• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

መስከረም 9፣ 2012/ “ኢትዮጵያዊነት ምንድነው” በሚል ርዕስ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ምክክር ተካሄደ

“ኢትዮጵያዊነት ምንድነው” በሚል ርዕስ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ምክክር ተካሄደ፡፡ወንድሙ ሀይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 9፣ 2012/ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ 116 ሚሊየን ብር ስራ ላይ ለማዋል እየሰራ መሆኑን ተናገረ

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ 116 ሚሊየን ብር ስራ ላይ ለማዋል እየሰራ መሆኑን ተናገረ፡፡ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 9፣ 2012/ በየጎዳናው እና በመጠለያዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ የተባሉ ታዳጊዎች

በየጎዳናው እና በመጠለያዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ የተባሉ ታዳጊዎችን ለመርዳት ከመንግስት እና ረጂ ተቋማት በተጨማሪ ግሰለቦችም ሊያግዙ ይገባል ተባለ፡፡ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 9፣2012/ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃ መሸጥ አይቻልም አለ

ባለስልጣኑ ከቅርብ ጊዜያው ወዲህ ቦቴ መኪናዎችን በመጠቀም የሚከናወኑ የውሃ ሽያጮች ራስ ምታት እንደሆኑበት ተናግሯል፡፡የውሃ ሽያጩ ምሽትን ተገን አድርጎ የሚከናወን በመሆኑ ለቁጥጥርም አዳጋች ሆኖብኛል ብሏል፡፡የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሞገስ አርጋው ድርጊቱ ከተማዋ ለውሃ ብክነት ከሚያጋልጡ ነገሮች አንዱ ነው ብለዋል፡፡ድርጊቱንም ለመቆጣጠር አዲስ ስልት አውጥተው እየሰሩ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡም ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበራቸው ጠይቀዋል፡፡የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከመንገዶች ባለስልጣንና ሌሎች ተቋማት ጋር ባለመቀናጀቴ ባለፉት 40 አመታት በተገቢው መንገድ ሳልሰጥ የቆየሁትን ፍሳሽ ቆሻሻን የማስወገድ ስራ ከዚህ አመት ጀምሮ ቀልጠፍ ብዬ መስጠት እጀምራለሁም ብሏል፡፡

ቴዎድሮስ ብርሃኑ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 9፣2012/ የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ማለፊያ ነጥብን አሳውቋል

ፈተናውን ከወሰዱ 1.3 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች መካከል 912 ሺ 292 ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል ማለፍ የሚያስችላቸውን ውጤት አምጥተዋልም ብሏል ኤጀንሲው፡፡በመደበኛው፣ በማታና በግል የተፈተኑ ተማሪዎች ለወንዶች 2 ነጥብ እና ከዚያ በላይ ለሴቶች ደግሞ 1.86 እና ከዚያ በላይ የማለፊያ ነጥብ ነው ተብሏል፡፡መስማት የተሳናቸው ወንዶች 1.86 እና ሴቶች 1.71 እንዲሆንም ተወስኗል፡፡አይነስውራን ወንዶች 1.71 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ሴቶች 1.6 እና ከዚያ በላይ ማስመዝገብ ወደ ቀጣይ ክፍል ያዘዋውራቸዋል፡፡ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎችና የፀጥታ ችግር ላጋጠማቸው አካባቢዎች ለወንዶች 1.86 እና ለሴቶች 1.71 ማለፊያ ውጤት ነው ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ ወደ ቀጣይ ክፍል ከተዘዋወሩት ተማሪዎች መካከል 750 ሺ 174 ወንዶች ናቸው፡፡162 ሺ 118 ተማሪዎች ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን ሰምተናል፡፡በአጠቃላይ ወደ 11ኛ ክፍል ከተዘዋወሩ ተማሪዎች መካከል የሴቶች ድርሻ 17.77 በመቶ መሆኑን ከአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡የባለፈው አመት የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 2.71 እና ለሴቶች 2.57 እንደበር ታውቋል፡፡በግል ለተፈተኑት ወንዶች 3.43 እና ለሴቶች 3.14 የማለፊያ ውጤት ሆኖ መመዝገቡን የኤጀንሲው መረጃ ያመለክታል፡፡

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 9፣2012/ የሀገር ባለውለታ የሆኑ አረጋውያን ተመልካች አጥተው፣ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ወድቀው ይታያሉ

የሀገር ባለውለታ የሆኑ አረጋውያን ተመልካች አጥተው፣ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ወድቀው ይታያሉ፡፡ የእነዚህን አረጋውያን ህይወት በዘላቂነት ለመቀየር ምን መደረግ አለበት?


ማህሌት ታደለ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 9፣ 2012/ አዳዲስ ተሽከርካሪዎችን ለሚያስመጡ ባለሃብቶች የታክስ ማበረታቻ ሊደረግላቸው መሆኑ ተሰማ

አዳዲስ ተሽከርካሪዎችን ለሚያስመጡ ባለሃብቶች የታክስ ማበረታቻ ሊደረግላቸው መሆኑ ተሰማ፡፡በየነ ወልዴ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 8፣ 2012/ ባይተዋሮቹን ማን ይቅበራቸው? በሁለት የመንግስት መስሪያ ቤቶች አተካራ ምክንያት የባይተዋር ቀብር ተስተጓጉሏል

ባይተዋሮቹን ማን ይቅበራቸው ? በሁለት የመንግስት መስሪያ ቤቶች አተካራ ምክንያት የባይተዋር ቀብር ተስተጓጉሏል፡፡ ሆስፒታሎች ችግሩ ጠንቶብናል እያሉ ነው፡፡ሕይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 8 2012/ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ማዞር እንደ ብቸኛና የመጨረሻ አማራጭ ሊታይ አይገባም ተባለ

የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ማዞር እንደ ብቸኛና የመጨረሻ አማራጭ ሊታይ አይገባም ተባለ፡፡ የማህበራዊ ጥናት መድረክ የልማት ድርጅቶችን ወደ ግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ማዛወርን በተመለከተ ያዘጋጀው ውይይት ትናንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ንጋቱ ረጋሣ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 9፣2012/ በአዲስ አበባ በንግድ ሱቆችና ድርጅቶች ላይ በተደረገው ፍተሻና ክትትል በከተማዋ የዋጋ ንረትን በመጨመር የኑሮ ውድነትን አባብሰዋል የተባሉ 609 ድርጅቶችና የንግድ ሱቆች መታሸጋቸውንና ከ2 ሺህ 300 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ተነገረ

በዚህም መሰረት 93 ዳቦ ቤቶች፣ 91 ወፍጮ ቤቶች፣ 63 ስጋ ቤቶች፣ 56 አትክልት እና ፍራፍሬ ቤቶች፣ 55 የኮንስራትራክሽን እቃ መሸጫዎች፣ 53 እህል ቤቶችና 28 ምግብ ቤቶች ከታሸጉት መካከል እንደሚገኙበት የአዲስ አበባ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ተናግሯል፡፡የቢሮው ኃላፊና በምክትል ከንቲባ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ እንዳብራሩት መጋዘኖች፣ ሌሎች ማከማቻዎች፣ የችርቻሮ ሱቆችና በሌሎች ዘርፎች የሚገኙ ተቋማትም መታሸጋቸውን፣ ህገወጥ ድርጊት የፈፀሙት ድርጅቶችና የንግድ ሱቆችና ድርጅቶች አስተዳደራዊና የህግ እርምጃዎች እንደሚወሰድባቸው አመልክተዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በአትክልት ተራ ህገ ወጥ ንግድና ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር በተከናወነ ስራ በ59 መኪኖች ላይ የሚገኙ የአትክልትና የፍራፍሬ ምርቶች መያዛቸውንና ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲደርስ ተደርጓል ብለዋል፡፡ቢሮው ከአስተዳደሩ ገቢዎች ባለስልጣን፣ አቃቤ ህግ ቢሮ፣ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮና ፖሊስ ኮሚሽን ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የቁጥጥርና የህግ ማስከበር እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ህገ የማስከበር ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በቀጣይ ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚደረግ ኢንጂነር እንዳወቅ ተናግረዋል፡፡

በግብይት ሰንሰለት ውስጥ እሴት የማይጨምሩ የኑሮ ውድነትን እያባባሱ ያሉት ህገ ወጥ ደላሎችን ከሰንሰለቱ በመቁረጥ አምራችና አቅራቢ እንዲገናኙ የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚከናወኑም ተናግረዋል፡፡ከህግ ማስከበሩ ባለፈ የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት የመንግስት ልማት ድርጅቶችና የህብረት ስራ ማህበራት በምርት ስርጭት ውስጥ ገብተው ገበያውን የማረጋጋት ስራ እንዲሰሩ ይደረጋልም ብለዋል፡፡የአዲስ አበባ የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የኑሮ ውድነትን በተመለከተ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አስመልክቶ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ህብረተሰቡ የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን እያባባሱ የሚገኙትን ሕገ ወጥ አካላትን በመጠቆም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ መጠየቃቸውን በመረጃው ያሰፈረው ኢዜአ ነው፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 8፣ 2012/ በቦለቄ ጭነት ላይ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ ተገልብጦ 5 ሰዎች ሞቱ

በቦለቄ ጭነት ላይ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ ተገልብጦ 5 ሰዎች ሞቱ፡፡ ሰባት ሰዎች ለከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡


ወንድሙ ሀይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers