• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ነሐሴ 16፣ 2011/ ከ145 በላይ በሆኑ የህክምና አገልግሎት ሰጭና መድሃኒት ሻጭ ተቋማት ላይ ቅጣት ተላለፈባቸው ተባለ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚሰሩ ከ23 ሺህ 500 በላይ ተቋማት ላይ በተደረገ ክትትል የጥራትና ብቃት እክል አለባቸው የተባሉ 145 ተቋማት እንደተቀጡ የከተማ አስተዳደሩ ተናግሯል፡፡አስተዳደሩ በአመቱ የስራ ክንውን ሪፖርቱ እንዳለው ከተቀጡት መካከል የግልና የመንግስት የጤና ተቋማት፣ የባህል ህክምና ማዕከላትና መድሃኒት ሻጮች ይገኙበታል፡፡

በተመሳሳይ በከተማዋ በሚሰሩ ከ31 ሺህ በላይ የምግብና የመጠጥ ድርጅቶችና ጤና ነክ ኢንዱስትሪዎች ላይ ቁጥጥር ተደርጓል ብሏል፡፡ችግር አለባቸው በተባሉ ከ3 ሺህ በላይ የምግብና የመጠጥ ድርጅቶች ላይም የተለያዩ ቅጣቶች ተላልፎባቸዋል ተብሏል፡፡ሃገራዊ የጤና ተቋማትን ደረጃ ያሟሉ 1 ሺህ 48 ሲሆኑ የውስጥ ጥራት የማረጋገጥ ሥርዓት የዘረጉ 721 መሆናቸውን ከሪፖርቱ ተመልክተናል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers