• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

መጋቢት 28፣ 2012/ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት እያገዙ ነው ተባለ

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት በተለየ መንገድ እያገዙ ነው ተባለ፡፡
ንጋቱ ረጋሣ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 28፣ 2012/ የጤና ሚኒስቴር በበጎ ፈቃደኝነት የኮሮና ቫይረስ ህመምተኞችን ለማገዝ ለተመዘገቡ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና ልሰጥ ነው ብሏል

የጤና ሚኒስቴር በበጎ ፈቃደኝነት የኮሮና ቫይረስ ህመምተኞችን ለማገዝ ለተመዘገቡ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና ልሰጥ ነው ብሏል፡፡ በሌላ በኩል ቻይናዊው ባለሀብት ጃክ ማ ለአፍሪካ የለገሱት ቀሪ የህክምናና የመከላከያ ቁሳቁስ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡
በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 28፣ 2012/ የሰንዳፋ ከተማ ነዋሪዎች በተለይ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ የውሃ ችግር አሳሳቢ ሆኖብናል ብለዋል

በሰንዳፋ ከተማ የውሃ ችግር ከተከሰተ 2 ዓመት ሆኖታል፡፡ አሁን ደግሞ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ችግሩ እጅግ አሳስቦናል ሲሉ የከተማው ነዋሪዎች ለሸገር ተናግረዋል፡፡ የከተማው ውሃ አቅርቦት ሂደት በበኩሉ ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት ባደርግም ከእኔ አቅም በላይ ነው ብሏል፡፡
የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 28፣ 2012/ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከ12,000 በላይ የሚሆኑ የክልሉ ታራሚዎች በይቅርታ እንደተፈቱ ተናገረ

ነፍሰ ጡርና ህፃናት ይዘው የታሰሩ እናቶች፣ ልዩ ልዩ ህመም ያለባቸው እድሜያቸው የገፋ ታራሚዎች በይቅርታ ከተፈቱት መካከል ይገኙበታል ተብሏል፡፡የደቡብ ክልል ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት በመልካም ስነ ምግባራቸው የተመረጡ 3 519 ወንድና 119 ሴት እንዲሁም የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመቀነስ በልዩ ሁኔታ ከ8 000 በላይ ታራሚዎች እንዲፈቱ ተደርጓል ተብሏል፡፡በይቅርታ እንዲፈቱ የተወሰነው ከ12 000 በላይ መሆናቸውን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 28፣ 2012/ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 44 ደረሰ

ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 164 ሰዎች ውስጥ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት፤ በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል 26ቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ናቸው።

ቀሪዎቹ ደግሞ ለቫይረሱ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦች ናቸው ተብለው የተመረመሩ መሆናቸውን ነው የገለጹት።ዛሬ በቫይረሱ የተያዙት ግለሰብ የ65 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ የዱከም ከተማ ነዋሪና የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።ግለሰቧ ተጓዳኝ ለሆነ በሽታ ወደ ህክምና ተቋም ከሄዱ በኋላ የቫይረሱን ምልክት በማሳየታቸው ነው ምርመራ የተደረገላቸው።በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 44 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንድ ግለሰብ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ይገኛሉ።
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 25፣ 2012/ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የኮሮና ወረርሽኝ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት የነሐሴውን ምርጫ ለማካሄድ ይረዳ ዘንድ አስቀድሜ ያወጣሁትን የጊዜ ሰሌዳ ስራ ላይ ለማዋል ተቸግሬያለሁ ሲል ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አቤት ብሏል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሁለት ፓርቲዎች ምርጫን ማራዘምም ሆነ መሰረዝን ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤትም ሆነ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠ ህገ መንግስታዊ ስልጣን አይደለም ይላሉ፡፡ የኔነህ ሲሳይ በዚህ ዙሪያ ይህን አዘጋጅቷል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 25፣ 2012/ የማህበረሰብ የጋራ የበሽታ መከላከል አቅም ‘ኸርድ ኢምዩኒቲ’ እና የኮሮና ነገር…

ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት በወረርሽኝ ደረጃ የተከሰቱ በሽታዎች ነበሩ፡፡ከእነዚህ በሽታዎች የተገኘው ተሞክሮ የሚያሳየው አንዳንዶች ቀለል ያለ ምልክት ያሳያሉ አንዳንዶች ደግሞ ምንም ምልክት ሳያሳዩ ቫይረሱ ቆይታውን ጨርሶ ሊጠፋ ይችላል፡፡በእንዲህ ዓይነቱ ጊዜ በሽታ የመከላከል አቅማቸው ጠንካራ የሆኑ ማህበረሰቦች ሊኖሩ ይችላሉ ይህም በእንግሊዝኛው ኸርድ ኢምዩኒቲ ይባላል፡፡በዚህ ረገድ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ እየታየ ያለው ነገር እንዴት ነው? ሲል ንጋቱ ረጋሣ ባለሙያ ጠይቋል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 28፣2012/ ታክሲዎች የመጫን አቅማቸውን በግማሽ እንዲቀንሱ ተወሰነ

በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች የሰው መቀራረብን ለመቀነስ ከመጫን አቅማቸው ግማሽ ብቻ እንዲጭኑ እና ተሳፋሪዎችም እጥፍ እንዲከፍሉ የከተማ አስተዳደሩ ወስኗል፡፡የአንበሳ አውቶብስ እና ሸገር አውቶብስ ደግሞ ያለ ምንም የዋጋ ጭማሪ 30 ሰው ብቻ እንዲጭኑ መወሰኑን ከከንቲባ ፅ/ቤት ሰምተናል፡፡

ውሳኔው ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል፡፡

ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 28፣ 2012/ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በተመለከተ ዓለም አቀፍ ህጎች ምን ይላሉ? ኢትዮጵያስ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ምን ማድረግ ይኖርባታል?

ኢ-ፍትሃዊ ሃሳቧ የበላይ እንዲሆን በአባይ ወንዝ ላይ የተያዘውን ድርድር ከጫፍ እንዳይደርስ የምትታትረው የግብፅ እንቅስቃሴ፤ ከአደራዳሪነት ወጥታ እስከ ስምምነት አርቃቂ የደረሰችው እና መወገኗን በግልፅ ያሳየችው አሜሪካ የያዘችው አቋም ኢትዮጵያን የሚያሳጣት ነገር ይኖር ይሆን? ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በተመለከተ ዓለም አቀፍ ህጎችስ ምን ይላሉ? ኢትዮጵያስ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ምን ማድረግ ይኖርባታል ስትል ትዕግስት ዘሪሁን የህግ ባለሙያዎችን አነጋግራለች፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 28፣ 2012/ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ለሚያመርቱ ፋብሪካዎች ድጋፍ እየተደረገ ስለሆነ የአቅርቦት ችግር አይኖርም ተባለ

የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ለሚያመርቱ ፋብሪካዎች ድጋፍ እየተደረገ ስለሆነ የአቅርቦት ችግር አይኖርም ተባለ፡፡
ንጋቱ ረጋሣ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መጋቢት 28፣ 2012/ የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽንም ለዚህ ችግር መወጫ እህል እና ሌሎችንም ቁሳቁሶችን በጎተራዎቼ አስቀምጫለሁኝ አትስጉ ብሏል

በየትውልዱ ፈታኝ ሁኔታዎች ገጥመው አልፈዋል፡፡ይኸኛውም ትውልድ ራሳችሁን ጠብቁ፣ ከቤት አትውጡ፣ ርቀታችሁን ጠብቁ፣ ያለው ለሌለው እያካፈለ ይህን አጥፍቶ ጠፊ ጊዜን በትብብር እንለፈው ነው የተባለው፡፡የወትሮው የረጅም ጊዜ ስንቅ አዘገጃጀታችንን መተግበሩም ለዚህ ጊዜ ይጠቅመናል፡፡

የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽንም ለዚህ ችግር መወጫ እህል እና ሌሎችንም ቁሳቁሶችን በጎተራዎቼ አስቀምጫለሁኝ አትስጉ ብሏል ትለናለች ህይወት ፍሬስብሃት

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers