• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ጥቅምት 11፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

 • የአዕምሮ ጤና ክብካቤ ማህበር የለጋሾችን እጅ እየተጠባበቅኩ ነው አለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስቱ አጥፍተዋል ያላቸውንና በቁጥጥር ሥር የሚያውላቸውን ዜጐች ስም ዝርዝር ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርዱ የማሳወቅ ግዴታ አለበት ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በጐች እና ፍየሎችን ከያዘ በቀናት ውስጥ የሚገድለው የደስታ መሰል በሽታን ለመከላከል የቁጥጥር ዘመቻ ተጀምሯል ተባለ፡፡ በሽታው በአርብቶ አደር አካባቢዎች መታየቱ ተነግሯል፡፡ (መሠረት በዙ)
 • ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚደረግ ብርበራ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አባልና የአካባቢው ነዋሪዎች በሚገኙበት መሆን አለበት ሲል የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ተናገረ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ በሚሆን ወጪ የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ሊገነባ መሆኑ ተሠማ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር ፕሮጀክት ትናንት ጋዜጠኞችና ሌሎች እንግዶችን ይዞ የሙከራ ጉዞ  አድርጓል፡፡ (ምህረት ስዩም)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የፓሪሱን የአለም መሪዎች የአየር ጠባይ ለውጥ ውሣኔዎችን ተከትሎ በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው አህጉራዊ የባለሙያዎች ስብሰባ ዛሬ ውሣኔዎችን ያሣልፋል ተባለ

ሸገር ከአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ ዛሬ እንደሰማው በፈረንሣይ ፓሪስ አምና በተዘጋጀው የመሪዎች ጉባኤ ላይ የበካይ ጋዝ እና የሙቀት መጠንን የሚወስኑ ስምምነቶች መውጣታቸውንና የተወሰኑ ሀገራት ስምምነቱን መፈረማቸውን ነው፡፡

ከወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ የአየር ጠባይ ለውጡን በሚመለከት የአለም መሪዎች በሞሮኮ ማራካሽ በሚያደርጉት ጉባኤ ላይ የፓሪሱን ስምምነት ሁሉም ሀገራት በፊርማቸው እንዲቀበሉ አፍሪካዊያን ጥሪ ያቀርባሉ ተብሏል፡፡

የአፍሪካ ልማትና የአለም የአየር ጠባይ ለውጥ በሚል በአዲስ አበባ የተዘጋጀው ስድስተኛው አህጉራዊ ስብሰባ ከሞሮኮው ጉባዔ ቀደም ተደርጐ የቀረበበት ዋናው ምክንያት የፓሪሱን ውሣኔ አፍሪካዊያን በመደገፍ በሌሎቹ ሀገራት ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር ታስቦ መሆኑንም ሰምተናል፡፡

አፍሪካ በ2030 እና በ2063 እንደ ጐርጐሮሣዊያን አቆጣጠር ላቀደችው የእድገት መዳረሻዋ አሁን የሚታየው የአየር ጠባይ ለውጥ አደጋና እንቅፋት እንዳይሆንባት ቅድመ ስራዎች መሠራት አለባቸውም ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ እስከ ስምንት መቶ የሚገመቱ አታሚዎችና አሳታሚዎች ቢኖሩም የሀገር ውስጥ የህትመት ፍላጐትን ለሟሟላት ግን አቅማቸው አልቻለም

ለዚህም መንግሥት የሰጠው አናሳ ትኩረት በዋናነት የተጠቀሰ ሲሆን ማበረታቻ አለመኖር ዘርፉን ወደ ኋላ ጠፍንገው ከያዙት ውስጥ ተጠቅሷል፡፡

ለዚህም ዘርፉ እንዳይሞት አስፈላጊውን እገዛ እንሻለን ሲሉ የኢትዮጵያ አታሚዎችና አሳታሚዎች ፕሬዝዳንት አቶ ተካ አባዲ አሳስበዋል፡፡

በክብር እንግድነት የተገኙት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ዘርፉ በትኩረት እንዲሰራበት የሥራ እድል ከመስጠት ጀምሮ እስከ ሚዲያ ብዝሃነት መስፋፋት ድርሻው ጉልህ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን አሁን ላይ በተፈለገው ልክ መጓዝ ባለመቻሉ ብዙ ሥራን የሚጠይቅ መሆኑን ጠቁመዋል አቶ ጌታቸው፡፡

“መፍትሄ ያመጣሉ የምትሏቸውን ኃሳቦች አቅርቡና እንነጋገርባቸው” ሲሉ በሸራተን አዲስ ለተገኙት ለአታሚና አሳታሚ ማህበራት ተወካዬች ጋብዘዋል፡፡

የህትመቱን ፈተና ለመቅረፍ ማህበሩ በተደራጀ መልኩ መቅረብ በመቻሉ መንግሥት የዘርፉን ችግር እንዲያስተውል ያስችለዋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የህትመት ኢንዱስትሪ ችግሮች፣ ስጋቶችና መፍትሄዎቻቸው የሚል ጥናት ያቀረቡት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው በለጠ የንባብ ባህላችን እንዳይዳብርና የህትመት ኢንዱስትሪው እንዳይስፋፋ ቴክኖሎጂው ፈተና መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 10፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በጥቂት የበጐ አድራጊ የህክምና ዶክተሮችና ተማሪዎች የተመሠረተው የጐጆ የህሙማን መርጃ ዘላቂ ማዕከል ሊገነባ መሆኑ ተሠማ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ቦንድ ገዝተው 5 ዓመት ለሆናቸው መመለስ ሊጀመር ነው ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • በመኸር እርሻ ከ3 መቶ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚገኝ ተነገረ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የፓሪሱን የአለም መሪዎች የአየር ጠባይ ለውጥ ውሣኔዎችን ተከትሎ በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው አህጉራዊ የባለሙያዎች ስብሰባ ዛሬ ውሣኔዎችን ያሣልፋል ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • በኢትዮጵያ እስከ ስምንት መቶ የሚገመቱ አታሚዎችና አሳታሚዎች ቢኖሩም የሀገር ውስጥ የህትመት ፍላጐትን ለሟሟላት ግን አቅማቸው አልቻለም ተባለ፡፡ (ምስክር አወል)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በ2009 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ114 ሚልዮን ብር በላይ በቦንድ ግዢ፣ በልገሳና በገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶች ተሰብስቧል ተባለ

እስካሁን ቃል ከተገባው 12 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ወደ 9 ቢሊዮን ብር ያህሉ ተሰብስቧል ሲል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ተናግሯል፡፡ምክር ቤቱ ዛሬ በ8ኛ መደበኛ ጉባዔው የ2008 በጀት አመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2009 አንደኛ ሩብ አመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ አባላት አቅርቧል፡፡

ከቦንድ ግዢ ከልገሳና ጽ/ቤቱ በ2008 ባዘጋጀው የገቢ ማሰገኛ ፕሮጀክቶች ከ134 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተነግሯል፡፡ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የመንግሥት ሰራተኛው በ3 እና በ5 ዙሮች የ4 ቢሊዮን ብር ቦንድ ገዝቷል ተብሏል፡፡በባለሀብቱና በንግድ ማህበረሰቡ ተሳትፎ በ2008 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ቦንድ ተገዝቷል 19 ሚሊዮን ብር የሚገመት ቁሳቁስም በተለያዩ ሽልማቶች በስጦታ አበርክተዋል፡፡

የባለ ሀብቱና የንግድ ማህበረሰቡ ተሳትፎ ጥሩ ጅምር ቢሆንም ቃል በተገባው ልክ አለመፈፀሙ በሪፖርቱ ላይ ተቀምጧል፡፡የብሔራዊ ምክር ቤቱ አባላት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ እየተወያዩ ሲሆን ብሔራዊ ምክር ቤቱ የቦርድ ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሮማን ገ/ስላሴ በምክር ቤቱ ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል፡፡

መሰረት በዙ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ ዘንድሮ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ለማጠናከር ሰባት ቢሊዮን ብር መድባለች ተባለ

መንግሥት ለጥቃቅን እንዲሁም ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች የተለያዩ ድጋፎችን ስሰጥ ቆይቻለሁ ይላል፡፡ይህ ድጋፍ በመሃል ያሉትን ኢንዱስትሪዎች ዘንግቷል የሚል አስተያየት ይሰማል፡፡አስተያየቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርም ይስማማበታል፡፡በሚኒስቴሩ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ትራንስፎርሜሽን ዳይሬክተር አቶ ሁነኛው አበባው እንዳሉት አሁን ለእነዚህም ኢንዱስትሪዎች ተገቢው ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ ለዚሁ ሲባል ሰባት ቢሊዮን ብር ዘንድሮ እንደተመደበ ነግውረናል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኢንዱስትሪዎችን ፍላጐት መሠረት አድርጐ ማሽኖችን በመግዛት እንደሚያቀርብ ከአቶ ሁነኛው ሰምተናል፡፡ባንኩ ይህንኑ አገልግሎት ለመስጠት የቅርንጫፎቹን ቁጥር እየጨመረ ይገኛል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም የቅርንጫፎቹን ብዛት 110 እንዳደረሰ ነግረውናል፡፡ድጋፉ የሚደረግላቸው ኢንዱስትሪዎች በተወሰነ ጊዜ የማሽኖቹን ዋጋ ይመልሳሉ ተብሏል፡፡
 
ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኪነ-ጥበብ ለሰላም በሚል ኃሣብ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና የመንግሥት አካላት ዛሬ ውይይት እያካሄዱ ነው

በወቅታዊ የኢትዮጵያ የሰላም ጉዳይ ላይ ኪነ-ጥበብ የራሱን አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይገባል በሚል ኃሣብ ባለሙያዎቹ ተሰባስበዋል፡፡ጋዜጠኛና ደራሲ አበረ አዳሙ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቲያትር ትምህርት ቤት ኃላፊና አቶ ተስፋዬ እሸቱ ኪነ-ጥበብ ለሰላም ባለው ጉዳይ ላይ የጥናት ወረቀት አቅርበዋል፡፡

ስለ ሀገር ፍቅር የሚያቀነቅኑ እና ወኔ የሚቀሰቅሱ አንድነትን የሚሰብኩ ሙዚቃዎች፣ ቲያትሮች እንዲሁም መፅሐፍት ቀደም ባለው ጊዜ ነበሩ አሁን ግን እየቀዘቀዙ መጥተዋል ሲሉ ባለሙያዎቹ ተችተዋል፡፡ይህ እንዳይቀጥል መሰራት አለበት ሲሉም ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

ፍቅርተ መንገሻ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአየር ጠባይ ለውጥ በአፍሪካ ከባድ ችግር የሆነው የውሃ መጠንን በጣም መቀነሱና የምግብ ዋስትናን በማሣጣቱ ነው ተባለ

በአዲስ አበባ በተጀመረውና ሁለተኛ ቀኑን በያዘው ስድስተኛው አህጉራዊ የአየር ጠባይ ለውጥና የአፍሪካ ልማት ጉባዔ ላይ የአየር ጠባይ ለውጥ ለአፍሪካ ሀገራት ግንባር ቀደሙን ችግር የሚያመጣው የምግብ ዋስትናን ስለሚያሣሣ ነው ተብሏል፡፡ በፓሪስ ፈረንሣይ አምና እንደ ጐርጐሮሣዊያን አቆጣጠር በ2015 በተዘጋጀው የአለም የአየር ጠባይ ለውጥ የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተደረሰው ስምምነት ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው የአፍሪካ አህጉር የአየር ጠባይ ለውጥ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን ላይ የኢትዮጵያ ወኪሎች በመገኘት በመጪው ወር በሞሮኮ ማራካሽ በሚዘጋጀው የአለም የአየር ጠባይ ለውጥ የመሪዎች ጉባዔ ላይ አፍሪካውያን በጋራ አንድ ድምፅ እንዲያሰሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ነገ ይጠናቀቃል ተብሎ በሚጠበቀው ስድስተኛው የአፍሪካ አህጉር የአየር ጠባይ ለውጥ ጉባዔ ላይ የፖሊሲ ጉዳዬችን በማንሣትና ውይይት በማደረግ የፓሪሱ ውሣኔዎች በማራካሹ የአለም የመሪዎች ስብሰባ ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የአፍሪካን ድምፅ የሚወክል ሰነድ ይቀርባል መባሉን ሰምተናል፡፡

የኔነህ ሲሳይ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 9፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን በቃሊቲ ማሰልጠኛ የነበሩ ፈታኞችን ቀይሬያለሁ፤ የሰልጣኞችን የፈተና ውጤት ይቀርፁ የነበሩ ካሜራዎችን በአዲስ ዘዴዎች ለመቀየር አስቤያለሁ እያለ ነው፡፡ (ምስክርአወል)
 • በአየር ፀባይ ለውጥ ላይ የሚመክረ 6ኛው አህጉራዊ ጉባዔ እንደቀጠለ ነው፡፡ (የኔነህሲሣይ)
 • በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው አህጉራዊ ጉባዔ የአየር ጠባይ ለውጥንና የዓለም የሙቀት መጠንን ተፅዕኖ ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት አፍሪካውያን የጋራ አቋማቸውን እንዲያጠናክሩ ተጠየቀ፡፡ (የኔነህሲሣይ)
 • በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ የአተት ወረርሽኝ መቀስቀሱ ተሠማ፡፡ (ህይወትፍሬስብሃት)
 • ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ቃል ከተገባው ውስጥ እስካሁን 9 ቢሊዮን ብር ያህል ተሰብስቧል ተባለ፡፡ (መሠረትበዙ)
 • ኢትዮጵያ ዘንድሮ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ለማጠናከር ሰባት ቢሊዮን ብር መድባለች ተባለ፡፡ (ንጋቱረጋሣ)

 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 8፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለኢትዮጵያ አጠቃላይ ምጣኔ ሐብት የሚያበረክተው ድርሻ አሁንም በተነፃፃሪ ዝቅተኛ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሳ)
 • ባለፉት 3 ወራት ብቻ በትራፊክ አደጋና በሌሎችም ምክንያቶች ከ126 ሚሊየን ብር በላይ የንብረት ኪሳራ እንደገጠመው የከተማዋ መንገዶች ባለሥልጣን እወቁልኝ አለ፡፡ (ተሕቦ ንጉሴ)
 • መንግስት በመላ ሐገሪቱ የነዳጅ ማደያዎችን የመገንባት እቅድ አለኝ አለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በግንባታ ላይ የሚገኘው ሕንጻ ውሃ እያጠጣ የነበረ ወጣት በኤሌክትሪክ ተይዞ መመቱ ተሰማ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በአየር ጠባይ ጉዳይ ላይ የሚመክር አህጉራዊ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ (የኔነህ ሲሳይ) 
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ባለፉት 3 ወሮች ለ3 ሺ 126 ጉዳዬች ነፃ የህግ ድጋፍ ሰጠ ተባለ

ማህበሩ ከተመለከታቸው ጉዳዮች 80 በመቶዎቹ በባልና ሚስት መካከል የተፈጠሩ ግጭቶች ሲሆን ከተስማሙት የተለያዩት ይበልጣሉ ተብሏል፡፡የፕሮግራም አስተባባሪዋ ወ/ሮ ሜሮን አራጋው ለሸገር ሲናገሩ የባልና ሚስት አለመግባባቶች፣ የአሰሪና ሠራተኛ ግጭቶች፣ የውርስና የአስገድዶ መድፈር እክሎች ያጋጠሟቸው 3 ሺ 126 ጉዳዮች ወደ ማህበሩ ቀርበው በስምምነት ሊወገዱ የቻሉት 220ዎቹ ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡

ቀሪዎቹ መስማማት ያልቻሉ ባልና ሚስቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲለያዩ የተለያዩ የቤት ውስጥ ጥቃት አድራሾችም በህግ እንዲጠየቁ በማድረግ መፍትሄ የተሰጣቸው ናቸው ተብሏል፡፡የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ባሳለፍነው ሳምንት በሶዶ ገና በ15 ዓመቷ በ35 ዓመት ሰው ጋር ጋብቻ አንድትፈፅም የተገደደች ታዳጊም በሰዎች ጥቆማ ካለእድሜ ጋብቻው መታደግ ተችሏል ጉዳዩ አሁንም እየታየ ነው ሲሉ ወ/ሮ ሜሮን ነግረውናል፡፡ ማህበሩ በየአመቱ 10 ሺ ያህል ጉዳዮችን እንደሚመለከትም ሰምተናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers