• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሁለት ሊትር ባንድ ትንፋሽ…

በቀን እስከ 20 ሊትር የሚጠጣው የድሬዳዋው ያሬድ ኃይሉን እናስተዋውቃችሁ፡፡በብየዳ ሙያ የሚተዳደረው ያሬድን የድሬዳዋ ሰው በውሃ ጠጪነቱ ነው የሚያውቀው፡፡ በልጅነቱ የጀመረው ይሄ ብዙ ውሃ የመጠጣት ፍቅር በርትቶበት አሁን ከምግቡም ይልቅ ውሃው ላይ ነው የምበረታው ይላል…ሙሉውን ያዳምጡ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

የኢትዮጵያ ሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ ሳምንት ሆኖታል...

የኢትዮጵያ ሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ ሳምንት ሆኖታል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሀገሪቱ ፀጥታ መልክ በማጣቱና በመደበኛው ሕግ ለማስከበር ባለመቻሉ መሆኑ ተነግሯዋል፡፡የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሃገራችን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ላይ የሚያስከትለው ችግር ምን ያህል ይሆን ? ንጋቱ ሙሉ የፖለቲካ ምሁር አነጋግሯል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የ‘ደረቅ ቼክ’ ዘመን

“የትምህርት ቢሮው ትምህርትን ለማሳደግ ተግቶ እየሠራ ነው!” አይነት ነገረ ግርም ይላል፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሚዲያ ላይ ሲቀርብ ደሞ የበለጠ ይገርማል...ይሄ ዜና ተብሎ! ይሄ ወሬ ተብሎ! ቆይ የትምህርት ቢሮው ትምህርትን ለማሳደግ ካልሠራ ግብርና ቢሮው ሊሠራለት ነው!

ሰውየው የሆነ ሥራ ሠርቶ ቼኩን ተቀብሏል፡፡ ገና ባንክ ሳይደርስ ሂሳቡን መሥራት፣ እቅድ ማውጣት ጀምሯል፣ ህልሙን በቅደም ተከተል ማስቀመጥ ጀምሯል፡፡ “መጀመሪያ ያንን የኩሽና ጣራ አድሳለሁ፡፡ ባለቤቴ ተሰቃየች እኮ!” “ልጄን ደግና ሆስፒታል ወስጄ አስመረምራለሁ፡፡” በገንዘቡ የሚሠራውን ነገር ተራ በተራ ያስቀመጠዋል፡፡ መቼም በሠላሰ ሺህ ብር ይህን ማድረግ አያቅተውም!

በንክ ይደርሳል፡፡ ቼኩን ይሰጣል፡፡ ገንዘብ ከፋዩ ኮምፒዩተር ላይ አፍጥጦ ይቆያል፡፡ ዘንድሮ “አጭበርባሪው ስለበዛ በደንብ ማጣራት ፈልጎ ይሆናል፡፡” ትንሽ ቆይቶ ከፋዩ ቼኩን ይመልስለታል፡

“ገንዘብ የለም፡፡”

ገንዘብ የለም! ባንክ ውስጥ ገንዘብ የለም ብሎ ነገር ምንድነው?
“ወንድሜ ያልከኝ አልገባኝም፡፡”
“ድርጅቱ በቂ ሂሳብ የለውም፡፡” 
“እነሱ ናቸው እኮ ቼኩን የሰጡኝ!”

“አውቃለሁ፡፡ እነሱም አላወቁት ይሆናል፡፡ መቶ ሃምሳ አምስት ብር ነው ያላቸው፡፡”
ይቺን ይወዳል! ሞባይሉን መዥረጥ ያደርጋል፡፡
“ሄሎ፣ እኔ ነኝ…

“ኦ…ገንዘብህን ወሰድክ?

“ምን እወስዳለሁ! ሂሳባችሁ ውስጥ በቂ ገንዘብ የለም ነው የሚሉት፡፡”
“እንዴት…በቅርብ ጊዜ አስገብተናል እኮ!”

“መቶ ሃምሳ አምስት ብር ብቻ ነው ያላችሁ ነው ያሉኝ፡፡” 
“ኦ…ሶሪ፣ የእኛ ስህተት መሆን አለበት፡፡”

“እኔ እኮ መጀመሪያም በካሽ ክፈሉኝ ያልኩት ችግር እንዳይገጥም ነው፡፡ አሁን ወደ ካሽ ለውጡልኝ፡፡”

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ተላላፊ የሆኑና በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ በሽታዎችን ለመከላከል በቂ ስራዎች ባለመሰራታቸው ስርጭታቸው በየጊዜው የአገሪቱ ስጋት እየሆኑ ነው ተባለ

ተላላፊ የሆኑና በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ በሽታዎችን ለመከላከል በቂ ስራዎች ባለመሰራታቸው ስርጭታቸው በየጊዜው የአገሪቱ ስጋት እየሆኑ ነው ተባለ፡፡ተላላፊ ከሆኑት ውሀ ወለድና ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ ተላላፊ ካልሆኑት ደግሞ እንደ ስኳርና የኩላሊት ህመሞች በቂ የሆነ የመከላከል ሥራ ያልተሰራባቸው ናቸው ተብሏል፡፡

ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ህመሞች መሆናቸው ግን ተነግሯል፡፡ይህን የሰማነው ዛሬ የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማህበር ባዘጋጀው 29ኛ አመታዊ ጉባኤው ላይ ነው፡፡በቅድመ በሽታ መከላከል የተመሰረተው የኢትዮጵያ የጤና ፖሊሲ ላይ ልዩ ትኩረት ያደርጋል በተባለው በዘንድሮ ጉባኤው ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ከመከሰታቸው በፊት መከላከል ላይ በርካታ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ተነግሯል፡፡

የጨቅላ ሕፃናትን እና እናቶችን ሞት መቀነሷ ኢትዮጵያ በበሽታ መከላከል ዘርፍ ትልቅ ለውጥ ያመጣችበት ነው የተባለ ሲሆን እንደ ወባ፣ ፖሊዮና ሌሎች በሽታዎችን ደግሞ ጨርሶ ከአገሪቱ ማጥፋት ላይ አሁን እየተሰራ ነው ውጤቶችም ተመዝግቧል ሲሉ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃን ተናግረዋል፡፡

በወረርሽኝ መልክ የሚነሱ ውሃ ወለድና ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ላይ ግን አሁንም ብዙ እንዳልተሰራ ተነግሯል፡፡በሽታዎቹ ሲከሰቱም ከፍተኛ ችግር እንደሚያደርሱ ነው የተነገረው፡፡በጉባኤው ላይ ስለ ቅድመ በሽታ መከላከል ጥናታዊ የምርምር ፅሁፎች ይቀርባሉ የተባለ ሲሆን ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለ3 ቀናት ያህል እንደሚካሄድም ሰምተናል፡፡

ምህረት ሥዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ወለድ የሚጠየቅባቸውና በአጭር ጊዜ የሚከፈሉ ብድሮችን መውሰድ አቁማለች ተባለ

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ወለድ የሚጠየቅባቸውና በአጭር ጊዜ የሚከፈሉ ብድሮችን መውሰድ አቁማለች ተባለ...የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር እንደሚለው በአጭር ጊዜ የሚከፈሉ ብድሮችን ኢትዮጵያ መውሰድ ያቆመችው ወጪ ንግዷ እስኪሻሻል ነው፡፡

ከዓለም ባንክና ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት /አይ ኤም ኤፍ/ ጋር ከተመከረ በኋላ የተወሰነ ውሳኔ እንደሆነም በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኢንፎርሜሽን ዳይሬክተር ሃጂ ኢብሣ ተናግረዋል፡፡ዳይሬክተሩ እንዳሉት ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ የምትወስደው በረጅም ጊዜ የሚከፈሉና የወለድ ምጣኔያቸው አነስተኛ የሆኑ ብድሮችን ብቻ ነው፡፡

ከዚህ ብድር ወደ ስልሣ በመቶ የሚጠጋው እንደ ዕርዳታ የሚቆጠር እንደሆነም ተናግረዋል፡፡የወጪ ንግዱን ለማሻሻል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነውም ብለዋል - ሃጂ ኢብሳ፡፡የኢትዮጵያ የዘንድሮ ስድስት ወር የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት በትንሹም የተሻለ ቢሆንም አሁንም ብዙ የሚቀረው እንደሆነ ሃጂ ኢብሳ ተናግረዋል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአፍሪካ በግዙፍነቱ የሚነገርለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤር ባስ A350 የምስለ በረራ ወይንም ሲሙሌተር ማዕከል ዛሬ ያስመርቃል ተባለ

በአፍሪካ በግዙፍነቱ የሚነገርለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤር ባስ A350 የምስለ በረራ ወይንም ሲሙሌተር ማዕከል ዛሬ ያስመርቃል ተባለ፡፡ ከአየር መንገዱ ሸገር እንደሰማው በዛሬው እለት በአየር መንገዱ ዋና መ/ቤት ይመረቃል የተባለው ምስለ በረራ ወይንም ሲሙሌተር በአፍሪካ በግዙፍነቱም ሆነ በዘመናዊነቱ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ወልደ ማርያምን ጨምሮ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት የስራ ሀላፊዎችና የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች በሚገኙበት ሥነ-ሥርዓት የምስለ በረራ ማዕከሉ ይመረቃል ተብሏል፡፡

ኤር ባስ A 350 ግዙፉና ታላላቅ አውሮፕላኖችን ለማብረር ስልጠና የሚሰጥበት ምስለ በረራ በኢትዮጵያ መዘጋጀቱ የበለጠ የአየር መንገዱን ተመራጭነት የሚያሳድገውና እምነት የሚጣልበት አየር መንገድ ያደርገዋል መባሉንም ሰምተናል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ በመዳረሻ ብዛቱ ቀዳሚ አየር መንገድ ከመሆኑም በላይ የተለያዩ ሀገር ዜጎች የስልጠና አገልግሎት የሚሰጥበት የመማሪያ ማዕከል መያዙም ለአየር መንገዱ አትራፊነትና ተመራጭነት ሌላኛው ምክንያት ነው መባሉንም ሰምተናል፡፡ ለኤር ባስ A 350 አውሮፕላኖች በረራ እንዲሆን የተገነባው ምስለ በረራ ወይንም ሲሙሌተር ምን ያህል ገንዘብ እንደጠየቀ ለጊዜው የተባለ ነገር የለም፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አያቶላህ ሆሚኒ

የሺአ ሙስሊሞች መሪና የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ መስራች አያቶላህ ሆሚኒ ማን ናቸው? እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው ዘርዘር አድርጎ ይነግረናል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አዋጅ ነጋሪው ጋዜጠኛ - አሰፋ ይርጉ…

አሁን ላይ ጋዜጠኛ አሰፋ ይርጉን ስንቶች ያውቁት ይሆን ? ብዙዎች በጆሮ ገብ ድምፁ የሚያውቁት አሰፋ ይርጉ የአብዮቱን ዘመን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና ሌሎች የደርግ ዘመን አዋጆችን በማንበቡ ይታወቃል፡፡ አቶ አሰፋ ይርጉ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትንም በማቋቋሙ ይታወቃል…

መኮንን ወልደአረጋይ በስንክሳር መሰናዶው የእኚህን አንጋፋ ጋዜጠኛ ታሪክ ዳስሷል፡፡ ወደ ዮትዩብ ቻናላችን ጎራ ብላችሁ እንድታዳምጡ ጋብዘናል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሳይንስ መረጃዎቻችን

በዚህ ሳምንት ከተሰሙ የሳይንስ መረጃዎች ግንባር ቀደሙ የፈረንሳይ ሳይንቲስቶች ይፋ ያደረጉት የጥናት ውጤት ነው፡፡ የጥናት ውጤቱ በፋብሪካ በከፍተኛ ሁኔታ የተቀነባበሩ ምግቦች ካንሰር አምጪ ናቸው ይላል፡፡ በ105 ሺ ሰዎች ላይ የተሰራው ይሄው ጥናት እንደሚለው ሰዎች በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን አብዝተው የሚመገቡ ከሆነ ለካንሰር የመጋለጣቸው እድል ይጨምራል፡፡

ውፍረት እና ሲጋራ ማጨስ ለካንሰር አጋላጭ ናቸው የሚለው የዓለም የጤና ድርጅት በፋብሪካ የተቀነባበረ ስጋን ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ለካንሰር አጋላጭ ነው ይለዋል፡፡
ፈረንሳያዊያኑ ተመራማሪዎች አብዛኞቹ ሴቶች የሆኑበትን የጥናቱን ፍቃደኞች የአመጋገብ ሁኔታ ለ5 ዓመታት ተከታትለዋል፡፡ በዚህም መሰረት የጥናቱ ተሳታፊዎች የሚመገቡት በፋብሪካ የተቀነባበረ ምግብ መጠን በ10 በመቶ ሲጨምር በካንሰር የተያዙ ሰዎች ብዛት ደግሞ በ12 በመቶ ሲጨምር ታይቷል፡፡

“በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦች መመገብ አሁን ባለው ሁኔታ እየጨመረ ከመጣ በቀጣይ አስርት ዓመታት በካንሰር የመያዝ ሁኔታ እጅጉን ያንረዋል” የሚለው ይህ የጥናት ውጤት በብሪቲሽ ሜዲካል ጆርናል ላይ ታትሞ ወጥቷል፡፡በዚህ ሳምንት የተሰማው ሌላው የሳይንስ መረጃችን ደግሞ እፅዋት በምድራችን ላይ ብቅ ስላለቡት ወቅት አዲስ መረጃ እነሆ ይለናል፡፡

ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከመሬት 4.5 ቢሊየን ዓመታት ዕድሜ ውስጥ፣ በመጀመሪያዎቹ 4 ቢሊየን ዓመታት ከማይክሮብ በስተቀር ምንም ዓይነት ሌላ ሕይወት አልነበረም፡፡ እናም በጥንታዊ እፅዋት ቅሪት ላይ በተደረገ ጥናት የመጀመሪያዎቹ እፅዋት በምድራችን ላይ ብቅ ያሉት የዛሬ 400 ሚሊየን ዓመታት ግድም እንደሆነ ነበር የሚታሰበው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሙሉ መመሪያ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሙሉ መመሪያ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባሳለፍነው አርብ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል።

ክፍል አንድ፡ የተከለከሉ ተግባራት

ንዑስ ክፍል አንድ፡ በማንኛውም የአገሪቱ ክፍሎች የተከለከሉ ተግባራት
1) ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን የሚጥስ ተግባር መፈጸም፣ በህገ መንግስቱና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ላይ የሚፈጸሙ በወንጀል ህጉ ከአንቀጽ 238 እስከ 260 ድረስ የተመለከተ ማናቸውንም ወንጀሎች መፈጸም
2) የህዝቦችን መቻቻልና አንድነት የሚጎዳ ተግባር መፈጸም። ማንነትን፣ ዘርን፣ቋንቋን፣ ሃይማኖትን፣ የፖለቲካ አመለካከትን መሰረት ያደረገ ማንኛውንም አይነት በህይወት፣ በንብረት እንዲሁም አካላዊ ወይም ስነልቦናዊ ጥቃት መፈጸም ወይም ማፈናቀል፣ እነዚህን ድርጊቶች እንዲፈጸሙ መቀስቀስ ማነሳሳት
3) በአሸባሪነት ከተፈረጁ ድርጅቶች አመራሮች፡ አካላት እና ጸረ ሰላም ቡድኖች ጋር ማናቸውንም ግንኙነት ማድረግ፣የአሸባሪ ድርጀቶችን አላማ ማስፈጸም ጽሁፎችን መያዝ ማስተዋወቅ
4) የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ማወክ፤ የተሽከርካሪ የባቡር እንቅስቃሴ ማወክ፣ የመንገድ ሃዲድ መዝጋት ጉዳት ማድረስና ሌሎች መሰል እንቅስቃሴ ማሳየትም ሆነ አገልግሎት ማስተጓጎል፣ ከተቀመጠው ታሪፍ በላይ ታሪፍ መጨመር የተከለከለ ስምሪት ማድረግ
5) የህዝብ አገልግሎት ማስተጓጎል ማቋረጥ፡ ህዝብ መገልገያዎች የንግድ ስራዎች ሱቆች የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት መዝጋት ወይም ምርትና አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረግ፣ ከስራ ቦታ ያለ በቂ ምክንያት መጥፋት ወይም ስራ ማቆምና ስራን መበደል
6) በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረስ፣ በህዝቦች በመንግስት ተቋማትና የግል ንብረት ላይ በማንኛውም መንገድ ጉዳት ማድረስ
7) የህግ አስከባሪዎች ስራ ማወክ፡ የህግ አስከባሪዎች የሚሰጡትን ማንኛውንም ትዕዛዝ አለማክበር፣ ስራቸውን አለማክበር፣ ለፍተሻ አለመተባበር፣ ወይም እንዲቆሙ ሲጠየቁ አለመቆም፣ ኬላዎችን ጥሶ ማለፍ፣ የህግ አስከባሪዎች ላይ ጥቃት መፈጸም ወይም ለመፈጸም መሞከር ስራቸውን ማዛባት፣እስረኞችን ወይም የህግ ታራሚዎችን ማስፈታት ወይም እንዲያመልጡ ማድረግ
8) ያልተፈቀዱ ሰልፍ የአደባባይ ስብሰባ፡ የህዝብና የዜጎች ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር ሲባል ከኮማንድ ፖስቱ ፍቃድ ውጭ ማናቸውንም ሰልፍና የአደባባይ ስብሰባ ማድረ
9) በትምህርት ተቋማት አድማ ማድረግ ፣በትምህርት ቤቶች፣ በዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደቶችን የማወክ፣ አድማ ማድረግ፣ የትምህርት ተቋማትን መዝጋት፣ እንዲዘጉ ቅስቀሳ ማድረግ ወይም የትምህርት ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት ማድረስ የተከለከለ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአለቃ ገብረሃና ነገር…

በመላው ኢትዮጵያ ታሪካቸውን ያልሰማ ማግኘት ይከብዳል፡፡ ስማቸው ሲጠቀስ ብዙዎች ቀልዶቻቸውን አስታውሰው ፈገግ ይላሉ፡፡ አለቃ ግን ሐገር የመሰከረላቸው ታላቅ ሊቅም ነበሩ…ለመሆኑ አለቃ ገብረሃና ማናቸው ? ተፈሪ ዓለሙ በትዝታ ዘ አራዳ መሰናዶው የእኚህን ተወዳጅ ኢትዮጵያዊ ታሪክ ያስቃኘበትን ፕሮግራሙን የመጀመሪያ ክፍል ወደ ሸገር ኦፊሺያል የዩትዩብ ቻናል ጎራ ብላችሁ ታዳምጡ ዘንድ ጋብዘናል...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers