• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በባሕርዳር ከተማ የባንኮች አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጠ ነው ተባለ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት የባንኮች አገልግሎት በዋና ከተማዋ ባህርዳር እስካሁን መቋረጡ ተሰማ…

ሸገር ወሬውን የሰማው ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ከሆኑት አቶ ንጉሱ ጥላሁን  ነው፡፡

ተቃውሞ ከተነሳበት ቀን ጀምሮም የደህንነቱ ነገር የገንዘብ ተቋማቱ ስላሳሰባቸው ከአገልግሎት ውጪ መሆናቸውን ኃላፊው ነግረውናል፡፡ በባህርዳር ከተማ የባንኮች አገልግሎት ብቻም ሳይሆን የተቋረጠው ትላልቅ ሆቴሎችና የንግድ ማዕከላትም ጭምር እንደሆኑ አቶ ንጉሱ ነግረውናል፡፡

ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ተቋማት መቼ ወደ ሥራቸው ይመለሳሉ ብለን የጠየቅናቸው ኃላፊው የክልሉ መንግሥት የአካባቢውን ፀጥታ ወደነበረበት ለመመለስ እየሰራ ነው በቀናት ውስጥም አገልግሎቱ ይጀመራል ብለውናል፡፡

በአማራ ክልል በጐንደር ከተማ አስቀድሞ የተነሳው ውዝግብ፣ ግጭትና ተቃውሞ አሁን መልክ በመያዙ የከተማው እንቅስቃሴ እንደነበር ሆኗል ሲሉም ነግረውናል፡፡ በአማራ ክልል የተቋረጡትን ትልልቅ የገንዘብ ተቋማትን በተመለከተም ሸገር አንዳንዶቹን ባንኮች አነጋግሮ ስራው መቋረጡን ማረጋገጥ ችሏል፡፡ አንዳንዶቹም የሥራ ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት በቀጠሮ ተለይተውናል፡፡

ተህቦ ንጉሴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ባለፈው የበጀት ዓመት ለድርቅ ተጐጂዎች 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ቶን ስንዴ መግዛቱን የመንግሥት ግዢ መሥሪያ ቤት እወቁልኝ አለ

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በድርቅ ለተጐዱ ዜጐች ከተገዛው 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ 410 ሜትሪክ ቶን ያህሉ የተገዛው ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር ነው ተባለ…

ከተፈፀመው 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ መካከል 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ያህሉ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ለተጐጂዎቹ መሰራጨቱን ሰምተናል፡፡

መንግሥት በዚህ አመት ከፈፀመው የ18 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ግዢ የ11 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ያህሉ ወጪ የተደረገው በድርቅ ለተጐዱ ዜጐች ለሚሆን የስንዴ ግዢ መሆኑን የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ተናግሯል፡፡

በአገልግሎቱ የግዢ ባለሙያ የሆኑት አቶ ወርቁ ገዛኸኝ እንዳሉት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በድርቅ ለተጐዱ ዜጐች የሚሆን 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዢ ተፈፅሟል፡፡

ከመካከሉም 410 ሜትሪክ ቶኑ የተገዛው ከዓለም ባንክ በተገኘ የ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ብድር ነው ብለዋል፡፡

በመንግሥት በጀት ደግሞ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ በ9 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ወጪ ግዢ መፈፀሙን ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ዘንድሮ ለካባ ተቆፍረው ሳይደፈኑ የቀሩ ጉድጓዶች ለ13 ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት መሆናቸወ ተሠማ

በአዲስ አበባ ለካባ ድንጋይ ማውጫ ተቆፍረው የተተዉ ጉድጓዶች ክረምት በገባ ቁጥር የሰው ህይወት እያጠፉ ነው፡፡ ዘንድሮም ለ13 ሰዎች ህይወት ህልፈት ምክንያት ሆነዋል ተባለ፡፡

መልሰው ሳይደፈኑ ቀርተው ውሃ እየታቆረባቸው ለሰዎች ሞት ምክንያት ሆነዋል የተባሉት የካ ወረዳ 11፣ ንፋስ ስልክ ሃና ማርያም አካባቢ፣ አቃቂ ወርቁ ሰፈር በተባለ ቦታ፣ ቦሌ ወረዳ 12 ቡልቡላ አካባቢ፣ ኮልፌ ቀራኒዬ ወረዳ 5 አጉስታ አካባቢ፣ የካ ወረዳ 10 ኮተቤ ሃና ማርያም አካባቢ፣ የካ ወረዳ 13 ጣፎ ኮንዶሙኒየም እንዲሁም ቦሌ ወረዳ 13 ሰላም ሰፈር የሚገኙ ጉድጓዶች ናቸው ተብሏል፡፡

የጉድጓዶቹ ብዛት 17 ሲሆን በተለይ አሁን ትምህርት ቤቶች ዝግ ስለሆኑ ታዳጊዎች ለዋና ብለው እንዳይገቡባቸው ወላጆች ቁጥጥር አድርጉ ተብላችኋል፡፡ እንዲህ ያለው የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለሥልጣን ነው፡፡ ጉድጓዶቹን ለሚቆፍሩ ፈቃድ ሰጪው የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ሲሆን በአስቸኳይ እናስደፍናለን የሚል ምላሽ ሰጥቶን እንደነበር ይታወሳል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በሺህዎች ከሚቆጠሩ ወጣቶች ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸው ተሠማ

ከ3 ሺ በላይ ወጣቶች ነሐሴ 13 እና 14 ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝና ከመንግሥት አካላት ጋር የሚወያዩበት መድረክ መዘጋጀቱን የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ተናገረ…

በዕለቱ ወጣቶቹ ለተሣትፏቸው፣ ተጠቃሚነታቸውና እንዲሁም ያጋጠሟቸውን ችግሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይናገራሉ ተብሏል፡፡ ወሬውን የሰማነው የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ለጋዜጠኞች ከሰጠው መግለጫ ላይ ተገኝተን ነው፡፡

የውይይቱ ተሣታፊዎችም ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ ሲሆን 30 በመቶዎቹ ሴቶች እንደሚሆኑ ሰምተናል፡፡

በገጠርና በአርብቶ አደር አካባቢዎች ያሉ ወጣቶች እንዲሁም አካል ጉዳተኛ ወጣቶች እንደሚገኙ በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አዲሱ አረጋ ተናግረዋል፡፡

ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ እድል መፈጠሩን የተናገሩት አቶ አዲሱ ወጣቶቹ ካላቸው ብዛት አንፃር ችግሮችን ለመፍታት ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅብን እናምናለን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ እርካታ ያልፈጠርንለት የሀገራችን ወጣት ብዙ ነው፡፡ እሱንም ለመፍታት ወገብ የሚያጐብጥ ሥራ ይጠብቀናል ብለዋል፡፡

ወጣቶቹን ስሜታዊ ሊያደርጉ የሚችሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መኖራቸውና እነሱን ትኩረት ሰጥቶ ለመቅረፍ እንሰራለን ብለዋል፡፡

ምስክር አወል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 3፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • በአዲስ አበባ ዘንድሮ ለካባ ተቆፍረው ሳይደፈኑ የቀሩ ጉድጓዶች ለ13 ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት መሆናቸወ ተሠማ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ለሰው ልጅ ምግብነት የሚውለው አሳ እና ቃሪያ ከውሾች ምግብ ጋር ተቀላቅለው ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ ሲሉ ተይዘዋል ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • በኦሮሚያ አካባቢዎች ሰሞኑን የታየው ተቃውሞ የሟቹ ቁጥር በክልሉ በኩል ገና አልታወቀም ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ንድፍ ይፋ ሆነ፡፡ ንድፉ ለአቪዬሽን ሙዚየም የሚሆን ቦታ ይኖረዋል ተብሏል፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • በባሕርዳር ከተማ የባንኮች አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጠ ነው ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • ወደ ኬንያ ሱዳን እና ጅቡቲ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሲጀመር ወደዛም ሥራ የመግባት ውጥን አለኝ የሚለው እና ማን ባስ የሚል ስሜ የተሰጠው ተቋም ልዩ የትራንስፖርት አገልግሎት ስለመጀመሩ ተናግሯል፡፡ ማን ባስ ትራንስፖርት አ/ማ የአክሲዬን ሽያጭም በቅርቡ እጀምራለሁ ያለ ሲሆን በሥራው ዙሪያ ኃላፊዎቹ ትናንት ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በሺህዎች ከሚቆጠሩ ወጣቶች ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸው ተሠማ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሥሯ የሚገኙ ቤተ-ክርስቲያኖች በፍልሰታ ፆም ወቅት ፀሎተ ምህላና የሰላም ትምህርት እንዲሰጡ ጠየቀች፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • ባለፈው የበጀት ዓመት ለድርቅ ተጐጂዎች 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ቶን ስንዴ መግዛቱን የመንግሥት ግዢ መሥሪያ ቤት እወቁልኝ አለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • ኢትዮጰያ ከኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች ወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ እየጨመረ ነው ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሳተላይት የሚሰራጭ የቴሌቭዥን ጣቢያ ለመክፈት የማመልከቻ ሰነድ ከገዙት መካከል የሥራ ኃሳባቸውን ዝርዝር ያቀረቡት 5ቱ ብቻ ናቸው ተባለ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በሳተላይት አማካይነት የሚሰራጭ የቴሌቭዥን ጣቢያ ለመክፈት የሚፈልጉ የሀገር ውስጥ ድርጅቶች የማመልከቻ ሰነድ እንዲወስዱ ጋብዞ ነበር፡፡

ድርጅቶቹ ማመልከቻውን ከወሰዱ በኋላ እስከ ሰኔ 30፣ 2008 ድረስ የፕሮጀክት ሰነዳቸውን እንዲያስገቡም የጊዜ ገደብ አስቀምጧል፡፡

የማመልከቻ ሰነዱን 28 የሀገር ውስጥ ድርጅቶች እንደወሰዱ በባለሥልጣኑ የመገናኛ ብዙሃን ምዝገባና ፍቃድ ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ሲሣይ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

የፕሮጀክት ሰነዱን አዘጋጅተው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለባለሥልጣኑ ያስገቡት ግን አምስት ድርጅቶች ብቻ እንደሆኑ ከአቶ ሙሉጌታ ሰምተናል፡፡

እነዚህ አምስት ድርጅቶች ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል፣ ድምፀ ወያነ ትግራይ፣ አርኪ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ እና ኢስት አፍሪካ ፊልም ፕሮዳክሽን እንደሆኑ ዳይሬክተሩ ነግረውናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ወንዝ ውስጥ የወደቁ ወይዘሮ ሕይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ቸርቸል ጐዳና አካባቢ በህገ-ወጥ መንገድ ለገበያ የቀረቡ 65 ጥንታዊ የብራና መፃህፍት ተገኙ ተባለ፡፡

በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የቅርስ ኢንቨንተሪ ደረጃ ማውጣት ዳይሬክተሩ አቶ ኤፍሬም አማረ ለሸገር ሲናገሩ በቅርቡ የፌዴራል ፖሊስ ባደረገው ክትትል ጥንታዊ የብራና መፃህፍቱን ያገኘው በስጦታ ዕቃዎች መሸጫ ሱቅ ውስጥ ነው ብለዋል፡፡

የብራና መፃህፍቱን ለገበያ ያቀረበው ግለሰብ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ እንደሆነም ሰምተናል፡፡

እነዚህ የብራና ፅሁፎች ባልተገባ መንገድ ለገበያ ሲቀርቡ ከጉራጌ ዞንና ከስልጤ 113 ጥንታዊ የብራና መፅህፍት ማይክሮ ፊልም ተቀርፀው መጥተዋል  ተብሏል፡፡

ከብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃህፍት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙት ኃላፊ አቶ እንዳለው አዳሙ ለሸገር ሲናገሩ 113ቱ የብራና ፅሁፎች በእስልምና ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ናቸው ብለዋል፡፡

ጥንታዊ የብራና ፅሁፎቹን ከተለያዩ መስጊዶች ነው በፊልም  ያሰባሰብነው ያሉት አቶ እንዳለው ባሉበት ስፍራ በጥንቃቄ አንዲጠብቁትም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተናል ብለዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 2፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ትላንት በባህርዳር ከተማ በተጠራው የተቃውሞ ህዝባዊ ሰልፍ ላይ የሰው ህይወት ጠፋ፤ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በሳተላይት የሚሰራጭ የቴሌቭዥን ጣቢያ ለመክፈት የማመልከቻ ሰነድ ከገዙት መካከል የሥራ ኃሳባቸውን ዝርዝር ያቀረቡት 5ቱ ብቻ ናቸው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በአዲስ አበባ ወንዝ ውስጥ የወደቁ ወይዘሮ ሕይወት አለፈ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በሕገ-ወጥ መንገድ ለገበያ ሊቀርቡ የነበሩ 65 የብራና መፃህፍት በፖሊስ መያዛቸው ተሠማ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ሰዎችን አጭበርብሮ ወደ 27 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት የወሰደው ግለሰብ የ5 ዓመታት የእሥራት ቅጣት ተፈረደበት፡፡ (ተክለማርያም ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በልተው ማደር የተሣናቸውን 20 በመቶ ያህል አዲስ አበቤዎች ለመደገፍ በአስተዳደሩ 450 ሚሊዮን ብር መመደቡ ተሠማ

ከአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መካከል 20 በመቶ የሚደርሱት ከድህነት ወለል በታች በሚባል የድህነት ደረጃ የሚኖሩ ናቸው ተባለ…

እነዚህ ዜጐች የምግብ ዋስትና ያልተረጋገጠላቸውና በልተው ማደር የከበዳቸው ናቸው ተብለዋል፡፡

የደሀ ደሀ የተባሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በልተው ማደር እንዲችሉ የከተማው አስተዳደር ከመጪው አመት ጀምሮ ለ10 አመት የሚዘልቅ የከተማ የምግብ ዋስትና መርሃ-ግብር ይጀምራል መባሉን ሰምተናል፡፡

ለዚህም 450 ሚሊዮን ብር መመደቡን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ግዛው ተናግረዋል፡፡

350 ሚሊዮን ብሩ ከዓለም ባንክ የተገኘ ብድር ሲሆን መቶ ሚሊየን ብሩን የኢትዮጵያ መንግሥት በጅቶታል፡፡

ኃላፊው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በመጪው 3 አመት ብቻ 66 ሺህ 150 ያህል የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በልተው ለማደር የሚያስችላቸው ገንዘብ በየወሩ ይሰጣቸዋል፡፡

እነዚህ ዜጎች ጧሪ ቀባሪ የሌላቸውና በጤናና በዕድሜ ምክንያት መስራት የማይችሉ አረጋውያን የሚሳተፉበት ነው ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ከደረጃ በታች ናችሁ የተባሉ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋሞች ተዘግተዋል ተባለ

በአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ በተደረገ ክትትል 21 የመንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛ ተቋሞች ተሰርዘዋል ተባለ፡፡የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የ2008 የሥራ ክንውኑን የተመለከተ ሪፖርቱ ላይ እንዳየነው በሀገር አቀፍ ደረጃ የ344 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ያሉበት ደረጃ በየአመቱ ተመልክቷል፡፡

በኦሮሚያ በ91 ማሰልጠኛ ተቋሞች ተፈትሸው 10ሩ እንዲዘጉ ተደርጓል ተብሏል፡፡በትግራይ 49፣ በደቡብ ክልል 53 እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር 8 የማሰልጠኛ ተቋማትን መመልከቱን የተናገሩት የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች በሁለቱ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከደረጃ በታች መሆናቸው የተለየ አንድ አንድ የማሰልጠኛ ተቋማት ተዘግተዋል ተብሏል፡፡

በትግራይ ከተዘጋው 1 ማሰልጠኛ በተጨማሪ 62ቱ ሥራ እየሰሩ በአንድ ወር ጊዜ የጐደላቸውን እንዲያሟሉ የተደረገ ሲሆን ሌሎች 11 ደግሞ ለ3 ወር ታግደዋል ተብሏል፡፡

ቴዎድሮስ ወርቁ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 29፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

 • በልተው ማደር የተሣናቸውን 20 በመቶ ያህል አዲስ አበቤዎች ለመደገፍ በአስተዳደሩ 450 ሚሊዮን ብር መመደቡ ተሠማ፡፡ (ትዕግስትዘሪሁን)
 • መንግሥት ከሀገር ውስጥ ሞባይል ገጣጣሚ ኩባንያዎች በመጪው ዓመት አርባ ሁለት ሚሊየን ዶላር አገኛለሁ ብሎ ተመኝቷል፡፡ ኩባንያዎቹ በበኩላቸው አቅማችን እየደከመ የኮንትሮባንድ ንግዱ ገበያውን እየተሻማን የተባለውን ገንዘብ ማምጣታችንን እንጃ እያሉ ነው፡፡ (ህይወትፍሬስብሃት)
 • መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በሀገራችን ተከስቶ የነበረው ድርቅ ያስከተለውን ተፅዕኖ ለመቀነስ ማህበራዊ ኃላፊነቴን እየተወጣሁ ነው አለ፡፡ (ንጋቱረጋሣ)
 • የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ሊዳሰሱ የማይችሉ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች እንዳይዘነጉና ከትውልድ ትውልድ ለማስተላለፍ ያግዛሉ ያላቸውን የጥናትና ምርምር ህትመቶችን አስመረቀ፡፡ (ምስክርአወል)
 • ከደረጃ በታች ናችሁ የተባሉ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋሞች ተዘግተዋል ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስወርቁ)
 • በአምራችና አገልግሎት ሰጭዎች ሥራ ላይ የሚውሉ አዳዲስ ደረጃዎች ወጡ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers