• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

መስከረም 9፣2012/ በአዲስ አበባ በንግድ ሱቆችና ድርጅቶች ላይ በተደረገው ፍተሻና ክትትል በከተማዋ የዋጋ ንረትን በመጨመር የኑሮ ውድነትን አባብሰዋል የተባሉ 609 ድርጅቶችና የንግድ ሱቆች መታሸጋቸውንና ከ2 ሺህ 300 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ተነገረ

በዚህም መሰረት 93 ዳቦ ቤቶች፣ 91 ወፍጮ ቤቶች፣ 63 ስጋ ቤቶች፣ 56 አትክልት እና ፍራፍሬ ቤቶች፣ 55 የኮንስራትራክሽን እቃ መሸጫዎች፣ 53 እህል ቤቶችና 28 ምግብ ቤቶች ከታሸጉት መካከል እንደሚገኙበት የአዲስ አበባ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ተናግሯል፡፡የቢሮው ኃላፊና በምክትል ከንቲባ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ እንዳብራሩት መጋዘኖች፣ ሌሎች ማከማቻዎች፣ የችርቻሮ ሱቆችና በሌሎች ዘርፎች የሚገኙ ተቋማትም መታሸጋቸውን፣ ህገወጥ ድርጊት የፈፀሙት ድርጅቶችና የንግድ ሱቆችና ድርጅቶች አስተዳደራዊና የህግ እርምጃዎች እንደሚወሰድባቸው አመልክተዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በአትክልት ተራ ህገ ወጥ ንግድና ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር በተከናወነ ስራ በ59 መኪኖች ላይ የሚገኙ የአትክልትና የፍራፍሬ ምርቶች መያዛቸውንና ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲደርስ ተደርጓል ብለዋል፡፡ቢሮው ከአስተዳደሩ ገቢዎች ባለስልጣን፣ አቃቤ ህግ ቢሮ፣ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮና ፖሊስ ኮሚሽን ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የቁጥጥርና የህግ ማስከበር እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ህገ የማስከበር ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በቀጣይ ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚደረግ ኢንጂነር እንዳወቅ ተናግረዋል፡፡

በግብይት ሰንሰለት ውስጥ እሴት የማይጨምሩ የኑሮ ውድነትን እያባባሱ ያሉት ህገ ወጥ ደላሎችን ከሰንሰለቱ በመቁረጥ አምራችና አቅራቢ እንዲገናኙ የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚከናወኑም ተናግረዋል፡፡ከህግ ማስከበሩ ባለፈ የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት የመንግስት ልማት ድርጅቶችና የህብረት ስራ ማህበራት በምርት ስርጭት ውስጥ ገብተው ገበያውን የማረጋጋት ስራ እንዲሰሩ ይደረጋልም ብለዋል፡፡የአዲስ አበባ የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የኑሮ ውድነትን በተመለከተ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አስመልክቶ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ህብረተሰቡ የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን እያባባሱ የሚገኙትን ሕገ ወጥ አካላትን በመጠቆም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ መጠየቃቸውን በመረጃው ያሰፈረው ኢዜአ ነው፡፡

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers