• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን ትናንት አስመረቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን ትናንት አስመረቀ፡፡ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በግንባታ ላይ የነበሩ የተለያዩ የስፖርት ማዘወተሪያዎች ናቸው ትላንት ተመርቀው አገልግሎት መስጠት የጀመሩት፡፡

ከነዚህም ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ግንባታው በጊዜ መጠናቀቅ ሳይሆንለት ለረዥም ጊዜ የተጓተተው የራስ ሀይሉ ዘመናዊ ጂምናዝየም ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ሰምተናል፡፡ጂምናዚየሙ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስና የእግር ኳስ ማጫወቻ ሜዳዎች ያሉትና ዘመናዊነቱን የጠበቀ ነው ተብሏል፡፡ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የሚገኘው ቆሼ ሜዳ ተብሎ የሚጠራው ቦታ ላይ ሦስት በአንድ የሜዳ ቴኒስ ከመታጠቢያ ክፍሎች ጋር ተሰርተውለታል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በተጨማሪ በጃልሜዳ የተጀመረው ዘመናዊ ጂምናዝየም 70 በመቶ መጠናቀቁን ተናግሯል፡፡ ወደፊት የአቃቂ ስቴዲየምን ለማጠናቀቅ እንዲሁም ለአራት ኪሎ ወ.ወ.ክ.ማ ባለ 7 ወለል ህንፃ ለመገንባት ኃሣብ እንዳለው የከተማዋ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እንዳለ ከበደ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በቅርቡ በካይሮ የተደረገው የአረብ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች ጉባኤ ስብሰባ የኢትዮጵያን የህዳሴ ግድብ ግንባታን የተመለከተ አይደለም ተባለ

በቅርቡ በካይሮ የተደረገው የአረብ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች ጉባኤ ስብሰባ የኢትዮጵያን የህዳሴ ግድብ ግንባታን የተመለከተ አይደለም ተባለ፡፡ ሸገር ወሬውን የሰማው ከውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሣ እንደተናገሩት ከአረብ የውሃ ሚኒስትሮች መሀከል የሱዳኑ አንድ በመሆናቸው በስብሰባው ላይ ተገኝተው ይህም እኛን የሚቃረን ነው ማለት አንችልም ብለዋል፡፡

በኢትዮያ እና በሱዳን መንግሥታት መሀከል ብዙ የጋራ ግንኙነትና ትስስር አለ የሚሉት ሚኒስትሩ ከ20 አመታት በላይ የዘለቀውን ትብብር በተመለከተ ከትላንት በስቲያ ባደረጉት ስብሰባ ላይ ይህንን ነግረውናል፡፡ሁለቱ ሀገራት በ2016 እንደ ጐርጐሮሣዊያን አቆጣጠር አዲስ አበባ ላይ በተጠራው ሁለተኛ የውሃ ሀብት ባለሙያዎች ስብሰባ ላይ በመሠረታዊነት የመከሩባቸውን የጋራ ነጥቦች በተመለከተም አቶ ሞቱማ ይናገራሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት በተዘረጋው የሀይል ማስተላፊያ የሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያ 100 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል እያገኘ ሲሆን የሀይል ፍላጐቱ ከዚህ በላይ እንዲሆን የሱዳን ፍላጐት ነው መባሉንም ሰምተናል፡፡በሱዳን የውሃ ሀብት ሚኒስቴር የተመራው የውሃ ሀብት ባለሙያዎች በቤንሻንጉል ክልል በመገኘት የታላቁን የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደትን መመልከታቸውንም ሰምተናል፡፡

የኔነህ ሲሳይ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በድርቁ ለተጐዱ ዜጐች ሁለተኛውን ዙር የአልሚ ምግብ እርዳታ እየሰጠሁ ነው አለ

እስካሁንም በ86 ሚሊዮን ብር ወጭ ለ360 ሺህ ዜጐች የአልሚ ምግብ እርዳታ መስጠቱን ተናግሯል፡፡መንግሥት በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የምግብ እርዳታ ያሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 9 ነጥብ 7 ሚሊዮን መውረዱን ቢናገርም የተለየ የአልሚ ምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጐች ቁጥር ግን ከ1 ነጥብ 7 ወደ 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ማደጉን ማህበሩ ተናግሯል፡፡

በመሆኑም ማህበሩ አልሚ ምግብ የሚያስፈልጋቸው ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም ከአምስት አመት በታች ለሆኑ ህፃናት ሁለተኛውን ዙር የአልሚ ምግብ  እርዳታ እየሰጠ መሆኑን በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የኮሙኒኬሽንና ሃብት ማሰባሰብ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ደግሰው አማኑ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ማህበሩ ከህብረተሰቡ በሚያገኘው ድጋፍ፣ በውጭ ሃገር ከሚሰሩ የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማህበራትና ከተባበሩት መንግሥታት ሥር ከሚሰሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች ያሰባሰበውን 86 ሚሊዮን ብር የአልሚ ምግብ እርዳታ ለግሶበታል፡፡

የተለየ የአልሚ ምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን የህብረተሰብ ክፍሎች መካከልም እስካሁን እጁን መዘርጋት የቻለው ለ360 ሺህ ያህሉ ብቻ መሆኑን ሰምተናል፡፡

የድርቁ ተጐጂዎች መልሰው እስኪቋቋሙና ወደነበሩበት ህይወት እስኪመለሱ ድረስ እርዳታውን እንደሚቀጥልም አቶ ደግሰው ተናግረዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 21፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ጅማ ዩኒቨርስቲ በሚቀጥለው አመት የኦንላይን ትምህርት በኢንጂነሪንግ ለመጀመር ሃሳብ አለው ተባለ፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • በመንግሥት ይዞታ ስር የሚገኙ 14 የልማት ድርጅቶች ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ ተዘጋጅተዋል ተባለ፡፡ (ወንድው ኃይሉ)
 • በድርቅ ጉዳት አጋጥሟቸው ለቆዩ ወገኖች የአልሚ ምግብ ድጋፍ እየተደረገለቸው ነው ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የሕዳሴውን ግድብ አካባቢያዊ ተፅዕኖ ጥናት ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ለሞጆና አካባቢዋ የቆዳ ፋብሪካዎች የዝቃጭ አወጋገድ ማቀለጣጠፊያ የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ ነው፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በአዲስ አበባ የተለያዩ የስፖርት ማዘወተሪያዎች ተገንብተው ለአገልግሎት መዘጋጀታቸው ተሠማ፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የናይጄሪያ በረራውን እንደማያቋርጥ ተናገረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የናይጄሪያ በረራውን እንደማያቋርጥ ተናገረ…

አየር መንገዱ ይህን ያለው እንደ ኢምሬትስ ያሉ የሌሎች አገሮች አየር መንገዶች ናይጄሪያ የገጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ መናር ተከትሎ በዚያ የሚያደርጉትን በረራ እንደሚያቋርጡ ከተናገሩ በኋላ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ናይጄሪያ የገጠማትን ወቅታዊ የፋይናንስ ቀውስ እረዳለሁ ቢሆንም አፍሪካዊያን በኩራት አየር መንገዳችን ሲሉ የሚጠሩት፣ የአህጉሪቱ ኩራት የሆነ አየር መንገድ ከሌሎች አየር መንገዶች በተለየ ያለበትን አፍሪካዊ ኃላፊነት ለመወጣት በረራውን እንደማያቋርጥ ለሸገር ተናግሯል፡፡

በረራውን ባለማቋረጥ ናይጄሪያ የገጠማትን የገንዘብ ችግር ለመፍታትም እንደሚያግዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተስፋ ማድረጉንም ሰምተናል፡፡

አየር መንገዱ የናይጄሪያ የውጭ ምንዛሪ ችግርን ለመፍታት መፍትሄ እያፈላለገ መሆኑንም ተናግሯል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ሰዓት ወደ ናይጄሪያ ሌጐስ፣ አቡጃ፣ ኡኑጉ እና ካኖ አየር ማረፊያዎች ይበራል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ዛሬ ረፋድ ላይ የደቡብ ሱዳኗ መዲና ጁባ መድረሳቸው ተሠማ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ዛሬ ረፋድ ላይ የደቡብ ሱዳኗ መዲና ጁባ መድረሳቸው ተሠማ…

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወሬ ምንጮች እንዳረጋገጥነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ረፋድ 3 ከ30 ላይ በጁባ አለምአቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱም የደቡብ ሱዳኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ታባን ዲንግ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደንግ አሎር፣ የካቢኔ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በአንድ ቀን ቆይታቸው በፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና ከምክትል ፕሬዝዳንቱ ጋር ይነጋገራሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በደቡብ ሱዳን ፓርላማ ተገኝተው ለጊዚያዊው ብሔራዊ ሸንጐው ንግግር እንደሚያደርጉም ሰምተናል፡፡

በመጨረሻም ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር በቤተ-መንግሥቱ ተገኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከደቡብ ሱዳን ጋር ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ይፈራረማሉም ተብሏል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሁለት ኤርትራዊያን የአየር ኃይል አብራሪዎች ከነ ተዋጊ ጄታቸው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተነገረ…

ሁለት ኤርትራዊያን የአየር ኃይል አብራሪዎች ከነ ተዋጊ ጄታቸው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተነገረ…

ሁለቱ አብራሪዎች አነስተኛ መጠን ያላትን ተዋጊ ጄት ባለፈው ረቡዕ መቐሌ ማሳረፋቸውንና በኤርትራ አየር ኃይል ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ አብራሪዎች መሆናቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

የወሬ ምንጩ የቀይ ባህር አፋሮች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ከሚባል የኤርትራ ተቃዋሚ ቡድን ቃል አቀባይ አቶ ነስረዲን አህመድ አሊ “ሰማሁ” ብሎ እንደዘገበው ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ሁለቱ አብራሪዎች አፈወርቂ ፍስሃዬ እና መብራቱ ተስፋማርያም ይባላሉ፡፡

የኢትዮጵያ አየር ሃይል ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ የሁለቱን ኤርትራዊያን አብራሪዎች ጄት አጅበው መቐሌ አሳርፈዋል ተብሏል፡፡

ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ራሷን ነጥላ ከቆየችው ኤርትራ ሁለቱ አብራሪዎች ወደ ኢትዮጵያ የኮበለሉበት አጋጣሚ ለብዙዎች መነጋገሪያ እንደሆነ መረጃው አስፍሯል፡፡

የኤርትራ መንግሥት የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ይፈፅማል የሚል ክስ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ይቀርብበታል፡፡

የሰብዓዊ መብት ጥሰቱን በመሸሽ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኤርትራዊያን የሜድትራኒያን ባህርን አቋርጠው አውሮፓ ለመግባት እንደሚሞክሩ በየጊዜው መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 18፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የዓለም ባንክ በአዲስ አበባ የሥራ አጦችን ብዛት ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት አግዛለሁ አለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የኢትዮጵያ የኢንጂነሪንግ ትምህርት ካለበት ችግር እንዲወጣ መላ የሚቀርብበት ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ወደ 350 ሚሊዮን ብር ገደማ አተረፍኩ አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አሰራሬን ለማዘመን ደፋ ቀና እያልኩ ነው አለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የኢትዮጵያ የዱቄት፣ ብስኩት፣ ፓስታና ማካሮኒ አምራቾች ከውጪ ሀገር ኩባንያዎች ጋር በጋራ መሥራት የሚችሉበት ዘዴ ላይ መነጋገራቸው ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የባሕር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ገዢዎች እየመጡላቸው ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የትራፊክ አደጋ የሚበዛባቸው ተብለው በጥናት የተለዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የአደጋዎቹን ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ አሁንም ዳግም እየተጠኑ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • በሞያሌ ኬላ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድ አባሎች ተግባራቸውን በአግባቡ መወጣት የሚያስችላቸውን ሥልጠና እየወሰዱ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • ሁለት ኤርትራዊያን የአየር ኃይል አብራሪዎች ከድተው ከነ ተዋጊ ጄቶቻቸው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተሠማ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ የሚኒስትሮች ስብሰባ ተካሄደ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪያ የማደርገውን በረራ አላቋርጥም አለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ዳሽን ባንክ በ2008 በጀት ዓመት ሰባት መቶ ሃያ ሰባት ሚሊየን ብር የተጣራ ትርፍ አገኘሁ አለ

ዳሽን ባንክ በ2008 በጀት ዓመት ሰባት መቶ ሃያ ሰባት ሚሊየን ብር የተጣራ ትርፍ አገኘሁ አለ…ይህ የባንኩ የተጣራ ትርፍ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሣከር የ1 በመቶ ቅናሽ ወይንም በ12 ሚሊየን ብር ዝቅ ማለቱን ዛሬ በጠቅላላ ጉባዔው ላይ ሲነገር ሰምተናል፡፡

ለትርፉ መቀነስም ከዓለም አቀፍ የባንክ እንቅስቃሴ የሚገኘው ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ በአብይ ምክንያትነት ተነስቷል፡፡ዳሽን ባንክ በበጀት አመቱ 224 ሚሊየን ብር ለመንግሥት ገቢ ማድረጉ የተነገረ ሲሆን ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ለመንግሥት 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ማስገባቱን በ20ኛው ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተናግሯል፡፡

የዳሽን ባንክ አጠቃላይ ንብረት 28 ቢሊየን ብር በላይ ደርሷል፤ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ነው መባሉንም ሰምተናል፡፡የአለም ኢኮኖሚ እንብዛም እምርታ አለማሳየት፣ የኢትዮጵያ ወጪ ንግድ መቀዛቀዝና የቢሮ ኪራይ ዋጋ መጨመር በ2008 በጀት ዓመት ለባንኩ አንደ ፈተና ያጋጠሙት ችግሮች መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከሴቶች መብትና ጥቅም ጋር በተገናኘ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የተሰጠባቸው የተመረጡ ውሣኔዎች ሰነድ ዛሬ ይፋ ተደረገ

ከሴቶች መብትና ጥቅም ጋር በተገናኘ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የተሰጠባቸው የተመረጡ ውሣኔዎች ሰነድ ዛሬ ይፋ ተደረገ…

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ መላኩ ዳኜ  በሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት ሰነዱ ሴቶች በቀላሉ ፍትህ እንዲያገኙ ይረዳል፤ ሴቶችን ለተመለከቱ ተመሳሳይ ወንጀልና ክርክሮችም ተመሳሳይ የህግ ትርጉም እንዲሰጥባቸው ያግዛል ብለዋል፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሣኔ የሰጠባቸውንና አስገዳጅ የህግ ትርጉም ከሰጠባቸው 18 ጉዳዮች የሴቶችን መብትና ጥቅም የተመለከቱት ብቻ ተመርጠው ተሰንደው በመፅሐፍ መልክ መዘጋጀታቸው ተነግሯል፡፡

በዳኝነት ሙያ ላይ ያሉትን ከመርዳት በተጨማሪ ሴቶችም መብትና ግዴታቸውን በቀላሉ የሚረዱበት ሰነድ ይሆናል ተብሏል፡፡

የሴቶችን መብትና ጥቅም የተመለከቱ ተመሣሣይ ወንጀሎች ተመሣሣይ የህግ ትርጉም እንዲሰጥባቸው ያግዛል የተባለው ሰነድ በሴቶች መብት ላይ ለሚሰሩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች፣ ለአቃቢያነ ህግ፣ ለጠበቆች፣ ለህግ ትምህርት ቤቶች እና ለሌሎችም ይሰራጫል መባሉን ሰምተናል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ የደን ሽፋኑን ለመጨመር ጥረት እየተደረገ መሆኑን የአካባቢና የደን ሚኒስትሩ ተናገሩ

በየአመቱ በሚደረግ የተፈጥሮ ሀብት ሥራና የተራቆቱ መሬቶች እንዲያገግሙ የማድረጉ ሥራ በሰፊው ስለተሰራ የሀገራችን ርጥበት አጠር አካባቢዎች በዕፅዋት እየተሸፈኑ ነው፤ በጐርፍ የሚጠቁ ቦታዎችም እየቀነሱ ነው፤ የሀገራችን የደን ሽፋንም 15 ነጥብ 5 በመቶ ደርሷል በ2012 ሃያ በመቶ እንዲሆንና በ2017 ደግሞ ሰላሣ በመቶ ለማድረስ እየተሰራ ነው ተባለ፡፡

ይህን ያሉት የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር ዴኤታው አቶ ከበደ ይማም ናቸው፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው እንደተናገሩት ለዚህም 5 ሚሊየን ሄክታር መሬትን በደን ለማልበስ እቅድ ተይዟል፡፡

የመሬት መሸርሸርና መራቆትን ለመከላከልም 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግም ለማድረግ እየጣርን ነው ብለዋል፡፡

ይህን ለማሳካትም የ10 ዓመት የደን ልማት ፕሮግራም መቀረፁን ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ከ4 ቢሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እንደነበር የተናገሩት አቶ ከበደ 80 በመቶ ችግኞች መተከላቸውን አስታውሰዋል፡፡ የመፅደቅና ያለመፅደቅ ነገር የሚታወቀው የበጋው ወራት ሲያልፍ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ሆኖም በግል ይዞታዎች የሚተከሉ ዕፅዋቶችን የመንከባከብ ልማዳችን ጥሩ ቢሆንም የጋራ መሬት ላይ የሚተከሉ ዕፅዋቶችን ግን ስንንከባከብ አንስተዋልም ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers