• Slider One

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ኀዳር 22፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ የአልኮል መጠጥን መሸጥ የተከለከለ ነው ቢባልም ታዳጊዎቹ ያለ ከልካይ መጠጥ እየገዙ ነው ተብሏል፡፡ (መሠረት በዙ)
 • ከውጭ የሚገቡ የእፅዋት ዝርያዎች በአገር በቀሎቹ ላይ የሚያደርሱትን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስና ለማስቀረት ኧረ መላ ምቱ እየተባለ ነው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የትራፊክ አደጋ የሚበዛበት 18 ማዞሪያ ጊዜያዊ መፍትሄ እየተበጀለት ነው ተባለ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
 • ትውልደ ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤላውያን በኢትዮጵያ የቀሩ ዘመዶቻቸው ወደ እሥራኤል እንዲመጡላቸው ለአገሪቱ ፓርላማ ጥያቄ ማቅረባቸው ተሠማ፡፡ (የኔነህ ከበደ)
 • XCMG የተባለ የቻይና ኩባንያ ከፍተኛ ውጤት ያላቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በውጪ ሀገር የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እረዳለሁ አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊታችን ጥር መጨረሻ አንስቶ ወደ ጊኒ ኮናክሪ በረራ ሊጀምር ነው፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የገዳ ስርዓት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት ተመዘገበ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የሴቶችና የሕፃናት መብት ለማስጠበቅ የየክልሎቹ ሕጐች ከሕገ መንግሥቱ ጋር መጣጣም እንዳለባቸው ተጠየቀ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ ማንኛውም ሰው በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሣኔ ከተላለፈበት በኋላ ከወንጀሉ ነፃ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከተገኘ ግለሰቡ የሚካስበት ህግ ሊወጣ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ ማንኛውም ሰው በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሣኔ ከተላለፈበት በኋላ ከወንጀሉ ነፃ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከተገኘ ግለሰቡ የሚካስበት ህግ ሊወጣ ነው ተባለ…ይህንን ያሉት የፌዴራል ምክትል ዐቃቤ ህግ የሆኑት አቶ ምትኩ ማዳ ናቸው፡፡

እስካሁን ይህን የመሰለ የህግ ማዕቀፍ በኢትዮጵያ የለም ያሉት አቶ ምትኩ በመጪው ጊዜ ተግባራዊ ይደረጋል በተባለው በሁለተኛው የሰብዓዊ መብት መርሃ-ግብር በስህተት የተፈረደባቸው ግለሰቦች ከወንጀሉ ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከተገኘ ለደረሰባቸ በደል የሚካሱበትና ስህተት የፈጠሩ የፍትህ አካላትም ተጠያቂ የሚሆኑበት የህግ ማዕቀፍ ፀድቆ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ አቶ ምትኩ ይህንን ያሉት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው ሰነዱን መነሻ አድርገው የምክር ቤቱ አባላት ላቀረቡላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ነው፡፡ከዚህ ቀደም የተለያየ የህግ ማዕቀፍ ያልተበጀላቸው፣ ለከባድ ወንጀሎች ምስክር ለሆኑና ለጠቋሚዎች የሚደረግ የህግ ከለላ ጠንካራ አይደለም ይህንን ችግር ለመፍታት ሰነዱ ምን ፋይዳ አለው በኢትዮጵያ ጥበቃ ከሚደረግላቸው የሰብዓዊ መብቶች መካከል በህይወት የመኖር መብት አንዱና ዋናው ነው፤ በህይወት ያለመኖር መብትስ ለምን ወንጀል ይሆናል እንደ መሠረታዊ የሰብዓዊ መብት ለምን አይታይም የሚሉ ጥያቄዎችም ከምክር ቤቱ አባላት ተነስተው ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ያላገኙ የፖለቲካ ፖርቲዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ከኮማንድ ፖስቱ ጋር እየመከሩ ነው

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ያላገኙ የፖለቲካ ፖርቲዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ከኮማንድ ፖስቱ ጋር እየመከሩ ነው…ዛሬ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በፌዴሽን ምክር ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ 30 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከኮማንድ ፖስቱ ጋር ሲመክሩ ይውላሉ፡፡

የመከላከያ ሚኒስቴርና የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬቴርያት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ የፖለቲካ ፖርቲዎቹን ሲያወያዩ አንደሚውሉ ሰምተናል፡፡የውይይት መድረኩ የተዘጋጀው በፖለቲካ ፓርቲዎቹ ተነሳሽነትና ጥያቄ ነው መባሉን ሰምተናል፡፡

ውይይቱ ለጋዜጠኞች ክፍት ባለመሆኑ ዝርዝሩን ልንነግራችሁ አልቻልንም፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኀዳር 21፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በማህበራዊ ግልጋሎት አሰልጥኖ በየወረዳ ለሥራ የመደባቸው ሠራተኞች ብንመደብም ሥራ እየሰራን አይደለም አሉ፡፡ ቢሮው ግን በየወረዳው የመደብኳቸው እስከ ሥራ ድርሻቸው ነው ይላል፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • ጥጥ አሰባሰቡ ላይ በሚፈጠር የጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት በሚመረቱት የፋብሪካ ውጤቶች ላይ የጥራት ማነስ እንደሚያስከትል ተነገረ፡፡ (ፍቅርተ መንገሻ)
 • ከፍርድ በኋላ ከወንጀል ነፃ መሆናቸው የሚረጋገጥ ፍርደኞች የሚካሱበት ሕግ ሥራ ላይ ሊውል ነው፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የኢትዮጵያ የባሕል ልብሶች በአሜሪካ ፈላጊ በዝቶላቸዋል ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ለማክበር ሽር ጉድ ላይ የምትገኘው ሐረር ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ ነው ብላለች፡፡ (ምሥክር አወል)
 • በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ቤተ-ሙከራዎች አቅም ያንሣቸዋል ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ያላገኙ የፖለቲካ ፖርቲዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ከኮማንድ ፖስቱ ጋር እየመከሩ ነው፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ኀዳር 20፣2009

በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ህጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን ለማስጀመርም ከሳዑዲ አረቢያና ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ሃገሮች ጋር የሁለትዮሽ ስምምነቱ እስካሁን አልተደረገም ተባለ

ህጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን ለማስጀመርም ከሳዑዲ አረቢያና ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ሃገሮች ጋር የሁለትዮሽ ስምምነቱ እስካሁን አልተደረገም ተባለ…ስምምነቱ እስካልተፈረመ ድረስ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ መጀመሪያ ጊዜ ቁጥር ያለው የጊዜ ሰሌዳ የለም መባሉን ሰምተናል፡፡ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳዑዲ አረቢያና ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ሀገሮች የይሁን ፊርማ እየጠበቅኩ ነው ብሏል፡፡

ከዛሬ ነገ በቅርቡ ይጀመራል ሲባል የነበረው የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪቱ እስካሁን ለምን ዘገየ ተብለው የተጠየቁት በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሚንስትር ድኤታ አቶ ዳመነ ዳሮታ ከአገረብ ሀገሮቹ ጋር በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የድርድር ሰነድ ተላልከን መልስ እየጠበቅን ነው ብለዋል፡፡ሥራውንም ለማስጀመር የሀገራቱ ውሣኔ እና ፈቃድ ነው እንጂ የሚፈቀደው እኛ ስለፈለግን ብቻ የሚሆን አይደለም ሲሉ ሚኒስትር ድኤታው ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በእፅዋት ዝርያ ምዝገባ የዘር ጥራትና ቁጥጥር አሰራር ሥርዓቱ የኢትዮጵያን ግብርና አደጋ ላይ የጣለ ነው ተባለ

በእፅዋት ዝርያ ምዝገባ የዘር ጥራትና ቁጥጥር አሰራር ሥርዓቱ የኢትዮጵያን ግብርና አደጋ ላይ የጣለ ነው ተባለ፡፡እንዲህ የተባለው ዛሬ በይፋ ሥራውን በጀመረው የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ምክር ቤት ጉባዔ ላይ ነው፡፡የምክር ቤቱ ሰብሣቢ ዶክተር ካሱ ኢላላ እንዳሉት የዝርያ ምዝገባና ቁጥጥር ሥርዓቱ ግልፅ ሆኖ አለመቀመጡ እና ባለቤት ያጣ በሚመስል መልኩ መገኘቱ በግብርና ሥርዓቱ ላይ አደጋ እንዲያንዣብብ አድርጓል፡፡የምርምር ሥርዓቱ ወደ አዲስ የምርምር ሥርዓት እንዳይገባም እንቅፋት ሆኗል ያሉት ዶክተር ካሱ ምርምሩ ከውጭ በሚገቡ የግብርና ተባዬች እና በሽታዎች ላይ እንዲጠመድ አድርጐታል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኀዳር 20፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

 • ከአረብ አገሮች ጋር የሁለትዮሽ ስምምነቱ ጉዳይ ዳር እስከሚደርስ ድረስ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የውጭ የሥራ ሥምሪት እንደማይኖር የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዕወቁት አለ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
 • የቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአይን ህክምናን መስጠት ልጀምር ነው አለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • ኢትዮጵያ ከሁለት መቶ በላይ የአሳ ዝርያዎች ቢኖሯትም በተለያዩ ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተመናመኑ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ለአለም የማይዳሰስ ቅርስነት ክብር ይገባቸዋል ተብለው ከየአገሪቱ ተመርጠው 37 የማይዳሰሱ ቅርሶች ለአዲስ አበባው 11ኛ የዩኔስኮ ጉባዔ ቀርበዋል፡፡ (ምስክር አወል)
 • በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐር ቪዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን የውሃ ኤነርጂ ዲዛይንና ቁጥጥር ዘርፍ ባለፉት ሦስት ወሮች ካከናወንኳቸውና እየሰራሁም ካለሁት ሥራ 120 ሚሊዮን ብር አገኘሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • 2ኛው ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ-ግብር ረቂቅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴዎች እየተመከረበት ነው፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የዝርያ ምዝገባና ቁጥጥር ሥርዓቱ ወጥነት የጐደለው መሆኑ በኢትዮጵያ ግብርና ላይ ስጋት መጋረጡ ተነገረ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በማንኛውም ሁኔታ ለውጭ ኩባንያ አይተላለፍም ተባለ፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • ባለቤቱን የገደለው በእሥራት ተቀጣ፡፡ (ምህረት ስዩም)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አስራ አንደኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ጥበቃ የበይነ መንግሥታት ኮሚቴ ጉባዔ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፈተ

አስራ አንደኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ጥበቃ የበይነ መንግሥታት ኮሚቴ ጉባዔ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፈተ፡፡በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ የተከፈተው ጉባዔ ዛሬን ጨምሮ ለአምስት ቀናት እንደሚቆይ ሰምተናል፡፡በአምስቱ ቀናት ጉባዔም በአለም የማይዳሰስ ቅርስነት ተመዝግበው ነገር ግን አፋጣኝ ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል ተብለው በተለዩ ቅርሶች ላይ የተሰሩ ሥራዎች ሪፖርት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት ለመመዝገብ የቀረቡ ቅርሶች ላይ ግምገማ እንደሚካሄድም ሰምተናል፡፡ለመመዝገብ ከቀረቡት 37 የማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ መስፈርቱን አሟልተዋል የሚባሉትም ይመዘገባሉ ተብሎ ፕሮግራም ተይዞላቸዋል፡፡የገዳ ሥርዓትን በጉባዔው ላይ በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት አስመዘግባለሁ ብላ ተስፋ ያደረገችው ኢትዮጵያ ጉባዔውንም በዋና ፀሐፊነት ትመራዋለች፡፡

በ11ኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ጥበቃ የበይነ መንግሥታት ኮሚቴ ጉባዔ ላይ ከአንድ መቶ በላይ ሀገራት የመጡ ተሣታፊዎች ተገኝተውበታል፡፡ከኩባ የመጡ የጉባዔው ተሣታፊ በቅርቡ ህይወታቸው ላለፈው የቀድሞ የኩባ ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ የህሊና ፀሎት ይደረግ ብለው በመጠየቃቸው የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ብዛት ያላቸው የአዲስ አበባ እግረኞች በሃሣብ ጭልጥ እያሉ ዜብራንና የትራፊክ መብራትን እየረሱ ለትራፊክ አደጋ እየተጋለጡ ነው ተባለ

ብዛት ያላቸው የአዲስ አበባ እግረኞች በሃሣብ ጭልጥ እያሉ ዜብራንና የትራፊክ መብራትን እየረሱ ለትራፊክ አደጋ እየተጋለጡ ነው ተባለ…በአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙት ባለሙያው አቶ ብርሃኑ ኩማ ለሸገር ሲናገሩ ዘንድሮ በአንደኛው ሩብ ዓመት ብቻ 120 እግረኞች የመንገድ ትራፊክ ህግን በመተላለፍ በመኪና አደጋ ህይወታቸውን ሲያጡ፤ 511 ለከባድ፣ 326 ሰዎች ደግሞ ለቀላል ጉዳት ተዳርገዋል ብለዋል፡፡

በ6 ሺ 681 የመኪና አደጋዎች ከደረሰው የሞትና የአካል ጉዳት በተጨማሪ 5 ሺ 724 የንብረት ውድመት ተመዝግቧልም ብለዋል፡፡

ኤጀንሲው እግረኞችን በሃሣብ ተውጥው እየተጓዙ ከሚደርስባቸው መሰል አደጋ ለመታደግ ለአንድ ወር የሚቆይ የድምፅ ማጉያ ቅስቀሣ ለመጀመር፣ በራሪ መልዕክቶችንም ለማሰራጨት በዝግጅት ላይ ነው ተብሏል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኤለኒኖ ያስከተለውን ድርቅ የተቸገረችው ኢትዮጵያ አሁንም ድርቅ እና ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የመጣባት መሆኑ ተሠማ

ኤለኒኖ ያስከተለውን ድርቅ የተቸገረችው ኢትዮጵያ አሁንም ድርቅ እና ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የመጣባት መሆኑ ተሠማ፡፡ከእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ አለማየሁ ብርሃኑ እንደሰማነው ኤልኒኖን ተከትሎ የሚመጣው የአየር ንብረት ለውጥ ቆላማ የኢትዮጵያ አካባቢዎችን ለድርቅ ዳርጓቸዋል፡፡

የአደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን በተለይም በአርብቶ አደር አካባቢዎች ድርቅ የተከሰተ መሆኑንና እስካሁን ባለው መረጃ ከ2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጐች ለድርቅ መጋለጣቸው መናገሩ ይታወሳል፡፡አጠቃላይ ሪፖርቱ በተያዘው ወር ማብቂያ እንደሚጠቃለል የሚጠበቀው የድርቁ ሁኔታ ምናልባትም እስከ 5 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብን ሊያዳርስ እንደሚችልም ኮሚሽኑ መናገሩ ይታወቃል፡፡ የመኸሩ ወቅት የአየር ሁኔታ መልካም የነበረ መሆኑን የተናገሩት አቶ አለማየሁ በቆላማው አካባቢ ግን የዝናብ እጥረትና መቆራረጥን አስከትሏል ብለዋል፡፡

ከድርቁም ባሻገር ያልተጠበቀ ዝናብ የመጣ በመሆኑ የደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ሊሰበሰቡ እንደሚገባ አቶ አለማየሁ ይናገራሉ፡፡ ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል የተረጂዎች ቁጥርና የሚያስፈልገው እርዳታ ዓይነትና መጠንስ የሚለው እየተጠና ሲሆን በቅርቡ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers