• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በፀደቀው የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት ማንኛውም ተቀጣሪ ከቅጥር ውጭ በተለያዩ ሥራዎች የሚያገኘውን ገቢ ግብር የሚከፍልበት ከደሞዙ ጋር ተደምሮ በሚገኘው መጠን ልክ ይሆናል ተባለ

ተሻሽሎ በቀረበውና ዛሬ በፀደቀው የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት ማንኛውም ተቀጣሪ ከቅጥር ውጭ በተለያዩ ሥራዎች የሚያገኘውን ገቢ ግብር የሚከፍልበት ከደሞዙ ጋር ተደምሮ በሚገኘው መጠን ልክ ይሆናል ተባለ…

ለምሣሌ አንድ ተቀጣሪ በተቀጠረበት ድርጅት የ3 ሺህ ብር ደመወዝተኛ ቢሆን ከቅጥር ውጭ በትርፍ ጊዜው ሰርቶ 10 ሺህ ብር ቢያገኝ በወሩ መጨረሻ ከስራው ውጭ ያገኘው 10 ሺህ ብር ከመደበኛ ደሞዙ ጋር ይደመራል፡፡ ግብር ሲከፍልም ለዛ ወር የ13 ሺህ ብር ደሞዝተኛ የሚከፍለውን ያህል ግብር ከደሞዙ ላይ ይቆረጣል ማለት ነው፡፡ አዋጁን ለማፅደቅ ዛሬ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባደረገው ውይይት ይህ አሰራር ተቀጣሪውን የሚጎዳ ነው የሚል አስተያየት ተሰጥቶ ነበር፡፡

በተሻሻለው የገቢ ግብር መሠረት ከ585 ብር በታች የሚያገኝ ደሞዝተኛ ከግብር ነፃ ይሆናል፡፡ ከ586 ብር እስከ 1 ሺህ 650 ብር ደሞዝተኛ የሆነ ደግሞ ከደሞዙ 10 በመቶ ግብር ይከፍላል፡፡

ከ1 ሺህ 653 እስከ 3 ሺህ 145 ብር የሚከፈለው ደሞዝተኛ 15 በመቶ የገቢ ግብር በየወሩ ይቀረጥበታል፡፡

ከ5 ሺህ 196 እስከ 7 ሺህ 758 ደሞዝ የሚያገኝ ደግሞ 25 በመቶ ፣ ከ7 ሺህ 759 እስከ 10 ሺህ 833 ብር ደሞዝተኛ ደግሞ 30 በመቶ የገቢ ግብር የሚከፍል ሲሆን ከ10 ሺህ 833 ብር በላይ የሚያገኝ ደሞዝተኛ ከደሞዙ 35 በመቶ የሚሆነው የገቢ ግብር መክፈል የሚጠበቅበት ይሆናል፡፡

 

በተጨማረም በቤት ኪራይና በንግድ ሥራ በወር 553 ብር ገቢ ከሚያገኙ ጀምሮ የተለያየ የመቶኛ ምጣኔ የገቢ ግብር የሚቆረጥባቸው መሆኑንም ሰምተናል፡፡

አዋጁ ከመፅደቁ በፊት ዛሬ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ባደረጉት ውይይት ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል ከመደበኛ ደመወዝ ውጭ ለቤት አበል ከሚሰጥ ገንዘብ ላይ የሚቆረጥን የገቢ ግብር የተመለከተው አንዱ ነው፡፡

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ገነት ታደሰ ለቤት አበል የሚሰጥ ገንዘብ ከደሞዝ ጋር ተደምሮ ስለሚቆረጠው የገቢ ግብር መልስ ሰጥተዋል፡፡

አዋጁ የሃገሪቱን ገቢ በራስ አቅም ለመሸፈን እንዲረዳ ከዚህ ቀደም ግብር የማይከፈልባቸውን የሥራ ዘርፎች ወደ ግብር ከፋይነት ለማስገባት የሚረዱ እንቀፆችን አካቷል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ደግሞ ከግብር ነፃ ያደረጋቸውም አሉ፡፡ ካለባቸው የወጭ ጫና የተነሳ በነዳጅ ፍለጋ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችና በንኡስ ተቋራጭነት የሚሰሩትን ከግብር ነፃ ካደረጋቸው መካከል ይገኙበታል፡፡

የበጀትና ፋይንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ገነት ነዳጅ ፍለጋ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች እስካሁን ፍላጐታቸው ተሳክቶ ኢትዮጵያ ነዳጅ ባታገኝም ካለባቸው የወጭ ጫና አንፃር እነሱ ላይ ግብር መጣሉ ለስራው እንዳይበረታቱ ያደርጋቸዋል የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡

የገቢ ግብር አዋጅ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ካፀደቃቸው ስድስት አዋጆች መካከል አንዱ ነው፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

 

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers