• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ኢትዮጵያ ከውጪ ሀገር እየገዛች የምታስገባውን ጥጥ ለማስቀረት እና የውጪ ምንዛሬን ለማዳን ያስችላል በማለት 70 ሺህ ሄክታር መሬቷ በጥጥ ዘር ተሸፈነ ተባለ

ኢትዮጵያ ከውጪ ሀገር እየገዛች የምታስገባውን ጥጥ ለማስቀረት እና የውጪ ምንዛሬን ለማዳን ያስችላል በማለት 70 ሺህ ሄክታር መሬቷ በጥጥ ዘር ተሸፈነ ተባለ፡፡ዘንድሮ ከ50 ሺህ ቶን ያህል ምርት ይጠበቃል፡፡የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ባራቲሁን ገሰሰ ለሸገር ሲናገሩ በጥጥ ዘር የተሸፈነው መሬት በደቡብ ኦሞ፣ በአፋር፣ በመተማ፣ በጋምቤላ እና በቤንሻንጉል ጉምዝ የሚገኝ ነው ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ምድር ይሰበሰባል የተባለው ይሄው ጥጥ ከ142 በላይ ለሆኑ የሀገር ውስጥ የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻዎች ይከፋፈላል ያሉት አቶ ባንቲሁን ምርቱን ለውጩ ገበያ ለማቅረብም እንዲቻል ለጥጥ የተመቸ 3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት አለ አልሚዎች ወደሥራው እንግባ ካላችሁ የባንክ ብድር እና የወጪ ገበያ ዕድል በመንግሥት ይመቻችላችኋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አሁን በጥጥ እርሻ ላይ 96 አልሚዎች ተሰማርተዋል ተብሏል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 24፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የሆቴሎችና መዝናኛዎች ግንባታና አገልግሎት ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተስማማ እንዲሆን ተጠየቀ፡፡ የመስኩ ግንባታና አገልግሎት የወደፊቱን አሳሳቢ ሁኔታ ከግምት ማስገባት ያሻል ተብሏል፡፡ (ምስክር አወል)
 • የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ያመቀው ከፍተኛ እንፋሎት 10 ሺ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ እንደሚያመነጭ ቢታወቅም እስካሁን ግን ጠብ ያለ ነገር የለም፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የሁለገብ የስልጠናና የሥራ ፈጠራ ማዕከል አዲስ አበባን ለማፅዳት የጀመርኩት ተንቀሣቃሽ የማስታወቂያ አገልግሎት ስኬታማ አድርጐኛል አለ፡፡ የከተዋን ፅዳት የሚቀንሱና በየጥጋ ጥጉ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች ብዛት ቢቀንስም ችግሩን ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ ከደንብ አስከባሪዎች ጋር በትብብር እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • በሰሜን ብሔራዊ ፓርክ ክልል ውስጥ የቆዩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች በሌላ አካባቢ እንዲሰፍሩ ተደረገ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ወፍ ዘራሽ የሰብል ዝርያዎች እየተሰበሰቡ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ሁለት የግል ሆስፒታሎች በመስኩ ተባብረው ለመሥራት ተስማሙ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ መውለድ እና በኑሮ ጫና የማህፀን ችግር የገጠማቸው እናቶች ከ250 ሺህ በላይ ይሆናሉ ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • ስምንት የኢትዮጵያ ትልልቅ ከተሞች የኤሌክትሪክ ማሻሻያ ሥራ ሊከናወንላቸው ነው፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ጥቅምት 22፣2009

ክፍል አስር አንድ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሥራ ባለደረባውን ለመግደል የሞከረው የፖሊስ አባል ቅጣት ተጣለበት፡፡

የሥራ ባለደረባውን ለመግደል የሞከረው የፖሊስ አባል ቅጣት ተጣለበት፡፡ምክትል ሳጅን አሰፋ ጅራኔ ጥቅምት 18 ቀን 2007 ከምሽቱ 4 ሰዓት ግድም ረዳት ሳጅን መንግሥቱ አብዲን ከተረኛ ፖሊስ ጠመንጃ ነጥቆ ለመግደል በመሞከሩ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ካራቆሬ ፖሊስ ጣቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተፈጠረ የሥራ  ግጭት ተከሳሽ ምክትል ሳጅን አሰፋ ጅራኔ የተረኛ ፖሊሱን አባል ክላሺንኮቭ ጠመንጃ ቀምቶና አቀባብሎ ረዳት ሳጅን መንግሥቱን ለመግደል ሲፈልግ እንደነበር የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ከዚህም ሌላ ተከሳሹ የግል ተበዳዩን በቦክስ መትቶ ህመም እንዲሰማው ማድረጉም ተጨማሪ ክስ ሆኖ ቀርቦበታል፡፡በአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ላይ መረዳት እንደሚቻለው ግድያው እንዳይፈፀም ያደረገው ሌላ የፖሊስ አባል ጠመንጃውን ስለቀማው ነው፡፡ተከሳሹ በቦክስ መምታቱን አምኖ ነገር ግን የግድያ ሙከራ አለማድረጉን ለፖሊስ በሰጠው ቃል አስረድቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሥራ ባለደረባውን ለመግደል የሞከረው የፖሊስ አባል ቅጣት ተጣለበት

የሥራ ባለደረባውን ለመግደል የሞከረው የፖሊስ አባል ቅጣት ተጣለበት፡፡ምክትል ሳጅን አሰፋ ጅራኔ ጥቅምት 18 ቀን 2007 ከምሽቱ 4 ሰዓት ግድም ረዳት ሳጅን መንግሥቱ አብዲን ከተረኛ ፖሊስ ጠመንጃ ነጥቆ ለመግደል በመሞከሩ ክስ መስርቶበታል፡፡

ካራቆሬ ፖሊስ ጣቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተፈጠረ የሥራ  ግጭት ተከሳሽ ምክትል ሳጅን አሰፋ ጅራኔ የተረኛ ፖሊሱን አባል ክላሺንኮቭ ጠመንጃ ቀምቶና አቀባብሎ ረዳት ሳጅን መንግሥቱን ለመግደል ሲፈልግ እንደነበር የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡ከዚህም ሌላ ተከሳሹ የግል ተበዳዩን በቦክስ መትቶ ህመም እንዲሰማው ማድረጉም ተጨማሪ ክስ ሆኖ ቀርቦበታል፡፡

በአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ላይ መረዳት እንደሚቻለው ግድያው እንዳይፈፀም ያደረገው ሌላ የፖሊስ አባል ጠመንጃውን ስለቀማው ነው፡፡ተከሳሹ በቦክስ መምታቱን አምኖ ነገር ግን የግድያ ሙከራ አለማድረጉን ለፖሊስ በሰጠው ቃል አስረድቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመርካቶ አካባቢ የመኪና ማቆሚያ መገንቢያ ቦታ አዘጋጀሁ አለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመርካቶ አካባቢ የመኪና ማቆሚያ መገንቢያ ቦታ አዘጋጀሁ አለ፡፡የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ያዘጋጀሁትን የመኪና ማቆሚያ ቦታም ለሚመለከተው አስተላለፊያለው ብሏል፡፡ ቦታው በአሜሪካን ግቢ መልሶ ማልማት የተገኘ ነው መባሉን ሰምተናል፡፡

አጠቃላይም የመሬቱ ስፋት 3 ሺ 920 ካሬ ሜትር እንደሆነ በመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ የኮሙኒኬሽን የሥራ ሂደት መሪ አቶ ንጉስ ተሾመ ለሸገር ተናግረዋል፡፡የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን መሬቱን ተረክቧል ያሉት አቶ ንጉስ በአሜሪካ ግቢ መልሶ ማልማት የተለያዩ መሬቶች ተዘጋጅተዋልም ብለውናል፡፡

የአሜሪካ ግቢ የመሬቱ አጠቃላይ ስፋት 16 ሄክታር መሆኑንም ሰምተናል፡፡

ተህቦ ንጉሴ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶችን አሿሿም ነባር ሂደት በአዲስ ይቀይራል የተባለ የጥናት ሰነድ በትምህርት ሚኒስትር መሰናዳቱን ሠማን

ሰነዱ የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች ሹመት በውድድርና በሚሰሩት ሥራ ተገማችነት እንዲሆን ሃሣብ ቀርቦበታል ተብሏል፡፡የትምህርት ሚኒስትር የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነው ለመሾም ዕጩ ሆነው የቀረቡ ሊያሟላቸው ስለሚገባቸው መስፈርቶች ዝርዝር የያዘውን ሰነድ ለክልሎች ልኳል ሲሉ የነገሩን የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ካባ ዑርጌሣ ናቸው፡፡

ክልሎች የቀረበላቸውን ሰነድ ተችተውና የራሳቸውን ሃሣብ አጠቃለው ለትምህርት ሚኒስትር እስኪመልሱ እየተጠበቁ መሆኑንም ሰምተናል፡፡ከዚህ በፊት በነበረው አሰራር የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች ሹመትን የተመለከቱ ከምሁራን የሚሰነዘሩ ወቀሳዎች ከመኖራቸው በተጨማሪ የትምህርት ሚኒስትር በፕሬዝዳንቶቹ የቋንቋና የብሔር መስፈርትነት ወቀሳ እንደበረታበት ተናግሮም ነበር፡፡

የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶችን የአሿሿም ሂደት ይቀይረዋል የተባለው ሰነድ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት ካገኘ፣ ለዕጩነት የቀረቡ ተሿሚዎች ዩኒቨርስቲዎቻቸውን ከየት ወዴት እንደሚያደርሱት የሚያሣዩበትን የሥራ እቅድ ማቅረብ ቀዳሚ መመዘኛ  ይሆናል ተብሏል፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 23፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተገልጋዮች እንደ ቅደም ተከተላቸው እንዲገለገሉ የሚያስችለው ስርዓት በአስራ ስምንት መስኮቶች ሊሰጥ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • መኖሪያቸውን ጐዳና ላደረጉ ከ350 ሺ በላይ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን የሥራ እድልና ምግብ የሚያስገኝ ፕሮግራም በቅርቡ ይጀምራል ተባለ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሚቀርቡልኝ በርካታ አቤቱታዎች ማጣራቱ ጊዜም ጥንቃቄም ጠያቂ ነው አለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶችን ሹመት በውድድር እንዲሆን ያስችላል የተባለ ሰነድ መዘጋጀቱ ተሠማ፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • በአዲስ አበባ መርካቶ ለመኪና ማቆሚያ የሚያገለግል መሬት ተዘጋጀ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲሱን ካቢኔ ሚኒስትሮች ሹመት አፀደቀ

በጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሣለኝ ቀርቦ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በሚፀድቀው የካቢኔ ሚንስትሮች ሹመት ከ30 የሚንስትር ቦታዎች በ16ቱ ላይ አዲስ ሰዎች ተሹመዋል፡፡

ዘጠኙ በነበሩበት እንዲቀጥሉ የተደረገ ሲሆን አምስቱ ተሸጋግረዋል፡፡

ዲሞክራሲን ለማስፋትና ጥልቀት እንዲኖረው ለማድረግ ሲባል በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ማዕከል መቋቋሙንም ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የነበረው የአማካሪ ሚንስትርነት የሹመት ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ተሽረው የፖሊስና ስትራቴጂያዊ እቅዶች አፈፃፀም ግምገማ ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ እንዲኖር ተደርጓል ብለዋል፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚንስርነት ማዕረግ የክላስተር ማስተባበሪያ የሹመት ቦታዎችም ተደርገዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 22፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲሱን ካቢኔ ሚኒስትሮች ሹመት አፀደቀ፡፡ ሚኒስትሮቹም ቃለ መሐላ በመፈፀም ኃላፊነታቸውን ተረክበዋል፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ያለፈው ዓመት የቡና ምርት የጥራት ችግር ገጥሞታል ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • በርካታ ወላጆች ልጆቻቸውን ተማሪ ቤት ከመላካቸው በፊት ማስተማር የሚጠበቅባቸውን አያስተምሩም ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የኢትዮጵያን ማዕድን የሚያወጡ ኩባንያዎች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በሚገባ እንዲወጡ ህግ እየተበጀ መሆኑ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • ኢትዮጵያ ለአገር ውስጥ የሐር አልባሳት ምርት ከሚያስፈልጋት ሐር 90 በመቶውን የምታስገባው ከውጭ ነው ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • ከባድ የጭነት መኪኖች ባልተፈቀደላቸው ጊዜ ወደ መንገድ በመግባት የአዲስ አበባን የትራፊክ ፍሰት እያስተጓጐሉት ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሞጆና አካባቢዋ አስራ አራት የቆዳ ፋብሪካዎች አሉ እነዚህ ፋብሪካዎች አካባቢን በከፍተኛ ደረጃ የሚበክል ፍሳሽ እንደሚለቁ ይነገራል

በሞጆና አካባቢዋ አስራ አራት የቆዳ ፋብሪካዎች አሉ እነዚህ ፋብሪካዎች አካባቢን በከፍተኛ ደረጃ የሚበክል ፍሳሽ እንደሚለቁ ይነገራል፡፡ፍሳሹ አካባቢን በማይጐዳ መንገድ እንዲወገድ ከረጅም ጊዜ አንስቶ ሲታሰብ መቆየቱን ሰምተናል፡፡ይህ ፕሮጀክት አሁን እውን የሚሆንበት ጊዜ መቃረቡን የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ ለገሠ ነግረውናል፡፡ፕሮጀክቱን ለማገዝ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ቃል ገብቷል ብለዋል፡፡

ባንኩ ገንዘቡን የሚሰጠው በብድርና በዕርዳታ እንደሆነም አቶ ወንዱ ነግረውናል፡፡አብዛኛው ግን ብድር ነው ብለዋል፡፡ፕሮጀክቱ አካባቢን የማይጐዳ የፍሳሽ አወጋገድ ፋብሪካዎቹ እንዲከተሉ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡

ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀው በካይ ጋዝ መጠን እንዲቀንስ የሚረዳ ቴክኖሎጂ እንደሆነም ነግረውናል፡፡ለካርቦን ንግድ በምታበረክተው አስተዋፅኦ ኢትዮጵያ የምታገኘው ገንዘብ እንደሚኖር ሰምተናል፡፡የፋብሪካዎቹን ተወዳዳሪነት እንደሚጨምርም አቶ ወንዱ ተናግረዋል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers