• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የአዲስ አበባ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮው ከመሬት ይዞታ አገልግሎት እና በሌሎችም ያልተገባ አሰራር ፈፅመው አግኝቻቸዋለሁ ያላቸው ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ላይ...

የአዲስ አበባ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮው ከመሬት ይዞታ አገልግሎት እና በሌሎችም ያልተገባ አሰራር ፈፅመው አግኝቻቸዋለሁ ያላቸው ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ተናገረ፡፡ቢሮው ከመሬት አስተዳደር ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለብልሹ አሰራር ሊጋለጥ የሚችል በመሆኑ በ2010 ዓ.ም 9 ወራት ባደረጉት ማጣራት ያልተገባ አሰራር ሲፈፅሙ ያገኘዋቸው አመራሮችና ሰራተኞች አሉ ብሏል፡፡

ከቢሮው የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ንጉስ ተሾመ እንደሰማነው ከከተማ አስተዳደሩ ጀምሮ በተደረገ ማጣራት 5 አመራሮች እና 128 ባለሙያዎች ያልተገባ አሰራር ሲፈፅሙ ተገኝተዋል ከስራ ማገድና ሌሎች እርጃዎችም ተወስዶዋል ብለዋል፡፡

ከበልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ በክፍለ ከተማ ደረጃ እስካሁንም ያልተፈቱ ችግሮች አሉ እነሱም በጊዜ ሂደት ለማስተካከል ቢሮው ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው ተብሏል፡፡በመሬት አስተዳደር ላይ የሚታዩት ችግሮች መፍትሄ እንዲሰጣቸው አሁንም በባለሙያዎች እና በአመራሩ ላይ የሚደረገው ክትትል ይቀጥላል መባሉን ሰምተናል፡፡

ምህረት ስዩም

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers