• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ነሐሴ 27፣ 2011/ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በቅርቡ የፀደቀው የፓርቲዎች የምዝገባና አሰራር አዋጅ ተቃውሞ ገጥሞታል! ለምን?

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በቅርቡ የፀደቀው የፓርቲዎች የምዝገባና አሰራር አዋጅ ተቃውሞ ገጥሞታል! ለምን?


የኔነህ ሲሳይ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 27፣ 2011/ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንጀራና ሌሎች ለምግብነት የሚውሉ የኢትዮጵያ የባልትና ውጤቶች ከባዕድ ነገሮች ጋር እየተቀላቀሉ መሸጣቸው ይነገራል

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንጀራና ሌሎች ለምግብነት የሚውሉ የኢትዮጵያ የባልትና ውጤቶች ከባዕድ ነገሮች ጋር እየተቀላቀሉ መሸጣቸው ይነገራል፡፡ታዲያ ይህ ጉዳይ ሁሉንም ምርቶች በጅምላ በመጨፍለቁ እንጀራን ለውጪ ገበያ የማቅረብ ስራችንን ጎድቶብናል ገበያም አሳጥቶናል ሲሉ አምራቾች ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 25፣2011/ በሐምሌ አስራ አንዱ ጥቃት ንብረት ለወደመባቸው ግለሰቦች ካሳ እንደሚሰጥ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ተናገረ

በወቅቱ በነበረው ችግር በከተማዋ የ3 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የሀዋሳ ከተማ ኮማንድ ፖስት ሀላፊ ኮሎኔል ተክለብርሃን ገ/መድህን ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ሁለት ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል፤ በአንድ ህንፃ ላይም ጉዳት ደርሶ ነበር ተብሏል፡፡ንብረት ለወደመባቸው የከተማ አስተዳደሩ ካሳ ይከፍላል የተባለ ሲሆን የጠፉ ንብረቶችንም የማስመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ሰላም የማረጋገጥ ስራ እየተከወነ መሆኑን የተናገሩት የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ገለታ ገረመው የከተማዋ ሰላም ወደነበረበት ተመልሷል ብለዋል፡፡

የኮማንድ ፖስቱ ሀላፊ ኮሎኔል ተክለብርሃንም ይህንኑ ይጋራሉ፡፡የመከላከያ ሰራዊት አባላትም በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ ከመንቀሳቀስ ውጪ የሚሰራው ስራ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ከክፍለ ከተሞች እስከ ቀበሌ በተዋቀረው ኮማንድ ፖስት አማካኝነትም ስለ ሰላም ውይይት ተደርጓል ብለዋል፡፡በመሆኑም ህብረተሰቡ በራሱ ሰላሙን ማስጠበቅ ይችላል ሲሉም ተናግረዋል፡፡እስከ አሁን በተሰራው ሰላም የማስከበር ስራ 68 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ ነው ተብሏል፡፡ከተማዋ ሰላሟን መልሳ ካገኘች የኮማንድ ፖስቱ መቆየት ለምን አስፈለገ የሚል ጥያቄም ለሀላፊው ቀርቦላቸዋል፡፡እሳቸውም የኮማንድ ፖስቱን ቆይታ የሚወስነው የክልሉ መንግስት ነው ብለዋል፡፡ኮሎኔል ተክለብርሃን ገብረ መድህን በአሁኑ ሰኣት በከተማዋ የሚያሳስብ የሰላም ችግር እንደሌለም ተናግረዋል፡፡

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 25፣2011/ “አለ በጅምላ” እንደታሰበው ሊሰራ ያልቻለበት ምክንያት ምን ይሆን?

እንዲህ እንዳሁኑ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ ጣራ ነክቶ ሸማቾቹ እንዳይማረሩ ይረዳል ተብሎ የታመነበት “አለ በጅምላ” የተሰኘ ድርጅት ከስድስት አመታት በፊት ተቋቁሞ ነበር፡፡ “አለ በጅምላ” ለውድድር የተመቸ አይደለም የሚባለውን የንግድ ሥርዓት በብዙ ይቀይረዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበትም ነበር፡፡ ግን፣ እንደዚያው ሊቀጥል ወይም እንደታሰበው ሆኖ ለመገኘት አልቻለም፡፡ “አለ በጅምላ” እንደታሰበው ሊሆን ባለመቻሉ፣ ሸማቾች በዋጋ ንረት አርጩሜ እንዲሸነቆጡ የራሱን ድርሻ አካፍሏል፡፡ ለመሆኑ “አለ ጅምላ” እንደታሰበው ሊሰራ ያልቻለው በምን ምክንያት ነው፡፡ ለወደፊቱስ? ንጋቱ ረጋሣ ጠይቋል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 25፣ 2011/ ባለሞያዎች የምጣኔ ሐብቱን ለማሻሻል ምን ይመክራሉ ?

ለመሆኑ ይህን ሕዝብን ያስደነገጠ የኑሮ ውድነት ምን አመጣው ? ውድነቱ ከውጭ በሚገቡ እቃዎች ላይ ብቻ አልሆነም፡፡ እዚሁ ደጃችን የሚመረቱት ምርቶችም ቢሆን የዋጋቸው ክብደት ገዝፏል፡፡የህዝብ ቁጥሩን የሚመጥን ምርት አለመኖር፣ ያለአግባብ የታተመ ብርና በብድር የሚመጣው ገንዘብ ወደ ገበያው መረጨቱ፣ በመንግስት እጅ የተያዘው መሬት ዋጋ ተንጠራርቶ የማይደረስበት መሆኑ የኑሮ ውድነቱን እንዳባባሱት የምጣኔ ሐብት ባለሞያዎች ሲነግሩን ሰንብተዋል፡፡ ታዲያ መፍትሄው ምንድን ነው ? ባለሞያዎች የምጣኔ ሐብቱን ለማሻሻል ምን ይመክራሉ? ትዕግስት ዘሪሁን ያዘጋጀችው ዘገባ ይህንን ይመለከታል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 25፣ 2011/ “እሳት” እየሆነ የመጣው የኑሮ ውድነት ጉዳይ

ሰሞነኛው የእሮሮ ወሬ የኑሮ ውድነት “እሳት” መሆን ነው፡፡ በየቦታው፣ ይኸኛው ተወደደ፣ የዚያኛው ዋጋ አሻቀበ የሚሉ የሸማቾችን የብስጭት ስሞታ መስማት የእለት ተዕለት ልምድ ሆኗል፡፡ ሁሉም ዋጋው ሰማይ ጫፍ ደርሶ “እንደውስጥ እግር እሳት” እያደር የሚያንገበግብ ሆኗል፡፡ የአሁኑ መወደድ ብቻ ሳይሆን፣ የዋጋ ተስፈንጣሪውን ጭማሪም ወደፊት መቆጣጠር የሚቻልበት ተስፋም አልታይ ብሏል፡፡ማህሌት ታደለ በየቦታው ተዘዋውራ ያናገረቻቸው ጥቂት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ ስለፍጆታ እቃዎች ስለ ምግብ ምርቶች መወደድ የከረረ አስተያየታቸውን ሰጥተዋታል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 24፣2011/ በአዲስ አበባ ለትራንስፖርት ተጠቃሚዎች የተገነቡ ተርሚናሎች ጉዳት ሳይገጥማቸው አገልግሎት እንዲሰጡ ሁሉም ሊጠነቀቅላቸው ይገባል ተባለ

በአዲስ አበባ ለትራንስፖርት ተጠቃሚዎች የተገነቡ ተርሚናሎች ጉዳት ሳይገጥማቸው አገልግሎት እንዲሰጡ ሁሉም ሊጠነቀቅላቸው ይገባል ተባለ፡፡


ምህረት ስዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 24፣ 2011/ የተለያዩ ጥፋቶችን ፈፅመዋል የተባሉ 167 አቅራቢዎች በማንኛውም የመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፉ መታገዳቸው ተነገረ

የተለያዩ ጥፋቶችን ፈፅመዋል የተባሉ 167 አቅራቢዎች በማንኛውም የመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፉ መታገዳቸው ተነገረ፡፡ንጋቱ ረጋሣ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 24፣ 2011/ ኢትዮ ቴሌኮም የቀጣይ 3 አመት ስትራቴጂውን ይፋ አድርጓል

ኢትዮ ቴሌኮም የቀጣይ 3 አመት ስትራቴጂውን ይፋ አድርጓል፡፡ በቀጣዩ አመትም 50 ነጥብ 4 ሚሊዮን ደንበኞችን ለማፍራትና ገቢዬንም 45 ነጥብ 4 ቢሊዮን ለማድረስ አቅጃለሁ ብሏል፡፡ በስፍራው ተገኝቶ የዋና ስራ አስፈፃሚዋን መግለጫ የተከታተለው ተህቦ ንጉሴ የላከልንን የኔነህ ሲሳይ ይነግራችኋል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 24፣ 2011/ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ለአየር በረራ ደህንነት ያግዛል የተባሉ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመተግበር ላይ መሆኑን ተናገረ

ባለስልጣኑ ደህንነቱ የተጠበቀ በረራ ለማስተናገድ ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በዘመናዊ የናቪጌሸን መሳሪያዎች አገልግሎት እየሰጠሁ ነው ብሏል፡፡በዚህ መሰረት በቅርቡ በድሬዳዋ የተተከለው የርቀት መቆጣጠሪያ ዘመናዊ መሳሪያ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አንሙት ለማ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ከአዲሶቹ መሳሪያዎች አንደኛው አንድ አውሮፕላን ያለበትን ትክክለኛ አቅጣጫን በዲግሪ፣ ርቀትን በኪሎ ሜትር እንዲሁም የበረራ መዳረሻ ማረፊያዎችን በሰዓት የሚያሳውቅ መሳሪያ እንደሆነና የአገልግሎት ሽፋኑም 370 ኪሎ ሜትር እንደሚያካልል ሰምተናል፡፡

ሌላኛው መሳሪያም ጠቀሜታው የጎላ ዘመናዊ የናቪጌሸን መሳሪያ ሲሆን፣ በሁሉም አቅጣጫ ለሚበሩ አውሮፕላኖች አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል፡፡ይኽ መሳሪያ የአየር ማረፊያዎችና የናቪጌሽን መሳሪያዎች በሌሉበት ቦታ ተክቶ አውሮፕላን የሚበርበትን መስመር ትክክለኛነት አመላካች መሳሪያ ሲሆን የአገልግሎት ሽፋኑም ከ148 እስከ 278 ኪሎ ሜትር እንደሚደርስ ሰምተናል፡፡ባለስልጣኑ ለወደፊቱ በኮምቦልቻ፣ አሶሳ፣ ጎዴ፣ ባህርዳርና ጎንደር ተመሳሳይ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ለመትከል ተሰናድቷል ሲሉ አቶ አንሙት ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 24፣2011/ በኢትዮጵያ የግንባታ ዲዛይን ሥራ አስፈላጊው ትኩረት አልተሰጠውም ተባለ

በዘርፉ ያሉ የጥራት መጓደል ችግሮች መነሻም የዲዛይን ጉዳይ በቂ ትኩረት ካለማግኘቱ ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል፡፡ይህ የተነገረው የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር 21ኛ አመታዊ ጉባኤውን ሲያካሂድ ነው፡፡የማህበሩ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መስከረም ታምሩ ለዲዛይን ስራዎች የሚሰጠው ጊዜ ማነስ እንዲሁም ደረጃውን የሚመጥን ባለሙያ አለመመደብ ለስራው የሚሰጠው ትኩረት በቂ እንዳልሆነ ማሳያዎች ናቸው ብለዋል፡፡የባለሙያዎች የምዝገባ መስፈርት የሙያተኞችን ብቃት ለማረጋገጥ አለማስቻሉና ዲዛይኖች ሳያልቁ የግንባታ ስራዎችን መጀመር በዘርፉ የሚስተዋሉ ተጨማሪ ችግሮች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

በተጠቀሱት ችግሮች የተነሳም የግንባታ ስራዎች መጓተት፣ የዋጋ መናርና የጥራት ችግሮች በስፋት እየተስተዋሉ መሆኑን ወ/ሮ መስከረም ተናግረዋል፡፡በተጨማሪም በአንዳንድ አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጠው የአርክቴክቸር ትምህርት የሥርዓተ ትምህርት ክፍተትና የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ያለበት መሆኑን ማህበሩ ባደረገው የዳሰሳ ጉብኝት ተመልክቷል ተብሏል፡፡ይህንንም ለማስተካከል ለሚመለከታቸው አካላት የማሻሻያ ሀሳቦች መቅረባቸውን ፕሬዝዳንቷ ሲናገሩ ሰምተናል፡፡የዲዛይን ስራዎችን ጥራት ለመቆጣጠርም አለም አቀፍ ደረጃዎችን ከአገር ውስጥ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በማገናዘብ መስራት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር እያካሄደው ባለው አመታዊ ጉባኤ በ2011 ላከናወናቸው ተግባራትና በመጪው አመት ሊሰሩ በታቀዱት ተግባራት ላይ አባላቱ እየተመካከሩ ነው፡፡

ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers