• Slider One

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ጃርቲ ተሽሏት ወደ ሐገሯ ልትመለስ ነው

በምስሉ ላይ የምትታየው የዚህች ሴት ታሪክ የዛሬ ዓመት በሸገር ልዩ ወሬ ተዳስሶ ነበር፡፡ ያኔ የአእምሮ ሕመምተኛ የነበረችው ጃርቲ አዲስ አበባ ጉለሌ ንግድ ባንክ አካባቢ ጎዳና ላይ በአሳዛኝ ሁኔታ የውሻ ቡችሎች እያጠባች ትኖር ነበር፡፡ ፕሮግራሙን ያዳመጡ ሰዎች ጉዳዩን እንጦጦ ላለው የጌርጌሴኖን የአእምሮ ሕመምተኞች መረጃ ድርጅት መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ሲነግሩ የጃርቲ ታሪክ ተቀየረ፡፡ ድርጅቱ ጃርቲን ወስዶ ተንከባክቦ አሳክሞ አሁን ላይ ጃርቲ ጤናዋ ተመልሶ ስለቀድሞ ሕይወቷ ለልዩ ወሬ አዘጋጁ ለወንድሙ ኃይሉ አጫውታዋለች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ረቡዕ ሰኔ 1፣2008 የሸገር ወሬዎች

 • የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን በጣም ለረጅም ዓመታት በተስፋ ሲያስጠብቅ የነበረውን አውራ ጎዳናዎች ዛሬ በይፋ ማጠናቀቄን እወቁልኝ ማለቱ ተሰምቷል፡፡
 • የቆመ መኪና ሰርቆ ሊሄድ ሲል የተያዘው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውሎ በህግ ተጠየቀ፡፡
 • በሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት እና ፖሊስ ኮሚሽን ጊቢ ውስጥ የነበሩ አንበሶችና አቦሸማኔዎች ወደ መናገሻ እየተጓዙ ነው፡፡
 • የኤሌክትሪክ ቆጣሪ አንባቢ ነኝ ብሎ ወደ ሌሎች ሰዎች ቤት በመግባት የውንብድና ሙከራ የፈፀመው ግለሰብ በእሥራት ተቀጣ፡፡
 • ምግብን፣ መድኃኒትንና የጤና ባለሞያዎችን ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ሊከለስ ነው፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለ16 ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን መደበኛ ጉባዔ ውሣኔ በማሣለፍ አጠናቋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቅዱስ ሲኖዶስ የተነጋገረባቸውን ጉዳዮች በመግለጫ መልክ ዛሬ ረፋድ ላይ ለጋዜጠኞች ሰጥተዋል፡፡ ከግንቦት 16 እስከ ዛሬ ሰኔ 1 ቀን ድረስ የተካሄደው ይህ ጉባዔ ለፓትሪያርኩ እንደራሴ ያስፈልጋል በሚለው ጉዳይ ላይ ሲመክር ሰንብቶ የእንደራሴውን አመራረጥና የቆይታ ጊዜ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን ያካተተ ህግ ተሰናድቶ ለመጪው ጥቅምት የሲኖዶስ ጉባኤ እንዲቀርብ ወስኗል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ-መብት

በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ላይ ያሉት የመልካም አስተዳደር ችግሮች የዜጐችን ሰብዓዊ መብት የሚጥሱ በመሆናቸው ከቀድሞ በተሻለ መንገድ ለመሥራት እየጣረ መሆኑን  ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ተናገሩ…የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለሁሉም የህብረተሰቡ ክፍል ስለ ሰብዓዊ መብት የማስተማር፣ ችግር ሲቀርብም ምርመራ አድርጐ የመፍትሄ ኃሳቦችን ማቅረብና በዘርፉ ላይ መንግሥትን ማማከር ዋና ሥራ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር በአገሪቱ ያለው የመልካም አስተዳደር ችግር ካልተቀረፈ በዜጐች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይኖራል ብለዋል፡፡ በህገ-መንግሥቱ ሩብ ያህሉ ድንጋጌ ስለ ሰብዓዊ መብት ያትታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት

የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት እክል አለበት የተባለ የኦዲት ሪፖርት ግኝት ዳግም እንዲያስመረምር ቢጠየቅም እስካሁን ተግባራዊ አላደረገም ተባለ የበጐ ምግባር ችግርም ኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራው ላይ ትኩረት እንዳይሰጥ አድርጐታል ተብሏል፡፡ኢንስቲትዩቱ ለሌሎች አርአያ መሆን ያለበት ቢሆንም ለዘመናት አብሮት የቆየው የበጐ ምግባርና አመለካከት ችግር አንቆ ይዞታል ሲባል የሰማነው በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ የኢንስቲትዩቱን የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም በመረመረበት ወቅት ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐያሲ አብደላ እዝራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በኢትዮጵያ የሥነ ፅሁፍ ታሪክ ለረጅም ዓመታት በሐያሲነት የሰራው አብደላ እዝራ በትላንትናው ዕለት በ58 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ በዛሬይቱ ኢትዮጵያና በአዲስ ዘመን ጋዜጦች እንዲሁም የደራሲያን ማሕበር በሚያሳትመው ብሌን መፅሔት ላይ ለበርካታ ዓመታት የሒስ ስራዎቹን አቅርቧል፡፡ ከታላላቅ ቀደምት የኢትዮጵያ ፀሐፍት እስከዛሬ ወጣት ደራሲያን ድረስ የአብደላ የሂስ ብዕር የኢትዮጵያን ሥነ ፅሁፍ በጥልቀት ቃኝቷል፣ ተችቷል፣ አቅጣጫ ጠቁሟል፡፡ ከዛሬ 2 ዓመታት ጀምሮ ደግሞ አብደላ እዝራ የሒስ ስራዎቹን በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በተከታታይ ለአንብብያን እያቀረበ ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 26፣2008 የሸገር ወሬዎች

ግንቦት 26፣2008 የሸገር ወሬዎች

 • በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለጋር መጠቀሚያነት የተገነቡ ቤቶች 90 በመቶዎች ተከራይተዋል ተባለ፡፡
 • ኢትዮጵያን ጨምሮ በታዳጊ ሀገሮች ከአጠቃላይ ሀገራዊ አመታዊ ምርት ከ1 እስከ 5 በመቶ በተሽከርካሪ አደጋ ምክንያት ይጠፋል ተባለ፡፡
 • የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ከስህተቶቼ እታረማለሁ አለ፡፡
 • በኢትዮጵያ በዘመናዊ ባርነት ዓይነት የሚኖሩ ሠራተኞች እና ህፃናት ቁጥር ከፍተኛ ነው ተባለ፡፡
 • የሶማሌና የአፋር እንዲሁም የኦሮምያና ሶማሌ ድንበር ማካለል ሥራ በዚህ አመት ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 29፣2008 የሸገር ወሬዎች

ግንቦት 29፣2008 የሸገር ወሬዎች

 • አንበሶችና አቦሸማኔዎች በህገ-ወጥ መንገድ እየታደኑ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ይወሰዳሉ ተባለ፡፡
 • በኮተቤ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ትናንት የደረሰ ጢስ በአራት ተማሪዎች ላይ የጤና እክል ፈጠረ፡፡
 • መንግሥት በተለያዩ ግዜያት በዘረፋና በሌሎች አጋጣሚዎች ከኢትዮጵያ የኮበለሉ ቅርሶችን ለማስመለስ ለምትንቀሳቀሱ ቡድኖችና ግለሰቦች ከጎናችሁ አለሁ ብሏችኋል፡፡ በራሴ ያሉበትን ያወቅኳቸውን ለማስመለስ ጥረት እያደረኩ ነው ብሏል፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኮቸኔል ተባይ ጣጣ

የኮቸኔል ተባይ ጣጣ

ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያስገኛል በሚል በበለስ ተክል ላይ እንዲራባ የተደረገው ኮቸኔል የተባለው ተባይ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ በሽታው ከደቡብ ትግራይ ወደ ምስራቅ ትግራይ እየተስፋፋ ነው ተባለ…የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ከአንድ የውጭ ሐገር ዜጋ ጋር በመሆን የተገበረውና የበለስ ምርትን ኢኮኖሚያው ጥቅም ይጨምራል የተባለው ተባይ ነው አሁን ላይ በሽታ አስከትሎ በአስጊ ሁኔታ እየተስፋፋ ያለው፡፡ኮቸኔል የተባለው ተባይ በበለስ ቅጠል ላይ እንዲራባ ሲደረግ የበለሱ ቀለም እንዲለወጥ ያደርጋል፡፡

ድምፃዊ መስፍን አበበ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ድምፃዊ መስፍን አበበ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አሳዛኝ ዜና

Mesfin Abebe መስፍን አበበእንጋፋው ድምፃዊ መስፍን አበበ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ… ያዥልኝ ቀጠሮ፣ አይሽ አይሽና፣ መልካም ልደትና ሌሎችም ተወዳጅ ሙዚቃዎችን በጊታር በመጫወት የሚታወቀው ድምፃዊ መስፍን አበበ ትናንት በድንገተኛ ህመም ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ዛሬ ከንጋቱ 11 ሰዓት ገደማ ህይወቱ ማለፉን ከቤተሰቦቹ ሰምተናል፡፡

መስፍን አበበ ከደሴ ወ/ሮ ስህን ትምህርት ቤት ባንድ ጋር በመሆን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በመዘዋወር ሙዚቃዎችን ይጫወት ነበር፡፡ ቦክስ ጊታሩን በመያዝ 22 ያህል ካሴቶችን ማሳተሙን ከቤተሰቦቹ ተነግሮናል፡፡ ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባት የነበረው የድምፃዊ መስፍን አበበ የቀብር ስነ-ሥርዓት ነገ ከቀኑ በ6 ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያ ይፈፀማል ተብሏል፡፡

ሸገር ለድምፃዊ መስፍን አበበ ቤተሰቦች ዘመድ ወዳጆችና አድናቂዎች በሙሉ መፅናናትን ይመኛል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

የጋራ መኖሪያ ቤቶች 20/80 40/60 ፕሮግራም

ሥራቸው ቀደም ብሎ የተጀመሩት የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የግንባታ ደረጃ ከ93 ከመቶ በላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ተናገሩ...በ20/80 ፕሮግራም ግንባታ ከተጀመረላቸው 132 ሺህ ሰባት መቶ ሁለት ቤቶች መካከል 39 ሺህ ያህሉ የግንባታ አፈፃፀማቸው ከ93 ከመቶ በላይ ደርሷል ያሉት ከንቲባ ድሪባ ኩማ በ2006 እና 2007 በጀት ዓመት የተጀመሩ የ20/80 ፕሮግራም ቤቶች 44 በመቶ ተገንብተዋል ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ መደበኛ ጉባዔውን ባካሄደበት ወቅት የከተማውን የ9ኝ ወር ሪፖርት በከንቲባው አማካኝነት ሲያቀርብ ነው ይህንን የሰማነው፡፡ አዲስ አበባ ከሚገነቡላት የ40/60 ፕሮግራም ቤቶች መካከል 1 ሺህ 292ቱ ቤቶች 94 ነጥብ 8 በመቶ ያህል ተጠናቀዋል ተብሏል፡፡ በተለያዩ ወቅቶች የተጀመሩ ቤቶች እንደመሆናቸው የግንባታ ሁኔታቸው እንደሚለያይም ተነግሯል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers