• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ኢትየጵያ በዚህ ዓመት ወደ ውጭ ከላከችው የተለያዩ የብረታ ብረት ምርቶች ከ22 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አግኝታለች ተባለ

ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ የሚልኩ የብረታ ብረት አምራች ኢንዱስትሪዎች 17 ገደማ ሆነዋል፡፡ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ፊጤ በቀለ ለሸገር ሲናገሩ ኢትየጵያ የብረት ምርቶችን ወደ ውጭ ለመላክ ልምምድ የጀመረችው በ2006 ሲሆን ያን ጊዜ ከ3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አግኝታበት ነበር፡፡

በዚህ አመት የኢንጂነሪንግ ውጤቶች፣ የጌጣ ጌጥ ምርቶችና የኤሌክትሪክ ሽቦዎች፣ የትራክተርና የእርሻ መሣሪያዎች ለውጭ ገበያ ቀርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ የብረታ ብረት ምርት በብዙዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች፣ በአሜሪካ፣ በየመንና ኖርዌይ እየተፈለገ መሆኑንም አቶ ፊጤ ተናግረዋል፡፡

የብረታ ብረት ኢንዱስትሪዎች ከውጭ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ሥራ ላይ የተጠመዱ ቢሆንም ለውጭ ገበያ ምርት ማቅረቡንም ጎን ለጎን እያስኬዱት መሆኑን ከአቶ ፈጤ ሰምተናል፡፡ የኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪዎች ከዚህ በላይ አምርተው ለውጭ ገበያ መላክ ቢችሉም በምንዛሪ አቅርቦት እጥረት አቅማቸው መገደቡን ሰምተናል፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers