• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ጥቅምት 18፣ 2012/ ማንን ምን እንጠይቅልዎ- በለገሃር ፕሮጀክት እስካሁን ያልፈረሱ ግን መፍረሳቸው የማይቀር ቤቶች የዚህ ዓመት እጣ ፈንታ ምን ይሆን…

በለገሃር ፕሮጀክት እስካሁን ያልፈረሱ ግን መፍረሳቸው የማይቀር ቤቶች የዚህ ዓመት እጣ ፈንታ ምን ይሆን? ግርማ ፍሰሐ፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክትል ሥራ አስፈፃሚና የአቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሊዲያ ግርማን ጠይቋል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 18፣2012/ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሰላም ጥሪ አስተላለፈ

በሰሞኑ ሁከት በአሰቃቂ ሁኔታ የሰው ሕይወት ያጠፉና በተለያየ ወንጀል የተሳተፉትንም መንግስት ባስቸኳይ ለህግ እንዲያቀርብ ጠይቋል፡፡የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡በመግለጫው የሰላም ጥሪ ያስተላለፈ ሲሆን መንግስትንም ከዝምታ ወጥቶ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል፡፡ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የአገሪቱ የሰላም እጦት በተለይ በኦሮሚያ ክልል ከሰሞኑ በተከሰተው ሁከት ሃይማኖታዊ ገፅታ እንዲላበስ መደረጉ ችግሩን አሳሳቢ አድርጎታል ብሏል ጉባኤው፡፡

የችግሩ ምክንያት ምንም ይሁን ምን አለመረጋጋቱ በመመካከር መፈታት ሲችል ወደ አልተገባ የሀይል እርምጃ በመግባት የሰው ልጆች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውንም ጉባኤው አስታውሷል፡፡ድርጊቱ በሁሉም ሃይማኖቶች ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ሀሳብና ተግባሩንም አምርረን እናወግዛለን ብሏል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤው፡፡በድርጊቱ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችም ይሁኑ ቡድኖች እንዲሁም የሚያባብሱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጠይቋል፡፡

ወንጀሉን የፈፀሙትንም የሚመለከታቸው የፍትህ አካላት አስፈላጊውን ማጣራት አድርገው በአስቸኳይ ህግ ፊት ሊያቀርቧቸው ይገባል ብለዋል፡፡ሰፋ ካለው የጉባኤው የጋራ መግለጫ ባሻገር እያንዳንዱ የጉባኤው የበላይ ጠባቂ የሆኑ የሃይማኖት አባቶችም ለእምነት ልጆቻቸውና ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሰላም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ሃይማኖት የግጭት መንስኤ መሆን የለበትም፣ ሰላምን አስከብራለሁ ብሎ የቆመው የመንግስት አካልም እንዲህ ያለውን ድርጊት ለምን ዝም ብሎ ይመለከታል ሲሉ የበላይ ጠባቂዎቹ ጠይቀዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 18፣ 2012/ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ከነበረው ግጭት ጋር በተገናኘ እስከ አሁን ከሶስት መቶ በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ

ሠሞኑን በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው ግጭት ተሳትፈው በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸው ተነግሯል፡፡የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ደሬሳ ተረፈ ዛሬ ለሸገር እንዳሉት እስከ አሁን ከሶስት መቶ የሚልቁ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡በግጭቱ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ተጨማሪ ሰዎችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ ቀጣይ እንደሆነ አቶ ደሬሳ ተናግረዋል፡፡ለዚህ የፀጥታ ሃይሎች ከህዝቡ ጋር በቅርበት እየሰሩ ናቸው ብለዋል፡፡

ትናንት ጠዋት ሞጆ እና አለምገና አካባቢዎች ላይ ሰልፍ ለመውጣት ከተደረገ ሙከራ ውጪ ክልሉ ወደ ቀድሞ መረጋጋቱ መመለሱንም ምክትል የቢሮ ሃላፊው ለሸገር ተናግረዋል፡፡በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ህብረተሰቡ ከስጋት ለመውጣት ጊዜ ቢጠይቀው አይፈረድበትም የሚሉት አቶ ደሬሳ፣ የፀጥታ ሃይሎች በተለይ ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች ጥበቃ እያደረጉ ስለሚገኙ ችግር አይኖርም ብለዋል፡፡ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል ጥፋተኛ ሆነው የሚገኙትን ለይቶ ወደ ህግ የማቅረቡ ስራ በፍጥነት እንደሚከናወን አቶ ደሬሳ ጨምረው ነግረውናል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 18፣ 2012/ ከተማሪዎች አቀባበል ጀምሮ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚደረግ ክትትል ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስፈን ይረዳል

ምንም እንኳ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ የራቁና የተነጠሉ ባይሆኑም፣ ከተማሪዎች አቀባበል ጀምሮ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚደረግ ክትትል ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስፈን እንደሚያግዝ ምሁራን ተናገሩ፡፡
 • የተማሪዎች ጥያቄ በአንድ ጀምበር የሚመለስ ስለማይሆን ተማሪዎች መታገስ አለባቸውም ተብሏል፡፡

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 17፣ 2012/ በመጪዎቹ 5 አመታት ውስጥ 124 ሺ ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ ነው ተባለ

በመጪዎቹ 5 አመታት ውስጥ 124 ሺ ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ ነው ተባለ፡፡ እቅዱን ለማስፈፀምም የተማሩ ወጣቶችን በማደራጀት በመስኖ ስራ እንዲሳተፉ ይደረጋል ተብሏል፡፡
 • በዚህ አመት በጣና በለስ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ወደ ስራ ለሚገቡ 960 የዲግሪ ተመራቂ ስራ አጥ ወጣቶች ለ10 ቀናት የሚቆይ ሥልጠና በባህር ዳር መሰጠት ጀምሯል፡፡

ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 18፣ 2012/ ኢትዮጵያ እንደ ጫካ ቡና እና የጫካ ማር ያሉ ተፈጥሯው የግብርና ምርቶች ባለቤት ናት

ምንም አይነት ሰው ሰራሽ ግብዓት ያልታከለባቸው ተፈጥሯዊ የግብርና ምርቶች በዓለም ገበያ ላይ ከፍተኛ ተፈላጊነትና የተሻለ ዋጋ አላቸው፡፡ኢትዮጵያ ደግሞ እንደ ጫካ ቡና እና የጫካ ማር ያሉ ተፈጥሯው የግብርና ምርቶች ባለቤት ናት፡፡እነዚህን ምርቶች የምትሸጣቸው ግን ማዳበሪያ እና ኬሚካል ከተጨመረባቸው የግብርና ምርቶች እኩል ነው ይባላል፡፡ለምን ይሆን? የንጋቱ ረጋሣ መረጃ ይህንን ይመለከታል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 18፣ 2012/ የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ጣቢያ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ 60 ሺህ ሰዓት የሚገመት ተቀርጾ የተቀመጠ የምስልና የድምፅ ክምችት መያዙ ይነገራል

የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ጣቢያ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ 60 ሺህ ሰዓት የሚገመት ተቀርጾ የተቀመጠ የምስልና የድምፅ ክምችት መያዙ ይነገራል፡፡
 • ዜጎች ከምስል ክምችቶቹ ታሪክን እንዲማሩ፣ ያለፈውን ትውልድ አኗኗርም እንዲያጤኑ እድል ለመስጠት ቢያንስ 50 አመት ሆኗቸው ቅርስ የሆኑ ክምችቶቹን ህብረተሰቡ በቅርቡ እንዲጠቀምበት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
ታዲያ ጣቢያው ይህን ሀላፊነቱን እየተወጣ ነው ወይ? ትዕግስት ዘሪሁን የቴሌቪዥን ጣቢያውን ጠይቃለች፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 17፣ 2012/ ታዳጊዎች መሰረታዊ የህግ እውቀት እንዲኖራቸው በትምህርት ቤቶች የህግ አስተምህሮ ለመስጠት የሚያስችል ጥናት

ታዳጊዎች መሰረታዊ የህግ እውቀት እንዲኖራቸው በትምህርት ቤቶች የህግ አስተምህሮ ለመስጠት የሚያስችል ጥናት ተጠናቅቆ ቢገኝም ወደ ተግባር ለመግባት እክሎች አጋጥመዋል ተባለ፡፡

 • ተማሪዎች መሰረታዊ የሕግ እውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ ግዴታውን የሚያውቅ ዜጋ ለመፍጠር ያስችላል ተብሏል፡፡

ምህረት ስዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 14፣ 2012/ እስከ ዛሬ በዩኔስኮ ተመዝግበዋል የተባሉት ቅርሶቻችን ምን ጥቅም አስገኝተዋል?

የሚዳሰሱት ባህላዊ ቅርሶቻችን ደማቅ ተቀባይነት ባገኙበት በአሁኑ ወቅት፣ በዩኔስኮ የመመዝገብ አስፈላጊነትም አብሮ ይነሳል፡፡ቅርሶች በዩኔስኮ መመዝገባቸው ደረጃቸውን ምን ያህል ከፍ ያደርገዋል ? እስከ ዛሬ በዩኔስኮ ተመዝግበዋል የተባሉት ቅርሶቻችን ምን ጥቅም አስገኝተዋል? በዩኔስኮ ለመመዝገብ ምን ማድረግ ያስፈልጋል? በየነ ወልዴ ወደ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ጎራ ብሎ ነበር…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 17፣ 2012/ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት የጭነት መኪና ዕጥረት ስራዬን እያስተጓጎለው ነው ብሏል

የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት የጭነት መኪና ዕጥረት ስራዬን እያስተጓጎለው ነው ብሏል፡፡ የትራንስፖርት ባለስልጣን በበኩሉ የመኪና ዕጥረት የለም ይላል፡፡
 • የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት አሁን ወደብ ላይ 9 ሺ ኮንቴይነር ተቀምጧል ይላል፡፡


ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 17፣ 2012/ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ዋና ኮሚሽነር የሰሞኑን አስከፊ ሁከት አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ሰሞኑን በተከሰተው ሁከት ምክንያት ሕይወት መጥፋቱን፣ ንብረት መውደሙን እንዲሁም የደረሰውን ማህበረሰባዊ ቀውስ በተመለከተ ለሸገር መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ኮሚሽነሩ ባለፈው በኢትዮጵያ ሶማሌና በአፋር ክልል መካከል በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከሚመለከታቸው ጋር ለመምከር በአፋር ክልል ተገኝተው ነበር፡፡
 • የሰብዓዊ ቀውሱ የፖለቲካ ቀውሳችን ውጤት ነው፡፡
 • የፀጥታ ሐይሎች ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆኑን አውቃለሁ ያሉት ኮምሽነሩ ሁሉም የህብረተሰቡ ክፍል ለዚህ ትብብር ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡


ሕይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers