• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

መጋቢት 25፣2012/ ከአኗኗራችን ሁኔታና በምርመራ ሂደት ካለፉ ሰዎች ቁጥር አናሳነት አንፃር የከፋ ነገር የምንሰማው ገና ወደፊት ነው የሚል ስጋት አንዣብቧል

ከሶስት ሳምንት በፊት የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ተገኘ ተባለ፡፡ እያለ እያለ ዛሬ ላይ 35 ሰዎች መያዛቸው ምንም እንኳን የሞት አደጋ ባይኖርም ከሌሎች ሀገሮች አንፃር ይህ የቫይረሱ ስርጭት ዝቅተኛ የሚባል ነው፡፡ይሁንና ከአኗኗራችን ሁኔታ እና በምርመራ ሂደት ያለፉ ሰዎች ቁጥር አናሳነት አንፃር የከፋ ነገር የምንሰማው ገና ወደፊት ነው የሚል ስጋት አንዣብቧል፡፡

የስጋቱን ደረጃ ከፍ የሚያደርገው ደግሞ ምንም ዓይነት የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ሰዎችም በቫይረሱ መያዛቸው እንደሆነ መታዘብ ይቻላል፡፡ በዚህ ጉዳይ ማህሌት ታደለ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለሙያ አነጋግራለች፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 25፣ 2012/ የአዳማ ከተማ ፖሊስ ለኮሮና ቫይረስ በሚያጋልጥ ሁኔታ አገልግሎት ሲሰጡ በነበሩ ከ650 በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ወሰደ

የአዳማ ከተማ ፖሊስ ለኮሮና ቫይረስ በሚያጋልጥ ሁኔታ አገልግሎት ሲሰጡ በነበሩ ከ650 በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ወሰደ፡፡
ወንድሙ ሀይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 25፣ 2012/ የኮቪድ 19 ስርጭት በውጭ ምንዛሪ ገቢ ላይ የሚፈጥረውን ከፍተኛ ጫና ለመቋቋም...

የኮቪድ 19 ስርጭት በውጭ ምንዛሪ ገቢ ላይ የሚፈጥረውን ከፍተኛ ጫና ለመቋቋም የኢትዮጵያ መንግስት እስከ 2 ቢሊየን ዶላር ከአዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት አልያም ከለጋሽ ሀገራት ማግኘት ሊኖርበት ይችላል ተባለ፡፡

ተህቦ ንጉሴ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 25፣ 2012/ ከፍተኛ ጥንቃቄ ካልተደረገ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በኮሮና የሚያዝ ሰው ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር እንደሚችል ተነገረ

በኢትዮጵያ የኮሮና ታማሚዎች ብዛት 35 ደርሷል፡፡ ሆኖም ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ ካልተደረገ በጥቂት ጊዜ ውስጥ አሃዙ በከፍተኛ ሁኔታ ሊለወጥ እንደሚችል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስቧል፡፡


ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 25፣ 2012/ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በማንኛውም ጊዜ የካርድ አቅርቦቴን ስለማላቋርጥ አቅርቦት ይቋረጣል በሚል ስጋት አይግባችሁ ብሏል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለኤሌክትሪክ ፍጆታችሁ በኤሌክትሮኒክ ካርድ የምትጠቀሙ ደንበኞቻችን በማንኛውም ጊዜ የካርድ አቅርቦቴን ስለማላቋርጥ አቅርቦት ይቋረጣል በሚል ስጋት አላስፈላጊ ጭንቀት ውስጥ አትግቡ ብሏችኋል፡፡
ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 25፣2012/ በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላብራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 74 ሰዎች ውስጥ 6 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላብራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 74 ሰዎች ውስጥ 6 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ። በሐገራችን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 35 ደርሷል፡፡ ሁሉም ታማሚዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው። 
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 25፣ 2012/ የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት እና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ በአፍሪካ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸው ተሰማ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ጠዋት ከአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርልስ ሚሸን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በፌስቡክ ገፃቸው ይፋ ባደረጉት መልዕክት ነው ይህን የተናገሩት፡፡ወረርሽኙ በአፍሪካ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል ከአውሮፓ ህብረት ጋር ልንሰራ በምንችልባቸው መንገዶች ላይ መክረናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤትና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለአፍሪካ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ በመሆናቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመስግነዋል፡፡

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮቪድ - 19 ስርጭት ለሚያስከትላቸው ፈታኝ ሁኔታዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል አመራር ላይ ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡አፍሪካ ከቀውሱ በኋላ ሊያጋጥማት የሚችለውን የኢኮኖሚ መሰናክል ለማቋቋም የጋራ ጥረት እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡

 ዘከሪያ መሐመድ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 25፣ 2012/በሳኒታይዘር ምርት ሂደት ላይ ጥንቃቄና ትኩረት ያስፈልጋል ተባለ...እንዲህ ያለው የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ነው

ድርጅቱ ዛሬ በኢትዮጵያ እየተመረቱ ያሉ ሳኒታይዘሮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።ወደ ድርጅቱ ማረጋገጫ ለማግኘት ከመጡ ሀያ አምራቾች ስድስቱ ብቻ አስፈላጊውን መስፈርት ማሟላት እንደቻሉም ተናግሯል።72 ሰዓት መቆየት የሚጠበቅበት መያዣም ጥራቱን ሊጠብቅ ይገባል ተብሏል።

በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ 72 የሚደርሱ ሳኒታይዘር ለማምረት የተዘጋጁ ተቋማት እንዳሉ የተናገረው ድርጅቱ፣ ምርቱ የራሱ የአመራረት ሂደቶች ስላሉትና የባለሞያዎችንም እገዛ ስለሚሻ ሰዎች በዘፈቀደ በቤት ውስጥ ከማምረት ሊቆጠቡ ይገባል ተብሏል።በተለይ ከ50 ሊትር በላይ በቤት ውስጥ ማምረት አደጋ ስለሚያስከትል ጥንቃቄ ያስፈልጋል ተብሏል።ዩኒቨርሲቲዎችና የህክምና ተቋማት ሳኒታይዘርን የማምረት አቅም እንዳላቸው ያስታወሰው ድርጅቱ በበቂ ሁኔታ ፈትሸው ጥራቱ ላይ እንዲያተኩሩና በተቻለ መጠን ስለምርቱ ይዘት የሚገልፁ ዝርዝሮችን በማሸጊያው ላይ እንዲለጥፉ መክሯል።

ተጠቃሚዎችም እጃቸው ላይ ውሀም ሆነ ላብ ካለ ሳኒታይዘር ሊጠቀሙ አይገባም ምክንያቱም የሳኒታይዘሩ አቅም ይዳከማልና ብሏል።በጥራት ቁጥጥሩ ዙሪያ ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር እየሰራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጥራት ምዘና ድርጅት እስካሁን በአምራች ድርጅቶች ፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ የጥራት ምዘና እያካሄደ ሲሆን በቀጣዮቹ ሁለትና ሶስት ቀናት ከንግድ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ሁሉም ሳኒታይዘር አምራች ተቋማት ምርታቸውን እንዲያስመዝኑ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ዛሬ ካደረገው መግለጫ ጎን ለጎን ለማሳያነት ያመረታቸውን በርከት ያሉ ሳኒታይዘሮችን ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ማበርከቱን ተመልክተናል።ለሳኒታይዘር ምርቶች ጥራት መመዘኛ የሚያገለግሉ ሙሉ ቁሳቁሶች እንዳሉት የተናገረው የኢትዮጵያ ጥራት ምዘና ድርጅት አምራቾች ምርታችሁን ወደ ገበያ ከማውጣታችሁ በፊት ጥራቱን አስፈትሹ፣ ተገልጋዮች እጥረት እንዳይከሰት ሲልም ራሳችሁን በተሻለ ከኮሮና ቫይረስ ለመጠበቅ እጃችሁን ሙልጭ አድርጋችሁ ብትታጠቡ ይመረጣል ብሏችኋል።

ቴዎድሮስ ብርሃኑ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 25፣ 2012/ በጓንት ላይ እየታየ ያለው ተገቢ ያልሆነ አጠቃቀም ለኮሮና ቫይረስ ተዛማችነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስለሚኖረው ጥንቃቄ አድርጉ ተብሏል

በጓንት ላይ እየታየ ያለው ተገቢ ያልሆነ አጠቃቀም ለኮሮና ቫይረስ ተዛማችነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስለሚኖረው ጥንቃቄ አድርጉ ሲል የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ ሸገር የጓንትና የፊት መሸፈኛ ማስክ መጠቀም ያለባቸው እነማን ናቸው ሲል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን ጠይቋል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 25፣ 2012/ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዘው የሚፈፀሙ ጥፋቶችን በተመለከተ የሐገራችን ሕግ ምን ይላል?

ባህር ማዶ የተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ ወደ ሐገራችን መግባቱ ከተሰማ እለት ወዲህ ወረርሽኝን መከላከል የሚጠይቀውን የጋራ ኃላፊነት በሚፃረር መልኩ የተለያዩ ጥፋቶች ስለመፈፀማቸው እየሰማን ነው፡፡የሸቀጦችን ዋጋ ማናር በስፋት የተሰማው አንዱ ጥፋት ሲሆን፣ ከሰሞኑ ደግሞ ከለይቶ ማቆያ ሹልክ ብሎ የመውጣት ወሬ ተሰምቷል፡፡

ለመሆኑ በሐገር ላይ ይህን መሰል ፈተና በተጋረጠበት ወቅት የሚፈፀሙ እንዲህ ያሉ ጥፋቶችን በተመለከተ የሐገራችን ሕግ ምን ይላል? ሕይወት ፍሬስብሃት የሕግ ባለሞያ ጠይቃለች
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 24፣2012/ መስቀል አደባባይ ለህዝባዊ አደባባይነት በሚመጥን መልኩ ከመሬት በታች እስከ 1400 ተሽከርካሪ ለማቆም የሚያስችል የመኪና ማቆሚያ በዘመናዊ መልኩ ይገነባል

መስቀል አደባባይ ለህዝባዊ አደባባይነት በሚመጥን መልኩ ከመሬት በታች እስከ 1400 ተሽከርካሪ ለማቆም የሚያስችል የመኪና ማቆሚያ በዘመናዊ መልኩ ይገነባል።የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ከመስቀል አደባባይ ማዘጋጃ ቤት ደረስ የሚካሄደው መልሶ ማልማትና የአረንጓዴ ስፍራ ግንባታ ቅድመ ዝግጅት ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል።

ለመልሶ ማልማቱና አረንጓዴ ስፍራ የቦታ ዝግጅትና የወሰን ማስከበር ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማና የአዲስ አበባ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በጋራ ዝግጅቱን ተመልክተዋል።በመስቀል አደባባይ መልሶ ግንባታ ቦታው ለህዝባዊ አደባባይነት በሚመጥን መልኩ በዘመናዊ መልኩ የሚገነባ ይሆናል።ቦታው ላይ ከመሬት በታች እስከ 1400 ተሽከርካሪ ለማቆም የሚያስችል የመኪና ማቆሚያ ይገነባል።ፋውንቴንና የተለያዩ መዝናኛዎችን ባካተተ መልኩ የሚገነባው መስቀል አደባባይ መልሶ ግንባታው በለግሀር— ቸርችል አደባባይ እስከ ፒያሳ ድረስ በሚሰራው አረንጓዴ ስፍራ ፕሮጀክት ጋር የተያያዘ ነው።

ከመስቀል አደባባይ እስከ ፒያሳ ድረስ ያለው መንገድ ትይዩ በሆነ መልኩ የሚገነባ ሲሆን በመንገዶቹ ጠርዝ ያለው የእግረኞች መሄጃ ሰፋ ባለ መልኩ የሚገነባ ሲሆን ለአካል ጉዳተኞች እንዲመች ተደርጎ እንዲሁም የብስክሌት መጓጓዧን ባካተተ መልኩ ይገነባል።ፕሮጀክቱ ዲዛይኑ የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርብ ወደ ስራ ይገባል።በቀጣይም ይህን እንደመነሻ በመውሰድ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ የማስዋብ ስራዎች የሚተገበሩ ይሆናል።

ዓለማየሁ ግርማ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers