• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትናንትናው ዕለት በዋይት ሐውስ ከአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት ማይክ ፔንስ ጋር ተነጋግረዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትናንትናው ዕለት በዋይት ሐውስ ከአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት ማይክ ፔንስ ጋር ተነጋግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ ዲሞክራሲ የምታደርገውን ሽግግር አስመልክተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን እንኳን ደስ ያሎት ያሉት ምክትል ፕሬዝደንት ፔንስ ሐገራቸው የኢትዮጵያን ልማት ለመደገፍ ቁርጠኛ ነች ብለዋል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በቅርቡ ካወያዩአቸው 400 የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ተመራቂዎች መካከል ሃምሳዎቹ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የትምህርት እድል ሊያገኙ ነው ተባለ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በቅርቡ ካወያዩአቸው 400 የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ተመራቂዎች መካከል ሃምሳዎቹ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የትምህርት እድል ሊያገኙ ነው ተባለ፡፡ይህን ያሉት የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ሀላፊው አቶ ፍጹም አረጋ ናቸው፡፡ አቶ ፍፁም እንዳሉት ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ለ50 የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የትምህርት እድል ለመስጠት ወስናለች፡፡

የትምህርት እድሉ የወደፊቷ ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ለውጥ ላይ ለለውጡ አጋዥ የሚሆን ትውልድ ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት መሆኑን ጽህፈት ቤቱ ተናግሯል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በቅርቡ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎችን ያወያዩ መሆናቸውን ያስታወሰው ጽህፈት ቤቱ ተማሪዎች ከተለምዷዊ አሰራር ወጥተው ማህበረሰባቸውን ማገልገል ላይ ትኩረት እንዲሰጡ መናገራቸውን ተናግሯል፡፡ከተወያዮቹ መሀከል 50 የሚሆኑት የዚህ እድል ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጽህፈት ቤቱ ሰምተናል፡፡

አስፋው ስለሺ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ነዋሪዎች ለመናፈሻ የተተወ ቦታ ላይ ቆሻሻ እየተጠራቀመ መቸገራቸውን ተናገሩ

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ነዋሪዎች ለመናፈሻ የተተወ ቦታ ላይ ቆሻሻ እየተጠራቀመ መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ለአምስት አመታት ያህል ለወረዳው አቤት ቢሉም ሰሚ ማጣታቸውን ከነዋሪዎች ሰምተናል፡፡ቆሻሻ ከተለያዩ አካባቢዎች በማሰባሰብ ይጠራቀምበታል ያሉት ነዋሪዎች ከቆሻሻው መጥፎ ጠረን በተጨማሪ ፍሳሽ ወደ ጊቢ እየገባብን ተቸግረናል ብለዋል፡፡

አንዳንድ ነዋሪዎችም ከመቸገራቸው የተነሳ ወደ ሌላ አካባቢ በመሄድ መከራየታቸውን ሰምተናል፡፡ስለ ችግሩ እውነትነት የተናገሩት በወረዳው የምግብና መድሃኒት ጽ/ቤት ሀላፊው አቶ ዮናስ ከበደ ችግሩን ለመፍታት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ከመስከረም ወር በኋላ አካባቢው ከቆሻሻ ማከማቻነት ነፃ እንደሚወጣም ነግረውናል፡፡በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታትም ክፍለ ከተማው በጀት ይዞ እየሰራ መሆኑንም ሰምተናል፡፡

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ሀላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ጌታቸው ትናንት ምሽት ሕይወታቸው ማለፉ ተነገረ

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ሀላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ጌታቸው ትናንት ምሽት ሕይወታቸው ማለፉ ተነገረ፡፡በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የርዕሰ መስተዳድሩ የህዝብ ግንኙነት እና አደረጃጀት አማካሪ የነበሩት አቶ ተስፋዬ በአሜሪካ የህክምና ክትትል ለማድረግ በሄዱበት ሕይወታቸው ማለፉን የነገሩን የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊው አቶ ንጉሱ ጥላሁን ናቸው፡፡የብአዴን እና የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ በአማራ ክልል የተለያዩ ቢሮዎች በሀላፊነት ማገልገላቸውንም ሰምተናል፡፡

ማህሌት ታደለ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በመንግሥት ከፍተኛ ድጎማ የሚቀርበውን ስንዴ እየወሰዱ በዳቦ ላይ ዋጋ በሚጨምሩ እና ግራም በሚቀንሱ አምራቾች ላይ እርምጃ እንደሚወስድም ተናግሯል

በመንግሥት ከፍተኛ ድጎማ የሚቀርበውን ስንዴ እየወሰዱ በዳቦ ላይ ዋጋ በሚጨምሩ እና ግራም በሚቀንሱ አምራቾች ላይ እርምጃ እንደሚወስድም ተናግሯል፡፡ የንጋቱ ረጋሳን ዝርዝር ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአሜሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን “ኢትዮጵያን እንገንባ” ሲሉ ጥሩ አቀረቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአሜሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን “ኢትዮጵያን እንገንባ” ሲሉ ጥሩ አቀረቡ… ንጋቱ ሙሉን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ንግድ ሚኒስቴር የዳቦ ስንዴ አቅርቦት ችግር እንዳለ በማስመሰል ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ጠቁሙኝ አለ

ንግድ ሚኒስቴር የዳቦ ስንዴ አቅርቦት ችግር እንዳለ በማስመሰል ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ጠቁሙኝ አለ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

185 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከጅቡቲ ወደ አገራቸው መግባታቸው ተሰማ

185 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከጅቡቲ ወደ አገራቸው መግባታቸው ተሰማ፡፡ትላንትና ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት 185 ስደተኞች በደላሎች አማካይነት በህገ-ወጥ መልኩ በጂቡቲ በኩል ወደተለያዩ አረብ አገራት ለመሄድ ጅቡቲ የገቡ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ቢሮ ተናግሯል፡፡ስደተኞቹ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው የተመለሱት በጅቡቲ በሚገኘው የኢትትዮጵያ ኤምባሲ እና በአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት በጋራ ባደረጉት ጥረት መሆኑንን ሰምተናል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የመንግስት የልማት ድርጅቶች በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ ሶስት ቢሊየን ብር የሚጠጋ ትርፍ ማግኘታቸው ተነገረ

የመንግስት የልማት ድርጅቶች በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ ሶስት ቢሊየን ብር የሚጠጋ ትርፍ ማግኘታቸው ተነገረ፡፡በመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ባለፈው በጀት ዓመት 2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ማትረፋቸው ተነገረ፡፡ የልማት ድርጅቶቹ ለማትረፍ አቅደው የነበረው 3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ነው ተብሏል፡፡

የሕንጻ ዕቃዎች አቅራቢ ድርጅት፣ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከተገኘው ትርፍ ከፍ ያለውን ድርሻ አበርክተዋል ተብሏል፡፡የልማት ተቋማቱ 37 ቢሊዮን ብር ግምት ያለው ምርትና አገልግሎት ሽያጭ በበጀት ዓመቱ ማከናወናቸውም ተሠምቷል፡፡

ከሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል አብዛኞቹ የስኳር ፕሮጀክቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውንም የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንዳፍራሽ አሠፋ ተናግረዋል፡፡የጣና በለስ ቁጥር-1፣ የኦሞ-ኩራዝ ቁጥር-5 እና የወልቃይት ምዕራፍ-2 አፈጻጸም ግን ከ40 በመቶ በታች ነው ብለዋል፡፡በ2011 በጀት ዓመት ኦሞ-ኩራዝ 5፣2፣3፤ ጣና በለስ-1 እና ወልቃይት ምዕራፍ-1 በአጠቃላይ አምስት የስኳር ፕሮጀክቶች ይጠናቀቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ነግረውናል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶሶች በጋራ ባለመስራታቸው ኢትዮጵያ ብዙ ትርፍ አጥታለች አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶሶች በጋራ ባለመስራታቸው ኢትዮጵያ ብዙ ትርፍ አጥታለች አሉ፡፡በሐገር ቤትና በውጭ የሚገኙት ሲኖዶሶች ትናንት በአሜሪካ ዋሽንግተን ባካሄዱት የውይይት መድረክ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ባለታላቅ ሥምና ታሪክ የሆነችና ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውጪ አትታሰብም ብለዋል፡፡

በቤተ ክርስቲያኒቱ የተፈጠረው ችግር ለረዥም አመታት ሳይፈታ በመቆየቱ የኢትዮጵያውያን ሰላም ሲሸረሸር ቆይቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ችግሩ የሁሉንም ኢትዩጵያውያን ቤት አንኳኩቷል ብለዋል፡፡የሁለቱ ሲኖዶሶች ውይይት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ቀጥሎ ይካሄዳል የተባለ ሲሆን በተመሳሳይ ፕሮግራሞች በፖለቲካ፣ ብሄርና ሀይማኖት የተጣሉ ወገኖችን የማስታረቅ ሥራዎች እንደሚሰሩም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢንጂነር ስመኘው በቀለ የቀብር ሥነሥርዓት መራዘሙን የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴው ገለፀ

በትላንትናው ዕለት ማለዳ በመስቀል አደባባይ በጥይት ተመትተው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት የኢንጂነር ስመኘው በቀለ የቀብር ሥነሥርዓት መራዘሙን የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴው ገለፀ፡፡
የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴው የቀብር ሥነሥርዓቱ የሚፈፀምበትን ቀን በሚቀጥሉት ቀናት እንደሚያስታውቅ ተናግሯል፡፡

የኢንጂነር ስመኘው በቀለ የቀብር ሥነሥርዓት ቤተሰቦቻቸው፣ በርካታ ሕዝብ እንዲሁም ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት እንደሚፈፀም ይጠበቃል፡፡ከዚሁ ጋር በተያያዘ … በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ለመወያየት ወደ አሜሪካ ያመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኢንጂነር ሥመኘው ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልፀዋል፡፡አሜሪካ እንደደረሱ ይህን አሳዛኝ ዜና መስማታቸውን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለኢንጂነር ስመኘው በቀለ ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers