• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሕዳር 3፣ 2012/ አዲስ አበባ ኮተቤ አካባቢ ግንባታው የሚካሄደው መንገድ በቀጣዩ አመት ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ ኮተቤ አካባቢ ግንባታው የሚካሄደው መንገድ በቀጣዩ አመት ይጠናቀቃል፡፡
 • የወሰን ማስከበር ችግር ለመዘግየቱ ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 3፣2012/ አንዳንድ መድሃኒቶችንና የህክምና መሳሪያዎችን እንደተቸገረ የሀኪሞች ማህበር ተናግሯል

አንዳንድ መድሃኒቶችንና የህክምና መሳሪያዎችን እንደተቸገረ የሀኪሞች ማህበር ተናግሯል፡፡
 • መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ደግሞ የሉም የተባሉት መድሃኒቶች አሉ እያለ ነው፡፡

ወንድሙ ሀይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 3፣ 2012/ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአለም አቀፉ መገናኛ ብዙሃን CNN ለማስታወቂያ 60 ሺ የአሜሪካ ዶላር መድቤያለሁ ማለቱን ሸገር ሰምቷል

CNN አየር መንገዱን እና ኢትዮጵያን በአለም ለማስተዋወቅ ተመርጧል ተብሏል፡፡በ60 ሺህ ዶላርም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በአሜሪካ በሚገኘው እውቁ የቴሌቪዥን ቻናል Cable News Network (CNN) ይተዋወቃል ብለው ለሸገር የነገሩት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ናቸው፡፡

በCNN የቴሌቪዥን ቻናልም ስለ ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚነገር ማስታወቂያ ለ2 ወር በየቀኑ 3 እና 4 ጊዜ ይተዋወቃል ተብሏል፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከCNN ጋር በማስታወቂያው ጉዳይ እንዳልተፈራረመ ነገር ግን በሂደት ላይ እንዳለ አቶ ተወልደ ነግረውናል፡፡

ተህቦ ንጉሤ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 3፣2012/ በአዲስ አበባ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለልማት ስራ በሚል ከተማሪዎች ገንዘብ ይሰበስባሉ ወይንስ አይሰበስቡም?

በአዲስ አበባ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለልማት ስራ በሚል ከተማሪዎች ገንዘብ ይሰበስባሉ ወይንስ አይሰበስቡም? ንጋቱ ሙሉ በአዲስ አበባ ጎዳና ያጋጠመውን ተንተርሶ ይመለከታቸዋል ያላቸውን ጠይቋል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 3፣ 2012/ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአየር ካርጎ ጭነት በተጨማሪ በመልቲ ሞዳል ከባህር አንስቶ ያለውን አሰራር ጨምሮ በአውሮፕላን አንድ ላይ የተቀናጀ አገልግሎት ለመስጠት ማሰቡን ሰምተናል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዳዲስ የቢዝነስ ዘርፎች ለመጀመር አቅጄያለሁ ብሏል፡፡ ከአየር ካርጎ ጭነት በተጨማሪ በመልቲ ሞዳል ከባህር አንስቶ ያለውን አሰራር ጨምሮ በአውሮፕላን አንድ ላይ የተቀናጀ አገልግሎት ለመስጠት ማሰቡን ሰምተናል፡፡
 • ከሌላው አለም ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ቱሪስቶችም አጠቃላይ የጉብኝት ፓኬጅ ጀምሬያለሁ ወደ ስራ ገብቻለሁ ማለቱም ተሰምቷል፡፡

ተህቦ ንጉሴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 3፣ 2012/ የህፃናት አድን ድርጅት (Save the children) የኢትዮጵያ መንግስት በሳምባ ምች የሚሞቱ ህፃናትን ለመታደግ ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ

ድርጅቱ መንግስት በሳምባ ምች የሚሞቱ ህፃናትን እንዲታደግ መጠየቁን በላከልን መግለጫ ተናግሯል፡፡እንደ ድርጅቱ አባባል ከሆነ በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት 4 ልጆች በሳምባ ምች በሽታ ምክንያት በየአንድ ሰዓቱ ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡በዚህ ስሌት ባለፈው ዓመት ብቻ 32 ሺ ህፃናት መሞታቸው ተነግሯል፡፡

የሳምባ ምች በሽታ በባክቴሪያ፣ ቫይረስ አልያም በፈንገስ የሚመጣ ሲሆን የህፃናትን ሳምባ በፈሳሽ በመሙላት ለሞት የሚዳርግ በሽታ ነው፡፡ባሳለፍነው ዓመት እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ 17 በመቶ ህፃናትንም ለህልፈት በመዳረግ ቀዳሚውን ደረጃ ይዟል፡፡ኢትዮጵያም በዚህ የተነሳ በአለም አራተኛዋ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሳምባ ምች ሞት አሀዝ የተመዘገበባት አገር ሆናለች፡፡ጥናቶች የተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ህፃናት ይልቅ በዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ያሉ ህፃናት አምስተኛ አመታቸውን ሳያከብሩ እንደሚሞቱ ያሳያል፡፡ስለሆነም የህፃናት አድን ድርጅት ይህን ገዳይ በሽታ ለመቆጣጠር የማደርገውን ጥረት መንግስት ምንም ሳያወላዳ ሊያግዘኝ ይገባል ሲል ጠይቋል፡፡

ቴዎድሮስ ብርሃኑ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 2፣ 2012/ በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማትና የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄዱ የመሰረታዊ አገልግሎት መርሃ ግብሮች አፈፃፀም

በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማትና የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄዱ የመሰረታዊ አገልግሎት መርሃ ግብሮች አፈፃፀም በለጋሾችና በኢትዮጵያ መንግስት በጋራ እየተገመገሙ ነው፡፡
 • ትምህርት፣ ጤና እና ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ዋንኛ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፡፡
የጋራ ግምገማውን ተስፋዬ አለነ ተከታትሏል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 2፣ 2012/ ኢግልድ በዱቤ ለወሰዱት ግብአት ገንዘብ ያልከፈሉኝን ፋብሪካዎች ሕግ ፊት አቅርቤያለሁ አለ

ኢግልድ ከስሬያለሁ ብሎ ባለሀብቱ ጥሎት የወጣው አይካ አዲስ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን ጨምሮ በዱቤ ለወሰዱት ግብአት ገንዘብ ያልከፈሉኝን ፋብሪካዎች ሕግ ፊት አቅርቤያለሁ አለ፡፡
 • ካበደረው 262 ሚሊየን ብሩ አልተመለሰለትም፡፡
 • ከዚህም ውስጥ ትልቁን ድርሻ የያዘው ከስሬያለሁ ብሎ ባለሐብቱ ከሐገር የወጣው የቱርኩ አይካ አዲስ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ነው ብሏል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 2፣ 2012/ ባለፈው አመት 2 ጊዜ የእሳት ቃጠሎ ያጋጠመው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከአለም አቀፉ የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት ዩኔስኮ የ74 ሺ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ እንደተመደበት ተሰምቷል

የፓርኩ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አበባ አዛናው ለሸገር ሲናገሩ ለባለሙያዎች ስልጠና ለመስጠትና ለቁሳቁስ ማሟያ የሚውል 74 ሺ የአሜሪካ ዶላር ከዩኔስኮ ለሰሜን ፓርክ ተብሎ ተልኳል፡፡ ገንዘቡ የእሳት አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ ለመቆጣጠር የሚያስችል ስልጠና ለመስጠት፣ ፓርኩን ለማልማት እና ለመንከባከብ የሚያግዝ ነው ቢባልም በአፈፃፀም በኩል የታየ ክፍተት ችግር ፈጥሯል ይላሉ አቶ አበባው፡፡ ዩኔስኮ 74 ሺህ ዶላሩን በተለይ ለሰሜን ፓርክ የሰጠ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ ዱር እንሰሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ለሌሎች ፓርኮችም አውለዋለሁ የሚል ሀሳብ ማምጣቱ ግራ አጋብቶናል ብለውናል አቶ አበባው፡፡

የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በአለም አቀፉ የትምህርት የሳይንስ የባህል ድርጅት ዩኔስኮ የተመዘገበ እና በተቋሙም ድጋፍ የሚደረግለት መሆኑን የሚናገሩት አቶ አበባው ድርጅቱ ንብረቱ ለሆነው ለሰሜን ብሔራዊ ፓርክ የሰጠውን ገንዘብ ለሌሎች ፓርኮች መጠቀም እንደማይቻል ያስረዳሉ፡፡የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ባለፈው አመት ባጋጠመው የእሳት ቃጠሎ አደጋ የተጎዳው ክፍል ሙሉ በሙሉ ማገገሙን አቶ አበባው ለሸገር ተናግረዋል፡፡በእሳት ቃጠሎ ጉዳት አጋጥሞት የነበረው አብዛኛው የፓርኩ ክፍል የሳር ምድር በመሆኑና በክረምት ወቅት የተከናወነው የችግኝ ተከላ ፓርኩ ከደረሰበት ጉዳት እንዲያገግም ማገዙን አቶ አበባው ነግረውናል፡፡የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት ጭላዳ ዝንጀሮ፣ ዋሊያ አይቤክስና ቀይ ቀበሮን ጨምሮ ሌሎች የዱር እንስሳት መገኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 2፣ 2012/ በመሬት ልማትና ማኔጅመንት፣ በግንባታ ፍቃድ አሰጣጥ እና በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ዙሪያ በአስር ከተሞች የተካሄደ የዳሰሳ ጥናት ነዋሪዎች ብዙም እርካታ እንደሌላቸው ማሳየቱ ተነገረ

በመሬት ልማትና ማኔጅመንት፣ በግንባታ ፍቃድ አሰጣጥ እና በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ዙሪያ በ10 ከተሞች የተካሄደ የዳሰሳ ጥናት ነዋሪዎች ብዙም እርካታ እንደሌላቸው ማሳየቱ ተነገረ፡፡
 • የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ለእነዚህ እና ሌሎችም የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ሐገር አቀፍ ደረጃ እያዘጋጀሁ ነው ብሏል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 1፣ 2012/ የወልዲያው ግጭት፣ ግጭቶችን የጎሳ ቀለም የመቀባት ጥረት እና የግጭት ቀስቃሾች በጎሳ ሥር የመደበቅ ሙከራዎች

ሸገር በወልዲያ ተከሰተ የተባለውን ግጭት መነሻ አድርጎ የሚከሰቱ ግጭቶችን ሁሉ የጎሳ ቀለም ለመቀባት፣ አልያም ግጭት ቀስቅሰው በጎሳ ለመደበቅ የሚደረጉ ሙከራዎችን ለመቆጣጠር ምን መደረግ አለበት ? ሲል የሕግ ባለሞያዎችን ጠይቋል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers