰርዘዋል ተባለ፡፡የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የ2008 የሥራ ክንውኑን የተመለከተ ሪፖርቱ ላይ እንዳየነው በሀገር አቀፍ ደረጃ የ344 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ያሉበት ደረጃ በየአመቱ ተመልክቷል፡፡

በኦሮሚያ በ91 ማሰልጠኛ ተቋሞች ተፈትሸው 10ሩ እንዲዘጉ ተደርጓል ተብሏል፡፡በትግራይ 49፣ በደቡብ ክልል 53 እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር 8 የማሰልጠኛ ተቋማትን መመልከቱን የተናገሩት የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች በሁለቱ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከደረጃ በታች መሆናቸው የተለየ አንድ አንድ የማሰልጠኛ ተቋማት ተዘግተዋል ተብሏል፡፡

በትግራይ ከተዘጋው 1 ማሰልጠኛ በተጨማሪ 62ቱ ሥራ እየሰሩ በአንድ ወር ጊዜ የጐደላቸውን እንዲያሟሉ የተደረገ ሲሆን ሌሎች 11 ደግሞ ለ3 ወር ታግደዋል ተብሏል፡፡

ቴዎድሮስ ወርቁ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 29፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

 • በልተው ማደር የተሣናቸውን 20 በመቶ ያህል አዲስ አበቤዎች ለመደገፍ በአስተዳደሩ 450 ሚሊዮን ብር መመደቡ ተሠማ፡፡ (ትዕግስትዘሪሁን)
 • መንግሥት ከሀገር ውስጥ ሞባይል ገጣጣሚ ኩባንያዎች በመጪው ዓመት አርባ ሁለት ሚሊየን ዶላር አገኛለሁ ብሎ ተመኝቷል፡፡ ኩባንያዎቹ በበኩላቸው አቅማችን እየደከመ የኮንትሮባንድ ንግዱ ገበያውን እየተሻማን የተባለውን ገንዘብ ማምጣታችንን እንጃ እያሉ ነው፡፡ (ህይወትፍሬስብሃት)
 • መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በሀገራችን ተከስቶ የነበረው ድርቅ ያስከተለውን ተፅዕኖ ለመቀነስ ማህበራዊ ኃላፊነቴን እየተወጣሁ ነው አለ፡፡ (ንጋቱረጋሣ)
 • የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ሊዳሰሱ የማይችሉ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች እንዳይዘነጉና ከትውልድ ትውልድ ለማስተላለፍ ያግዛሉ ያላቸውን የጥናትና ምርምር ህትመቶችን አስመረቀ፡፡ (ምስክርአወል)
 • ከደረጃ በታች ናችሁ የተባሉ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋሞች ተዘግተዋል ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስወርቁ)
 • በአምራችና አገልግሎት ሰጭዎች ሥራ ላይ የሚውሉ አዳዲስ ደረጃዎች ወጡ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ አካባቢዎች የትዳር አጋር እናገናኛለን

አሁን አሁን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የትዳር አጋር እናገናኛለን፣ በፍቅር መሐል ጥል ከመጣም እናስታርቃለን በዚህ ስልክ ቁጥር ደውሉልን የሚሉ ማስታወቂያዎች ይታያሉ…

ለመሆኑ ከነዚህ ማስታወቂያዎች ጀርባ ያለው ምን ይሆን ? በሚል የሸገሩ ተህቦ ንጉሴ የስልክ አገልግሎቱን ፈትሿል የአገልግሎቱ ሰጪ ኢትዮቴሌኮምንና ባለሞያም አነጋግሯል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የጥራት መሥፈርታቸውን ያላሟሉ የታሸጉ የመጠጥ ውሃ በሚያቀርቡ አምራቾች ላይ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተባለ

በተለያየ ጊዜ ያልሆኑትን ነን የሚሉና ጥራታቸው የተጓደለ የታሸገ የመጠጥ ውሃዎች እየተለዩ እንደሆኑ ሰማን…

አስገዳጅ የጥራት ደረጃ መሥፈርቶችን አሟልተው ወደ ገበያ መግባት ያለባቸው የታሸጉ ውሃዎች ይሄንን ሳያሟሉ በከተማው እና በተለያዩ የክልል ከተሞች እየተቸበቸቡ ነው ተብሏል፡፡

በዚህ መሠረትም የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጥራት የጐደላቸው የውሀ አምራች ኩባንያዎች እንዳሉ ስላረጋገጥኩ እርምጃ ለመውሰድ ሥራዬን አጠናቅቄያለሁ ብሏል፡፡

የሚመለከተው መሥሪያ ቤት የጥራታቸውን ጉዳይ አረጋግጦ የላከልኝ የውሃ አምራች ኩባንያዎችንም ቁጥር አውቄያቸዋለው ማለቱን ነግሮናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ለአተት ተገቢውን ትኩረት አልሰጡም የተባሉ 20 ሕክምና መስጫዎች ታሸጉ፡፡ ማስጠንቀቂያም የተሰጣቸው አሉ

ለአተት በሽታ ተገቢውን ትኩረት ሳይሰጡ ህመምተኛውን አጉላልተዋል፣ ተገቢውን ህክምና እንዳያገኝ ወደ ህክምና ማዕከላት ፈጥነው አልላኩም የተባሉ 20 የግል የጤና ተቋማት ታሽገዋል ተባለ…

38 የሚሆኑ የግል የጤና ተቋማት ከዚሁ ጋር በተያያዘ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው የአዲስ አበባ የምግብ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ተናግሯል፡፡

ባለሥልጣኑ በአዲስ አበባ አተት መከሰቱ ከተገነረበት ጊዜ ጀምሮ ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን በዘመቻ ቁጥጥር እያደረገ ነው ያሉት የባለሥልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ በቁጥጥሩ ለአተት በሽታ አጋላጭ ናቸው የተባሉ  800 የሚደርሱ ምግብ እና መጠጥ አምራች ተቋማት፣ ስጋ ቤት እና አትክልት ቤቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ሊካሄድ ነው

አስገዳጁ ሀገር አቀፍ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ለመጀመሪያ ጊዜ ከነገ በስቲያ ጀምሮ ይካሄዳል ተባለ፡፡

ወሳኝ ኩነቶች የሚባሉት ልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺና ሞት ናቸው፡፡

ዛሬ ረፋድ ላይ ሀገር አቀፍ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ማብሰሪያ መድረክ ላይ ተገኝተን እንደሰማነው ከነገ በስቲያ የሚጀመረው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አስገዳጅ በመሆኑ የማያስመዘግቡትና የማይመዘገቡት የእስራትና የገንዘብ መቀጮ ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡

ጋብቻ፣ ሞትና ፍቺ ከተፈፀሙ በ30 ቀኖች ውስጥ ልደት ደግሞ በ90 ቀኖች ውስጥ መመዝገብ አለበት ተብሏል፡፡

በተጠቀሱት ቀኖች ያልተመዘገበ ወሳኝ ኩነት አጥጋቢ ምክንያት እስካልቀረበበት ድረስ ያስቀጣል መባሉንም በዝግጅቱ ላይ ሰምተናል፡፡

ምዝገባው ለዜጐች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎቶች ጠቀሜታቸው የጐላ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺና ሞት የሚባሉት ወሳኝ ኩነቶች አንዴ ከተመዘገቡ በኋላ ድጋሚ ማስመዝገብ አይቻልም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

ሐምሌ 28፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • በአዲስ አበባ ለአተት ተገቢውን ትኩረት አልሰጡም የተባሉ 20 ሕክምና መስጫዎች ታሸጉ፡፡ ማስጠንቀቂያም የተሰጣቸው አሉ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የአዲስ አበባን ሁለት ትላልቅ ወንዞች የማፅዳት ሥራ ሊከናወንላቸው ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የኢትዮጵያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ2008 በጀት ዓመት ከንብረት ጉዳት ከ3 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የካሣ ክፍያ አግኝቻለሁ አለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የአርባ ምንጭ የአዞ ቄራ በመጪው ዓመት የእንስሣቱን ሥጋ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ይጀምራል ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የSOS ሳልሕ ዓለም አቀፍ ተቋም የምሥራቅ አፍሪካ ቢሮ በአዲስ አበባ ይከፈታል፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በአዲስ አበባ የድጋፍ ሰጭ የመጓጓዣ አገልግሎት አቅራቢዎች ሥራው አላዋጣንም ሲሉ ከአስተዳደሩ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ጋር እየተወዛገቡ ነው፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • የጥራት መሥፈርታቸውን ያላሟሉ የታሸጉ የመጠጥ ውሃ በሚያቀርቡ አምራቾች ላይ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ሊካሄድ ነው፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers