• Slider One

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ህጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን ለማስጀመርም ከሳዑዲ አረቢያና ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ሃገሮች ጋር የሁለትዮሽ ስምምነቱ እስካሁን አልተደረገም ተባለ

ህጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን ለማስጀመርም ከሳዑዲ አረቢያና ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ሃገሮች ጋር የሁለትዮሽ ስምምነቱ እስካሁን አልተደረገም ተባለ…ስምምነቱ እስካልተፈረመ ድረስ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ መጀመሪያ ጊዜ ቁጥር ያለው የጊዜ ሰሌዳ የለም መባሉን ሰምተናል፡፡ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳዑዲ አረቢያና ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ሀገሮች የይሁን ፊርማ እየጠበቅኩ ነው ብሏል፡፡

ከዛሬ ነገ በቅርቡ ይጀመራል ሲባል የነበረው የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪቱ እስካሁን ለምን ዘገየ ተብለው የተጠየቁት በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሚንስትር ድኤታ አቶ ዳመነ ዳሮታ ከአገረብ ሀገሮቹ ጋር በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የድርድር ሰነድ ተላልከን መልስ እየጠበቅን ነው ብለዋል፡፡ሥራውንም ለማስጀመር የሀገራቱ ውሣኔ እና ፈቃድ ነው እንጂ የሚፈቀደው እኛ ስለፈለግን ብቻ የሚሆን አይደለም ሲሉ ሚኒስትር ድኤታው ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በእፅዋት ዝርያ ምዝገባ የዘር ጥራትና ቁጥጥር አሰራር ሥርዓቱ የኢትዮጵያን ግብርና አደጋ ላይ የጣለ ነው ተባለ

በእፅዋት ዝርያ ምዝገባ የዘር ጥራትና ቁጥጥር አሰራር ሥርዓቱ የኢትዮጵያን ግብርና አደጋ ላይ የጣለ ነው ተባለ፡፡እንዲህ የተባለው ዛሬ በይፋ ሥራውን በጀመረው የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ምክር ቤት ጉባዔ ላይ ነው፡፡የምክር ቤቱ ሰብሣቢ ዶክተር ካሱ ኢላላ እንዳሉት የዝርያ ምዝገባና ቁጥጥር ሥርዓቱ ግልፅ ሆኖ አለመቀመጡ እና ባለቤት ያጣ በሚመስል መልኩ መገኘቱ በግብርና ሥርዓቱ ላይ አደጋ እንዲያንዣብብ አድርጓል፡፡የምርምር ሥርዓቱ ወደ አዲስ የምርምር ሥርዓት እንዳይገባም እንቅፋት ሆኗል ያሉት ዶክተር ካሱ ምርምሩ ከውጭ በሚገቡ የግብርና ተባዬች እና በሽታዎች ላይ እንዲጠመድ አድርጐታል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኀዳር 20፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

 • ከአረብ አገሮች ጋር የሁለትዮሽ ስምምነቱ ጉዳይ ዳር እስከሚደርስ ድረስ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የውጭ የሥራ ሥምሪት እንደማይኖር የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዕወቁት አለ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
 • የቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአይን ህክምናን መስጠት ልጀምር ነው አለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • ኢትዮጵያ ከሁለት መቶ በላይ የአሳ ዝርያዎች ቢኖሯትም በተለያዩ ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተመናመኑ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ለአለም የማይዳሰስ ቅርስነት ክብር ይገባቸዋል ተብለው ከየአገሪቱ ተመርጠው 37 የማይዳሰሱ ቅርሶች ለአዲስ አበባው 11ኛ የዩኔስኮ ጉባዔ ቀርበዋል፡፡ (ምስክር አወል)
 • በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐር ቪዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን የውሃ ኤነርጂ ዲዛይንና ቁጥጥር ዘርፍ ባለፉት ሦስት ወሮች ካከናወንኳቸውና እየሰራሁም ካለሁት ሥራ 120 ሚሊዮን ብር አገኘሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • 2ኛው ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ-ግብር ረቂቅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴዎች እየተመከረበት ነው፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የዝርያ ምዝገባና ቁጥጥር ሥርዓቱ ወጥነት የጐደለው መሆኑ በኢትዮጵያ ግብርና ላይ ስጋት መጋረጡ ተነገረ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በማንኛውም ሁኔታ ለውጭ ኩባንያ አይተላለፍም ተባለ፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • ባለቤቱን የገደለው በእሥራት ተቀጣ፡፡ (ምህረት ስዩም)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አስራ አንደኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ጥበቃ የበይነ መንግሥታት ኮሚቴ ጉባዔ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፈተ

አስራ አንደኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ጥበቃ የበይነ መንግሥታት ኮሚቴ ጉባዔ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፈተ፡፡በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ የተከፈተው ጉባዔ ዛሬን ጨምሮ ለአምስት ቀናት እንደሚቆይ ሰምተናል፡፡በአምስቱ ቀናት ጉባዔም በአለም የማይዳሰስ ቅርስነት ተመዝግበው ነገር ግን አፋጣኝ ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል ተብለው በተለዩ ቅርሶች ላይ የተሰሩ ሥራዎች ሪፖርት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት ለመመዝገብ የቀረቡ ቅርሶች ላይ ግምገማ እንደሚካሄድም ሰምተናል፡፡ለመመዝገብ ከቀረቡት 37 የማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ መስፈርቱን አሟልተዋል የሚባሉትም ይመዘገባሉ ተብሎ ፕሮግራም ተይዞላቸዋል፡፡የገዳ ሥርዓትን በጉባዔው ላይ በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት አስመዘግባለሁ ብላ ተስፋ ያደረገችው ኢትዮጵያ ጉባዔውንም በዋና ፀሐፊነት ትመራዋለች፡፡

በ11ኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ጥበቃ የበይነ መንግሥታት ኮሚቴ ጉባዔ ላይ ከአንድ መቶ በላይ ሀገራት የመጡ ተሣታፊዎች ተገኝተውበታል፡፡ከኩባ የመጡ የጉባዔው ተሣታፊ በቅርቡ ህይወታቸው ላለፈው የቀድሞ የኩባ ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ የህሊና ፀሎት ይደረግ ብለው በመጠየቃቸው የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ብዛት ያላቸው የአዲስ አበባ እግረኞች በሃሣብ ጭልጥ እያሉ ዜብራንና የትራፊክ መብራትን እየረሱ ለትራፊክ አደጋ እየተጋለጡ ነው ተባለ

ብዛት ያላቸው የአዲስ አበባ እግረኞች በሃሣብ ጭልጥ እያሉ ዜብራንና የትራፊክ መብራትን እየረሱ ለትራፊክ አደጋ እየተጋለጡ ነው ተባለ…በአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙት ባለሙያው አቶ ብርሃኑ ኩማ ለሸገር ሲናገሩ ዘንድሮ በአንደኛው ሩብ ዓመት ብቻ 120 እግረኞች የመንገድ ትራፊክ ህግን በመተላለፍ በመኪና አደጋ ህይወታቸውን ሲያጡ፤ 511 ለከባድ፣ 326 ሰዎች ደግሞ ለቀላል ጉዳት ተዳርገዋል ብለዋል፡፡

በ6 ሺ 681 የመኪና አደጋዎች ከደረሰው የሞትና የአካል ጉዳት በተጨማሪ 5 ሺ 724 የንብረት ውድመት ተመዝግቧልም ብለዋል፡፡

ኤጀንሲው እግረኞችን በሃሣብ ተውጥው እየተጓዙ ከሚደርስባቸው መሰል አደጋ ለመታደግ ለአንድ ወር የሚቆይ የድምፅ ማጉያ ቅስቀሣ ለመጀመር፣ በራሪ መልዕክቶችንም ለማሰራጨት በዝግጅት ላይ ነው ተብሏል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኤለኒኖ ያስከተለውን ድርቅ የተቸገረችው ኢትዮጵያ አሁንም ድርቅ እና ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የመጣባት መሆኑ ተሠማ

ኤለኒኖ ያስከተለውን ድርቅ የተቸገረችው ኢትዮጵያ አሁንም ድርቅ እና ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የመጣባት መሆኑ ተሠማ፡፡ከእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ አለማየሁ ብርሃኑ እንደሰማነው ኤልኒኖን ተከትሎ የሚመጣው የአየር ንብረት ለውጥ ቆላማ የኢትዮጵያ አካባቢዎችን ለድርቅ ዳርጓቸዋል፡፡

የአደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን በተለይም በአርብቶ አደር አካባቢዎች ድርቅ የተከሰተ መሆኑንና እስካሁን ባለው መረጃ ከ2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጐች ለድርቅ መጋለጣቸው መናገሩ ይታወሳል፡፡አጠቃላይ ሪፖርቱ በተያዘው ወር ማብቂያ እንደሚጠቃለል የሚጠበቀው የድርቁ ሁኔታ ምናልባትም እስከ 5 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብን ሊያዳርስ እንደሚችልም ኮሚሽኑ መናገሩ ይታወቃል፡፡ የመኸሩ ወቅት የአየር ሁኔታ መልካም የነበረ መሆኑን የተናገሩት አቶ አለማየሁ በቆላማው አካባቢ ግን የዝናብ እጥረትና መቆራረጥን አስከትሏል ብለዋል፡፡

ከድርቁም ባሻገር ያልተጠበቀ ዝናብ የመጣ በመሆኑ የደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ሊሰበሰቡ እንደሚገባ አቶ አለማየሁ ይናገራሉ፡፡ ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል የተረጂዎች ቁጥርና የሚያስፈልገው እርዳታ ዓይነትና መጠንስ የሚለው እየተጠና ሲሆን በቅርቡ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኀዳር 19፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

 • ከአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች መካከል በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የወጣውን ደረጃ አሟልተው አራተኛ ደረጃ ምድብ ውስጥ የገቡ ትምህርት ቤቶች አለመኖራቸውን ሰማን፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ህዳር 22 የሚታሰበውን አለም አቀፍ የኤች አይቪ ቀን ምክንያት በማድረግ ነገና ከነገ በስቲያ ነፃ የህክምና የምርመራ አገልግሎት አሰጣለሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ጊዜ እና ዘመን የማያመጣው ነገር የለም አሁን ዘመኑ በተለያየ ምክንያት መውለድ ላልቻሉ ባለትዳሮች መልካሙን ዜና ይዞላቸው መጥቷል፤ ይሁን እንጂ መልካሙ ወሬ ኢትዮጵያ ሲደርስ ችግር የገጠመው ይመስላል…  (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በማሳ ላይ የሚገኝ እህልና አዝርዕት እንዳይጐዳ ገበሬው በአፋጣኝ የሰብል ስብሰባ እንዲያከናውን ተመከረ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በሃሳብ ጭልጥ ማለት እግረኞችን ለመኪና አደጋ እያጋለጠ ስለሆነ በድምፅ ማጉያ ቅስቀሳ ሊደረግ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የባዬ ቴክኖሎጂ ውጤት ምርጥ ዘሮች የሙከራ ምርት አጥጋቢ መሆኑ ተነገረ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • በአዲስ አበባ ከሚሰጠው የጤና አገልግሎት የግል ተቋሞች ከግማሽ በላይ ድርሻ አላቸው ተባለ፡፡ (ፍቅርተ መንገሻ)
 • ትናንት በፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የተከፈተው 11ኛ የዩኔስኮ ቅርሶች ጥበቃ ከዛሬ ጀምሮ ለ5 ቀን የሚቆየውን ጉባዔ ጀምሯል፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • በህገ-ወጥ መንገድ ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ያስተላለፈች ግለሰብ በእሥራት ተቀጣች፡፡ (ምህረት ስዩም)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መንግሥት በኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሣ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ውስጥ የነበረውን 75 በመቶ ድርሻ ጠቅልዬ ልሸጠው ነው አለ

የኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሣ ማምረቻ አክሲዮን ማህበር በመንግሥትና በአንድ የውጭ ድርጅት ባለቤትነት ተይዞ ቆይቷል፡፡ከአክሲዮን ማህበሩ ድርሻ 25 በመቶው የተያዘው ናም ፓክ በተባለና በአሜሪካ ስም በተመዘገበ ኩባንያ ነው፡፡ቀሪው 75 በመቶ ደግሞ የመንግሥት ድርሻ እንደሆነ ሰምተናል፡፡

መንግሥት አሁን ይህን ድርሻዬን ጠቅልዬ ልሸጠው ነው ብሏል፡፡ሽያጩን ለማከናወን ከሰሞኑ ጨረታ እንደሚያወጣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ነግረውናል፡፡ሌሎች ሁለት ድርጅቶችን በጋራ ለማልማትም ጨረታ እንደሚወጣ ከዳይሬክተሩ ከአቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ሰምተናል፡፡

በጋራ ለማልማት ጨረታ ይወጣባቸዋል የተባሉት አዳሚ ቱሉ ፀረ ተባይ ማዘጋጃ አክሲዮን ማህበር እና አዋሽ መልካሳ አልሙኒየም ሰልፌትና ሰልፈሪክ አሲድ አክሲዮን ማህበር ናቸው ብለዋል፡፡በባቱ ከተማ የሚገኘው አዳሚ ቱሉ ፀረ ተባይ ማዘጋጃ አክሲዮን ማህበር ዋና ምርቶቹ ፀረ ተባይና ፀረ አረም መድሃኒቶች ናቸው፡፡

አዋሽ መልካሳ አልሙኒየም ሰልፌትና ሰልፈሪክ አሲድ አክሲዮን ማህበር ደግሞ ለጨርቃ ጨርቅና ለቆዳ በግብዓትነት የሚያገለግሉ ኬሚካሎችን ያመርታል፡፡የውሃ ማጣሪያ ኬሚልም ሌላው ምርቱ ነው፡፡በአዋሽ መልካሳ አካባቢ የሚገኝ እንደሆነም አቶ ወንዳፍራሽ ነግረውናል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያን የአየር ክልል ጥሰው የገቡትና በጋምቤላ አየር ማረፊያ ለሦስት ቀናት የቆዩት 20ዎቹ አውሮፕላኖች መለቀቃቸው ተሠማ

የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው በጋምቤላ አየር ማረፊያ እንዲቆዩ ተደርገው የነበሩ 20 የሲቪል አውሮፕላኖች መለቀቃቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ተናገረ…አውሮፕላኖቹ ጐብኚዎችን ጭነው ነዳጅ ቀድተው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማምራት እቅድ እንደነበራቸው ሰምተናል፡፡

መነሻቸውን ከሱዳን ያደረጉት እነዚህ አውሮፕላኖች በመንግሥት በተደረገው ውሣኔ ከሦስት ቀናት ቆይታ በኋላ ካሉበት አየርማረፊያ ተነስተው እንዲበሩ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ አውሮፕላኖቹ የአውሮፓ አውሮፕላኖች መሆናቸው ታውቋል፡፡የአለም አቀፍ በረራ ህግን በመተላለፍ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ፈቃድ ሳያገኙ የአየር በረራ ክልሉን በመጣሳቸው ነበር በጋምቤላ አየር ማረፊያ ቆይተው ምርመራ እንዲደረግባቸው የተወሰነው፡፡

በአውሮፕላኖቹ የበረራ ሁኔታ ላይ የተደረገው ምርመራ ተጠናቆ ለሪፖርት አለመድረሱን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው ለሸገር ተናግረዋል፡፡የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ያከናወናቸውን ሥራዎች ሪፖርት እያቀረበ ሲሆን የአቪዬሽኑ ተገልጋይ የሆኑ ድርጅቶችም ጥያቄዎቻቸውን አቅርበው ከአቪዬሽኑ ጋር እየመከሩ ነው፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኀዳር 16፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

 • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአምስተኛ ጊዜ የዓመቱ ምርጡ አፍሪካዊ አየር መንገድ ተብሎ ተሸለመ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • ብሔራዊ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የሚተዳደርበት በጀት አነስተኛ ነው ተባለ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
 • የኢትዮጵያ ገበሬ ከሚያመርተው እና ከራሱ ተርፎ ለገበያ የሚያወጣው ምርት ከ22 በመቶ የዘለለ አይደለም ይህን ለመቀየር ገበሬውን የገበያ አምራች ለማድረግ ታስቧል ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • መንግሥት በኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሣ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ውስጥ የነበረውን 75 በመቶ ድርሻ ጠቅልዬ ልሸጠው ነው አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የኢትዮጵያን የአየር ክልል ጥሰው የገቡትና በጋምቤላ አየር ማረፊያ ለሦስት ቀናት የቆዩት 20ዎቹ አውሮፕላኖች መለቀቃቸው ተሠማ፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጡ ዝቅተኛው በዜሮ ነጥብ 25 ሲቀንስ ከፍተኛው ደግሞ በዜሮ ነጥብ 10 ይጨምራል ተባለ

በኢትዮጵያ በአየር ንብረት መለወጥ ምክንያት ላለፉት ስድስት አስርት አመታት መረጃዎች እንዳሳዩት በየአስር አመቱ ዝቅተኛው የሙቀት መጠን በዜሮ ነጥብ 25 ድግሪ ሴንቲግሬድ የሚጨምር ሲሆን፤ ከፍተኛው አማካይ የሙቀት መጠን ደግሞ በዜሮ ነጥብ 10 ድግሪ ሴንቲግሬድ ይጨምራል ተባለ፡፡

በአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር፣ በሬድ ፕላስ ሴክሬተሪያት ኢትዮጵያ፣ በፋና ብሮድካሲቲንግ ኮሮፖሬት አዳራሽ በተዘጋጀው የደን ምንጣሮ እና መመናመን ምክንያቶችና መፍትሄዎቹ ላይ በተደረገ ውይይት የዝናብ መጠን በአማካይ በሀገሪቱ ተመሣሣይ ሲሆን በሰሜንና ደቡብ ምዕራብ በሀገሪቱ ክፍሎች የቀነሰ ሲሆን በመካከለኛው ኢትዮጵያ ጨምሮ እንደተስተዋለ ተነግሯል፡፡ይህንን የዝናብ መቀነስ መጠን እየጨመረ ካለው የሙቀት መጠንና ከፍተኛ የትነት ሁኔታ ጋር ተባብሮ ችግሩን ሲያባብሱ ቆይተዋል ተብሏል፡፡

ለዚህ ዓይነቱ ችግር መከሰት ዋና ምክንያት ነው የተባለው ደግሞ የደን ምንጣሮ ነው፡፡ሰዎች በአምስት ዋና ዋና ምክንያቶች ደኖችን አንደሚመነጥሩ በሬድ ፕላስ ኢትዮጵያ አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር ይተብቱ ሞገስ በጥናት አመላክተዋል፡፡እንደ ዶክተሩ ጥናት የእርሻ መሬት መስፋፋት፣ የሰደድ እሣት፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች፣ ማዕድን የማውጣት ሥራዎችና የከተሞች መስፋፋትን በዋና ምክንያትነት ዘርዝረዋቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers