• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሕይወት ተፈራ፤ሁለተኛ ሳምንት ክፍል ሁለት

‘Tower in the sky’ (ማማ በሰማይ) እንዲሁም በቅርቡ ደግሞ Mine to Win (ኀሠሣ) በሚሰኙት መፅሐፍቶቿ የምትታወቀው ሕይወት ተፈራ ከመዓዛ ብሩ ጋር አድርጋው የነበረውን ጨዋታ የሁለተኛውን ሳምንት ክፍል ሁለት እንድታዳምጡ ጋብዘናል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የቡቡ ነገር - በስልክ የተጠራበት ቦታ የሚሄደው ውሻ…

ውሻው ቡቡ ይሰኛል፡፡ ባለቤቱ ያለበት ቦታ እንዲመጣ (የሥራ ቦታ ወይም ሆቴል) ሲፈልግ ጓደኛው ጋር ይደውልና ቡቡን አቅርቡልኝ ይላል፡፡ ከዛም ስልኩ ስፒከር ላይ ይደረግለትና ባለቤቱ ቡቡን፣ “ቡቡ … ተድላ ነኝ - ና” ይለዋል - ተድላ ሆቴል ነው ያለሁት ና ማለቱ ነው፡፡

ቡቡ ወዲያው ወደ ተድላ ሆቴል ሮጦ ባለቤቱን አዲስ ታዬን ያገኘዋል ይለናል ወንድሙ ኃይሉ…ፒያሳ ባለ አንድ ክሊኒክ የጥበቃ ሰራተኛ ሆኖ የሚሰራው የውሻው ባለቤት አዲስ ታዬ ከቡቡ ጋር አብረን ነው የምንኖረው፣ ደሞዜ የጋራችን ነው ይላል - አዲስ ጥሩ ምግብ ሲበላ ቡቡም ጥሩ ሥጋ አይቀርበትም፡፡

ቡቡ ፍራሽ አለው - አጠገቤ ነው የሚተኛው ይላል አዲስ…አረ ቡቡ ለዳንስስ ማን ብሎት…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከሒሳብ አያያዝና አወቃቀር ሥርዓት ውጪ ከ4 ሚሊዮን 682 ሺህ ብር በላይ ወጪ አድርጎ መገኘቱን...

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከሒሳብ አያያዝና አወቃቀር ሥርዓት ውጪ ከ4 ሚሊዮን 682 ሺህ ብር በላይ ወጪ አድርጎ መገኘቱን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2008 በጀት አመት የሒሳብ ምርመራ ሪፖርት አሣየ፡፡በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የ2008 በጀት አመት በፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ የሒሳብ ኦዲት ግኝት ላይ የቀረበው ሪፖርት ሲያድምጥ ውሏል፡፡

ዩኒቨርስቲው ሒሳብ መደቡን ያልጠበቀና በጀት አመቱን ባልጠበቀ ወጪ በ2008 ዓ/ም 4 ሚሊዮን 682 ሺ 383 ብር በትክክል የወጪ ሒሳብ መደብ ሳይመዘገብ መገኘቱን የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡ዶልቼ ኢንጂነሪግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለ ድርጅትም የኤሌክትሪክ የውሃና የጥገና እንዲሁም ለዩኒቨርስቲዎች ምክክር መድረክ መከፈል የሚገባው በአጠቃላይ 178 ሺ 742 ብር በጀት አመቱን ሳይጠብቅ የወጣ ወጪ ነው ተብሏል፡፡

ለወጪዎች ተገቢው የሰነድ ማስረጃ ሳይቀርብ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት 1 ሚሊየን 60 ሺህ ብር የድጋፍ ክፍያዎች የክፍያ ደረሰኝ ሳይቀርብ ተከፍሎ መገኘቱን ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡ማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት የሚፈፅመውን ግዥ በግልፅ የጨረታ ዘዴ እንዲፈፅም የሚያዝ ሕግ ቢኖርም የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ግን የ69 ሚሊየን 476 ሺህ 518 ብር የተለያዩ ግዥዎችን ከሕግ ደንብና መመሪያ ውጪ ያለ ምንም ውድድር በቀጥታ ግዥ ፈፅሞ መገኘቱን የኦዲት ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

ዩኒቨርስቲው በወቅቱ መሰብሰብና ማወራረድ የነበረበት 3 ሚሊዮን 137 ሺ 589 ብር ከ2001 እስከ 2008 ዓ/ም ድረስ መወራረድ ቢኖርበትም ያላወራረደው ሒሳብ መሆኑ ተነግሯል፡፡በቋሚው ኮሚቴው ተገኝተው በዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቱ ለተነሱና በኦዲት በተረጋገጡ የሒሳብ ግኝቶች ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠየቁት የዩኒቨርስቲው ተወካይም መወራረድ ከነበረበትና ለተለያዩ ክፍያዎች ወጪ ከሆነ ገንዘብ ከ8 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚሆነውን ማሰባሰብ ችለናል፣ ዩኒቨርስቲዎች አሁን ለተገኙበት የኦዲት የሂሳብ ግኝቶች ማስተካከያ ለማድረግ ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

በግዥና ወጪ ሥርዓት ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮች በኦዲት መስሪያ ቤቱ ለተገኙ የሒሳብ ክፍተቶች ምክንያቶች ናቸው ያሉ ሲሆን ዩኒቨርስቲው ሕጋዊ ክፍያ ለመፈፀምና ግዥ ለማከናወንም ያለበት አካባቢ አመቺ አለመሆኑና ደረጃቸውን የጠበቁ የግዥ ሥርዓቶች እንዳይፈፅም አጋልጦታል ሲሉ የዩኒቨርስቲው ተወካይ ለቋሚ ኮሚቴው ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ምህረት ስዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ይህ የጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማርያም ታሪክ ነው…

ለመሆኑ ጌታቸው ኃይለማርያም ማነው ? አትቸኩል ትደርስበታለህ፡፡ እውን በዚህች ዓለም ምን የሚያስቸኩል ነገር አለ - ሕይወት ራሷ አጭር ናት፡፡ ቢሆንም ሰው ሲጨነቅ አልወድምና ልንገርህ - ጌታቸው ኃይለማርያም ጋዜጠኛ ነው፤ የደራሲ በዓሉ ግርማ ጓደኛ!!!

የበዓሉ ግርማን “ኦሮማይ”ን ካነበብክ ወይም ስለእሱ መፅሐፍ ከሰማህ እዚያ በዓሉ ሕይወቱን የገበረለት መፅሐፍ ውስጥ ያለው ፀጋዬ ኃይለማርያም የተባለው ጋዜጠኛው ገፀ ባህሪ እንግዲህ ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማርያም ነው፡፡ዝና እንደጤዛ በናኝ ሆኖ እንጂ በዛን ዘመን ሬድዮ ወይም ቴሌቪዥን ያየ ሰው ሁሉ የሚያደንቀው ሥመጥር ጋዜጠኛ ነበር ጌታቸው ኃይለማርያም፡፡

በኢትዮጵያ ሬድዮ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣ፣ በተለይም “ዜና ፋይል” የተባለውን የዜና አቀራረብ ስልት የጀመረ በርካታ አንጋፋ ጋዜጠኞችን መርቶ ያሰራ ሥመጥር የመገናኛ ብዙሃን ሰው ነው…ለኢትዮጵያ ሬድዮ ትልቅ ራዕይ የነበረው፣ ቢልለት በዓለማችን የተለያዩ ከተሞች ሪፖርተሮችን ልኮ ከቦታው ማስዘገብን የሚያልም ነው የሚሉለት የጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይማርያምን ዝርዝር ታሪክ መኮንን ወልደአረጋይ በስንክሳር ዶክመንተሪው ተመልክቶታል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕይወት ተፈራ ከመዓዛ ብሩ ጋር፤የመጀመሪያውን ሳምንት ክፍል ሁለት

Tower in the sky’ (ማማ በሰማይ) እንዲሁም በቅርቡ ደግሞ Mine to Win (ኀሠሣ) በሚሰኙት መፅሐፍቶቿ የምትታወቀው ሕይወት ተፈራ ከመዓዛ ብሩ ጋር አድርጋው የነበረውን ጨዋታ የመጀመሪያውን ሳምንት ሁለተኛ ክፍል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕይወት ተፈራ ከመዓዛ ብሩ ጋር

‘Tower in the sky’ (ማማ በሰማይ) እንዲሁም በቅርቡ ደግሞ Mine to Win (ኀሠሣ) በሚሰኙት መፅሐፍቶቿ የምትታወቀው ሕይወት ተፈራ ከመዓዛ ብሩ ጋር አድርጋው የነበረውን ጨዋታ የመጀመሪያውን ሳምንት የመጀመሪያ ክፍል 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

እጣንና ከርቤ…

ለመሆኑ ስለእጣን እና ከርቤ ምን ያውቃሉ ? በሐገራችን ታሪክ … ባህል፣ እምነት፣ ኢኮኖሚ ላይ ለክፍለዘመናት ትልቅ ቦታ ይዞ ስለቆየውና አሁንም ጉልህ ቦታ ይዞ ስለሚገኘው ስለእጣን እና ከርቤ የሸገሩ መኮንን ወልደአረጋይ ያዘጋጀውን ዶክመንተሪ እንድታዳምጡ ጋብዘናል...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ሲጋራ ማጨስን ለማስቆም በሚያደርገው ጥረት ሕብረተሰቡ እንዲሳተፍለት ጠየቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ሲጋራ ማጨስን ለማስቆም በሚያደርገው ጥረት ሕብረተሰቡ እንዲሳተፍለት ጠየቀ፡፡ከትናንት ጀምሮ እስከ መጋቢት 30 የሚቆይ የህዝብ አሳታፊ መድረክ እየተካሄደም እንደሆነ ሰምተናል፡፡ህዝብ በሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች ሲጋራ ማጨስ የሚከለክል ህግ በቅርቡ የወጣ ቢሆንም በተግባር ግን ችግሩ እንዳለ አስተዳደሩ አምኗል፡፡

እየጨመሩ ለሄዱት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መብዛት አንድ መንስኤ ሲጋራ ነው ያለው አስተዳደሩ 2007 ላይ የወጣውን የቁጥጥር መመሪያ ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል፡፡በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በሆቴሎች፣ በምግብና መጠጥ ቤቶች፣ በህዝብ ትራንስፖርት፣ በጤናና በትምህርት ተቋማት ሲጋራ ማጨስ የተከለከለ እንደሆነ ያስታወሰው አስተዳደሩ በነዚህ ተቋማት የማስጠንቀቂያ ፅሁፎች ሊለጠፍ እንደሚገባ አስታውሷል፡፡

ትንባሆ እንዳይጨስ ለመከለከል የተጀመረው ስራ ጥሩ ቢሆንም ችግሩ ግን አሁንም በሰፊው ይታያልና ህብረተሰቡ እንዲሳተፍበት ጠይቋል፡፡

አስፋው ስለሺ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers